በቁም እንስሳት ላይ የሚፈፀምን የኮንትሮባንድ ንግድ ለመከላከል ለአርብቶ አደሩ ምቹ የገበያ ሁኔታ ሊፈጠርለት ይገባል ተባለ።

ኢትዮጵያ በቁም እንስሳት ሀብቷ ከአፍሪካ በቀዳሚነት የምትገኝ ሲሆን፥ በዓለምም በዘርፉ ሰፊ ሀብት ካላቸው ጥቂት ሀገራት ተርታ ትመደባለች።

ይሁን እንጂ ይኸው ሀብቷ ለደላሎች እና ለህገወጥ ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ሲሳይ እየሆነ የሀብቷን ያህል መጠቀም ሳትችል የበይ ተመልካች በመሆን ብቻ ዓመታት ተቆጥረዋል።

በእንስሳት እና አሳ ሀብት ልማት ሚንስቴር የእንስሳት እና የእንስሳት ምርት ዳይሬክተሩ አቶ ፍቃዱ ጌታቸው እንደሚናገሩት፥ ህገወጥ የንግድ ሰንሰለቱ በሀገሪቱ ስር የሰደደ ነው።

በዚህም የቁም እንስሳት የኮንትሮባንድ ንግድ አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ የሚከናወን ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ሱማሌ፣ አፋር እና ቤንሻንጉልጉሙዝ፣ ትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።

በጎዴ፣ ቶጎ ጫሌ እና በባሌ አካባቢዎች ህገወጥ ደላሎቹ በስፋት የሚንቀሳቀሱበት ስፍራዎችም ሆነው ተለይተዋል።

በሀገር ደረጃ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመቆጣጠር ግብረ ሀይል የተቋቋመ ሲሆን፥ የአሳ እና እንስሳት ሀብት ልማት ሚንስቴር ችግሩን በጥናት መለየቱን ለማወቅ ችለናል።

እንሰሳቱን ከሀገር ለማስወጣት በሚደረገው ጥረት ውስጥ በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ሲውሉ የመኖ፣ የጥበቃ፣ የህክምና እና የመሳሰሉት አገልግሎቶችን ለሟሟላት የሚያስችል በጀት ባለመኖሩ እርምጃ ለመውሰድ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።

ይህንን ችግር በጥናት በመለየትም ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ አዲስ ስልት ቀይሷል።

ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የቁጥጥር ሂደቱን ህጋዊ ለማድረግ በህገወጥ መንገድ የሚያዙት እንስሳቶች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ህጋዊ ግብይት ተፈጽሞ የሚመለስ 30 ሚልየን ብር በጀት ለማስፀደቅ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን አቶ ፈቃዱ ተናግረዋል።

ከዚህ እንቅስቃሴ ጎን ለጎንም ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ስጋ እና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በቅንጅት አርብቶ አደሩን ከህገወጥ ደላሎች ለመነጠልና ረዥም የግብይት ሰንሰለቱን ለማሳጠር እየሰሩ እንደሆነም ለማወቅ ችለናል።

በኢትዮጵያ ስጋ እና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የስጋ፣ የማርና መኖ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ተቀባ እሸቴ፥ ኢንስቲትዩቱ አርሶ አደሩን እና ህጋዊ ነጋዴውን ለማቀራረብ እየሰራ እንደሆነ ነው የተናገሩት።

በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥ ያሉት ቄራዎች 57 ሺህ ቶን ስጋ በዓመት እያመረቱ ለዓለም አቀፍ ገበያ አያቀረቡ ነው።

በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው “አላና ኢንድያ” የተሰኘው ግዙፍ የቄራ ፋብሪካ ብቻውን ደግሞ 130 ሺህ ቶን የስጋ ምርት ማምረት የሚያስችል አቅም ይዞ ገበያው ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።

እነዚህ ሁኔታዎችም ለአርብቶ አደሩ ምቹ የገበያ አማራጮችን በመፍጠር ተጠቃሚነትን ያረጋግጣሉ ተብሎም በመንግስት ታምኖበታል።

የቁም እንስሳት ግብይትን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ በ2006 ዓ.ም ዘመናዊ የግብይት ስርዓት አዋጅ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል።

