የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ሕንፃ በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው
የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ሊያስገነባ ነው:: የሕንፃው መሠረት ድንጋይ ማክሰኞ ሚያዚያ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. የኦሮሚያ ክልልና የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት በይፋ ተቀምጧል:: የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኦሕዴድ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ የኦሕዴድ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እና የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንትና የሥራና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓብይ አህመድ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማና ሌሎችም ተገኝተዋል:: ሕንፃው በቦሌ መንገድ የኦሮሚያ