(EBC)- በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የስብሰባና ኤግዝቢሽን ማዕከልን በ120 ሚሊዮን ዶላር ለመገንባት ከቻይናው ሲጂሲኦሲ ጋር ስምምነት ተፈጽሟል፡፡

አዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ የስብሰባና ኤግዚብሽን ማእከል በአንድ ጊዜ እስከ 5 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ነው ተብሏል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ በባለድርሻዎች መዋጮ የሚከናወን ሲሆን ከባለድርሻ አካላቱ መካከል በዋነኝነት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፤ የንግድ ምክር ቤት፤ የአቢሲኒያ ባንክና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ይጠቀሳሉ፡፡

በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የስብሰባ ማዕከል መኖሩ የቢዝነስ፤ የንግድና የወጪ እንዲስፋፋ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡

ግንባታውም በ3 አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
(EBC)- በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የስብሰባና ኤግዝቢሽን ማዕከልን በ120 ሚሊዮን ዶላር ለመገንባት ከቻይናው ሲጂሲኦሲ ጋር ስምምነት ተፈጽሟል፡፡ አዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ የስብሰባና ኤግዚብሽን ማእከል በአንድ ጊዜ እስከ 5 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ነው ተብሏል፡፡ የማዕከሉ ግንባታ በባለድርሻዎች መዋጮ የሚከናወን ሲሆን ከባለድርሻ አካላቱ መካከል በዋነኝነት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፤ የንግድ ምክር ቤት፤ የአቢሲኒያ ባንክና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ይጠቀሳሉ፡፡ በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የስብሰባ ማዕከል መኖሩ የቢዝነስ፤ የንግድና የወጪ እንዲስፋፋ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡ ግንባታውም በ3 አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
0 Comments 0 Shares