የአዋጁ መተግበር ወጣቶች ተደራጅተው በከብት ማድለብ እንዲሰማሩ እና የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ያስቻለ ቢሆንም፥ አርኪ በሚባል ደረጃ ግን አለመተግበሩን ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ማሳያ ናቸው።
በቁም እንስሳት ላይ የሚፈፀምን የኮንትሮባንድ ንግድ ለመከላከል ለአርብቶ አደሩ ምቹ የገበያ ሁኔታ ሊፈጠርለት ይገባል ተባለ። ኢትዮጵያ በቁም እንስሳት ሀብቷ ከአፍሪካ በቀዳሚነት የምትገኝ ሲሆን፥ በዓለምም በዘርፉ ሰፊ ሀብት ካላቸው ጥቂት ሀገራት ተርታ ትመደባለች። ይሁን እንጂ ይኸው ሀብቷ ለደላሎች እና ለህገወጥ ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ሲሳይ እየሆነ የሀብቷን ያህል መጠቀም ሳትችል የበይ ተመልካች በመሆን ብቻ ዓመታት ተቆጥረዋል። በእንስሳት እና አሳ ሀብት ልማት ሚንስቴር የእንስሳት እና የእንስሳት ምርት ዳይሬክተሩ አቶ ፍቃዱ ጌታቸው እንደሚናገሩት፥ ህገወጥ የንግድ ሰንሰለቱ በሀገሪቱ ስር የሰደደ ነው። በዚህም የቁም እንስሳት የኮንትሮባንድ ንግድ አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ የሚከናወን ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ሱማሌ፣ አፋር እና ቤንሻንጉልጉሙዝ፣ ትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። በጎዴ፣ ቶጎ ጫሌ እና በባሌ አካባቢዎች ህገወጥ ደላሎቹ በስፋት የሚንቀሳቀሱበት ስፍራዎችም ሆነው ተለይተዋል። በሀገር ደረጃ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመቆጣጠር ግብረ ሀይል የተቋቋመ ሲሆን፥ የአሳ እና እንስሳት ሀብት ልማት ሚንስቴር ችግሩን በጥናት መለየቱን ለማወቅ ችለናል። እንሰሳቱን ከሀገር ለማስወጣት በሚደረገው ጥረት ውስጥ በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ሲውሉ የመኖ፣ የጥበቃ፣ የህክምና እና የመሳሰሉት አገልግሎቶችን ለሟሟላት የሚያስችል በጀት ባለመኖሩ እርምጃ ለመውሰድ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። ይህንን ችግር በጥናት በመለየትም ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ አዲስ ስልት ቀይሷል። ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የቁጥጥር ሂደቱን ህጋዊ ለማድረግ በህገወጥ መንገድ የሚያዙት እንስሳቶች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ህጋዊ ግብይት ተፈጽሞ የሚመለስ 30 ሚልየን ብር በጀት ለማስፀደቅ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን አቶ ፈቃዱ ተናግረዋል። ከዚህ እንቅስቃሴ ጎን ለጎንም ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ስጋ እና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በቅንጅት አርብቶ አደሩን ከህገወጥ ደላሎች ለመነጠልና ረዥም የግብይት ሰንሰለቱን ለማሳጠር እየሰሩ እንደሆነም ለማወቅ ችለናል። በኢትዮጵያ ስጋ እና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የስጋ፣ የማርና መኖ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ተቀባ እሸቴ፥ ኢንስቲትዩቱ አርሶ አደሩን እና ህጋዊ ነጋዴውን ለማቀራረብ እየሰራ እንደሆነ ነው የተናገሩት። በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥ ያሉት ቄራዎች 57 ሺህ ቶን ስጋ በዓመት እያመረቱ ለዓለም አቀፍ ገበያ አያቀረቡ ነው። በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው “አላና ኢንድያ” የተሰኘው ግዙፍ የቄራ ፋብሪካ ብቻውን ደግሞ 130 ሺህ ቶን የስጋ ምርት ማምረት የሚያስችል አቅም ይዞ ገበያው ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል። እነዚህ ሁኔታዎችም ለአርብቶ አደሩ ምቹ የገበያ አማራጮችን በመፍጠር ተጠቃሚነትን ያረጋግጣሉ ተብሎም በመንግስት ታምኖበታል። የቁም እንስሳት ግብይትን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ በ2006 ዓ.ም ዘመናዊ የግብይት ስርዓት አዋጅ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል። የአዋጁ መተግበር ወጣቶች ተደራጅተው በከብት ማድለብ እንዲሰማሩ እና የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ያስቻለ ቢሆንም፥ አርኪ በሚባል ደረጃ ግን አለመተግበሩን ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ማሳያ ናቸው።
Like
1
0 Comments 0 Shares