WWW.ETHIOPIANREPORTER.COM
በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የምሕረት አዋጁን አለመጠቀማቸው መንግሥትን አሳስቧል
  4,000 ስደተኞች ብቻ የጉዞ ሰነድ ወስደዋልየሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በአገሪቱ በሕገወጥ መንገድ ኑሯቸውን የሚገፉ የውጭ ዜጎችን በተመለከተ ያወጣውን የምሕረት አዋጅ፣ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትጵያውያን እየተጠቀሙበት ባለመሆኑ የኢትዮጵያ መንግሥትን በእጅጉ አሳስቦታል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲሱ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የአገሪቱን ወቅታዊ የዲፕሎማሲ ሁኔታ አብራርተዋል፡፡ በተለይ በቅርቡ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩ ስደተኞችን በተመለከተ ያወጣውን አዋጅ አስመልክተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡በሳዑዲ ዓረቢያ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ከመጋቢት 21 እስከ ሰኔ 20 ቀን
0 Comments 0 Shares