ከወጣቶች አሥር ቢሊዮን ብር በጀት ተጠቃሚ ለመሆን ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሥራ አጦች ተመዘገቡ
የፌዴራል መንግሥት ለወጣቶች የሥራ ዕድል ከበጀተው አሥር ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የ3.3 ሚሊዮን ሥራ አጥ ወጣቶች ምዝገባ ተካሄደ፡፡ ቤት ለቤት በአገር አቀፍ ደረጃ ወጣቶቹን መመዝገቡን፣ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡ ሚኒስትሩ አቶ ርስቱ ይርዳው የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን የመለየት ሥራ በየክልሉ የቤት ለቤት ቅስቀሳና ግብረ ኃይል በማደራጀት እየተከናወነ ነው፡፡እስከ መጋቢት ወር 2009 ዓ.ም. ድረስ በተካሄደው ሥራ ፈላጊዎችን የመለየት ተግባር 3,337,983 ሥራ ፈላጊ ወጣቶች