አዲስ አበባ ግንቦት 21/2009 አትሌት መሰረት ደፋር በቤጂንግ ኦሊምፒክ በአምስት ሺህ ሜትር ሴቶች ያስመዘገበችው የነሐስ ሜዳሊያ ወደ ብር አደገ።
ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዛሬ በላከው መረጃ እንዳመለከተው መሰረት ሜዳሊያው የተቀየረላት በወቅቱ ሁለተኛ ወጥታ የነበረችው በትውልድ ኢትዮጵያዊት በዜግነት ቱርካዊት አትሌት ኤልቫን አብይ ለገሰ የተከለከለ አበረታች መድሃኒት ተጠቅማ መገኘቷ ስለተረጋገጠ ነው።
አትሌት ኤልቫን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2007 እስከ 2009 ድረስ ያገኘችውን ክብር፣ ጥቅምና ሜዳሊያዎች ተነጥቃለች።
በ29ኛው የቤጂንግ ኦሊምፒክ በአምስት ሺህ ሜትር ሴቶች አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በአንደኝነት በማጠናቅቅ የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቷ ይታወሳል። አትሌት መሰረት ደፋር ደግሞ ሶስተኛ ነበር የወጣችው።
ሁለተኛ የወጣችው አትሌት አብይ ለገሰ ሜዳሊያዋን ስለተነጠቀች የመሰረት የነሐስ ሜዳሊያ ወደ ብር ማደግ ችሏል።
በወቅቱ አራተኛ ሆነ ያጠናቀቀችው ኬንዊቷ ሲሊቪ ኬቤት የነሐስ ሜዳሊያ ታገኛለች።
ከዚህ ቀደም አትሌት ሶፍያ አሰፋ በለንደን ኦሊምፒክ በሶስት ሺህ ሜትር መሰናክል ሴቶች ያገኘችው የነሐስ ሜዳሊያ ወደ ብር ማደጉ አይዘነጋም።
ኢትዮጵያ እስካሁን በተሳተፈችባቸው 13 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች 22 የወርቅ፣ 11 የብርና 20 የነሐስ በድምሩ 53 ሜዳሊያዎች መሰብሰብ ችላለች።

0 Comments
0 Shares