ገንዘቤ ዲባባ በኡጂን የዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸነፈች

የስድስት ጊዜ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቷ ገንዘቤ ዲባባ በአሜሪካ ኡጂን የአምስት ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸነፈች።

ገንዘቤ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 14 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ ከ22 ማይክሮ ሰከንድ ወስዶባታል።

ገንዘቤ ትናንት ምሽት ውድድሩ ከመካሄዱ በፊት በእህቷ ጥሩነሽ ዲባባ የተያዘውን የ5 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን በመስበር ጭምር እንደምታሸንፍ ተናግራ ነበር።

ይሁንና ገንዘቤ ውድድሩን ስታሸንፍ የገባችበት ሠዓት ክብረ ወሰኑን እሰብረዋለሁ ካለችውና ጥሩነሽ ዲባባ እ.አ.አ 1985 ኦስሎ ላይ ካስመዘገበችው 14 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ከ15 ማይክሮ ሰከንድ የዓለም ክብረ ወሰን በ14 ሰከንድ የዘገየ ነው።

በትናንቱ የኡጂን የሴቶች የአምስት ሺህ ሜትር ሩጫ ገንዘቤን ተከትላ የገባችው ኬንያዊቷ ሊሊያን ካሳይት ስትሆን ውድድሩን ለማጠናቀቅ 14 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ ከ80 ማይክሮ ሰከንድ ወስዶባታል።

ውድድሩን ሶስተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና የኔዘርላንድስ ዜግነት ያላት ሲፋን ሀሰን ናት።
ገለቴ ቡርቃና ደራ ዲዳ አራተኛና አምስተኛ ሆነው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በኡጂን የዳይመንድ ሊግ ውድድር የወንዶች የአምስት ሺህ ሜትር ዛሬ ምሽት የሚካሄድ ሲሆን እንግሊዛዊው ሙሃመድ ፋራህና ከዚህ በፊት ፋራህን አስከትለው ያሸነፉት ኢትዮጵያዊያኑ ዮሚፍ ቀጄልቻና ኢብራሂም ጀይላን የሚያደረጉት ውድድር ይጠበቃል።

አዲስ አበባ ግንቦት 19/2009 (ኢዜአ)
ገንዘቤ ዲባባ በኡጂን የዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸነፈች የስድስት ጊዜ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቷ ገንዘቤ ዲባባ በአሜሪካ ኡጂን የአምስት ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸነፈች። ገንዘቤ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 14 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ ከ22 ማይክሮ ሰከንድ ወስዶባታል። ገንዘቤ ትናንት ምሽት ውድድሩ ከመካሄዱ በፊት በእህቷ ጥሩነሽ ዲባባ የተያዘውን የ5 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን በመስበር ጭምር እንደምታሸንፍ ተናግራ ነበር። ይሁንና ገንዘቤ ውድድሩን ስታሸንፍ የገባችበት ሠዓት ክብረ ወሰኑን እሰብረዋለሁ ካለችውና ጥሩነሽ ዲባባ እ.አ.አ 1985 ኦስሎ ላይ ካስመዘገበችው 14 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ከ15 ማይክሮ ሰከንድ የዓለም ክብረ ወሰን በ14 ሰከንድ የዘገየ ነው። በትናንቱ የኡጂን የሴቶች የአምስት ሺህ ሜትር ሩጫ ገንዘቤን ተከትላ የገባችው ኬንያዊቷ ሊሊያን ካሳይት ስትሆን ውድድሩን ለማጠናቀቅ 14 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ ከ80 ማይክሮ ሰከንድ ወስዶባታል። ውድድሩን ሶስተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና የኔዘርላንድስ ዜግነት ያላት ሲፋን ሀሰን ናት። ገለቴ ቡርቃና ደራ ዲዳ አራተኛና አምስተኛ ሆነው ውድድራቸውን አጠናቀዋል። በኡጂን የዳይመንድ ሊግ ውድድር የወንዶች የአምስት ሺህ ሜትር ዛሬ ምሽት የሚካሄድ ሲሆን እንግሊዛዊው ሙሃመድ ፋራህና ከዚህ በፊት ፋራህን አስከትለው ያሸነፉት ኢትዮጵያዊያኑ ዮሚፍ ቀጄልቻና ኢብራሂም ጀይላን የሚያደረጉት ውድድር ይጠበቃል። አዲስ አበባ ግንቦት 19/2009 (ኢዜአ)
Like
1
0 Comments 0 Shares