ማንቼስተር ዩናይትድ የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩሮፓ ሊግ በእንግሊዙ ማንቼስተር ዩናይትድ አሸናፊነት ተጠናቋል።
የላንክሻየሩ ክለብ ትናንት ምሽት በስዊድን ፍሬንድስ አሬና በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ፥ የሆላንዱን አያክስ አምስተርዳምን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ፖል ፖግባ ከዕረፍት በፊት ሄንሪክ ሚኪታሪያን ደግሞ ከእረፍት መልስ የድል ጎሎችን ለማንቼስተር ዩናይትድ አስቆጥረዋል።
ድሉን ተከትሎም ማንቼስተር በትልቁ የአውሮፓ የክለቦች ውድድር በሆነው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ በቀጥታ መግባቱን አረጋግጧል።
በምሽቱ ጨዋታ በወጣቶች የተሞላው አያክስ አምስተርዳም በኳስ ቁጥጥር ሙሉውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የተሻለ ነበር።
የልምድ ማነስ እና የመሃል ሜዳውን የኳስ ቁጥጥር በሶስተኛው የሜዳ ክፍል መድገም አለመቻላቸው ግን የማንቼስተርን መረብ እንዳይደፍሩ አድርጓቸዋል።
ልምዳቸውን የተጠቀሙት ማንቸስተሮችም ወደ ትልቁ የአውሮፓ የክለቦች ውድድር መድረክ ለመመለስ ያደረጉት ጥረት ተሳክቶላቸዋል።
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆም በአውሮፓ መድረክ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ያሳኩትን ድል አራት ማድረስ ችለዋል።
ከፖርቶ ጋር የቀድሞውን የማህበረሰብ (አሁን ዩሮፓ ሊግ) እና የቻምፒየንስ ሊግ፣ ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ጋር ደግሞ ቻምፒየንስ ሊግን ሲያነሱ ትናንት ምሽት አራተኛውን ዋንጫ ከማንቼስተር ጋር በስቶኮልም አሳክተዋል።
ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሁለት የቻምፒየንስ ሊግ እና ሁለት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን በማንሳትም ብቸኛው አሰልጣኝ ሆነዋል።
ከጨዋታው በፊት በማንቼስተር ተዘጋጅቶ በነበረው የሙዚቃ ድግስ ላይ በደረሰው ጥቃት ለሞቱ ንጹሃን ዜጎች የህሊና ፀሎት ተደርጓል።
ከዚህ ባለፈም ማንቼስተር ዩናይትድ በጨዋታው ጥቁር ጨርቅ የተጫዋቾች ክንድ ላይ በማሰር ገብቷል።
በርካታ የክለቡ ደጋፊዎችም ተጫዋቾች ለከተማዋ መጽናኛ የሚሆነውን ድል ያስመዘግቡ ዘንድ የሚጠይቅ ባነር ይዘው ወደ ስታዲየም ገብተዋል።
ከድሉ በኋላም የማንቼስተር ተጫዋቾች የማንቼስተርን አንድነት የሚገልጽ ባነር በመያዝ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።
ማንቼስተር ዩናይትድ በአውሮፓ የክለቦች ውድድር ሶስት ትልልቅ ዋንጫዎችን በማንሳት አምስተኛው ክለብ ሆኗል።
የተሰረዘውን ካፕ ዊነርስ ካፕ፣ ቻምፒየንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግን በማሸነፍ፥ አያክስ፣ ባየር ሙኒክ፣ ቼልሲ እና ጁቬንቱስ ብቸኛዎቹ ክለቦች ነበሩ።
ትናንት ምሽት ይህን ማሳካት የቻለው ማንቼስተርም የአራቱን ክለቦች ጎራ መቀላቀል ችሏል።

0 Comments
0 Shares