የሜርኩሪ ማእድን አለን በማለት ከ9 ሚልየን ብር በላይ አንድን ግለሰብ በማጭበርበር ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በተባሉ አራት ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ።
ተከሳሾቹ ሬድዋን ሀሩን፣ እስክንድር ሰይድ፣ ሪዳ አሊ እና መሀመድ ቃይድ የሚባሉ ናቸው።
1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ነዋሪነታቸው በድሬዳዋ ከተማ እና በአዲስ አበባ ሲሆን፥ 3ኛ ተከሳሽ ግን በዜግነት ጅቡቲያዊ ናቸው።
የከሳሽ አቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር እንደሚያስረዳው፥ ግለሰቦቹ የማይገባቸውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ ቢላል የተባለን ግለሰብ የአቃቤ ህግ ሶስተኛ ምስክር የሆነ መስፍን የተባለ ግለሰብ እንዲያስተዋውቃቸው ያደርጉታል።
ከዚያም “የሜርኩሪው ባለቤቶች ድሬዳዋ ናቸው፤ ነገር ግን ሜርኩሪውን ለአረቦች ሊሸጡት ስለሆነ አንተ የገንዘብ አቅም ስላለህ ገዝተህ ተጠቀም” በማለት የግል ተበዳይን ያሳምኑታል።
በመሆኑም በአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ 1ኛ ተከሳሽ ሬድዋን ሀሩንና ሙክታር መሀመድ የተባለ ግለሰብ ከድሬዳዋ የመጡ ግለሰቦች መስለው የግል ተበዳይን ይተዋወቁታል።
ታህሳስ 21 ቀን 2008 ዓ.ም ከግል ተበዳይ መኖርያ ቤት በመሄድ ሜርኩሪውን እንፈትሸው በማለት ሙክታር መሀመድ የተባለው ግለሰብ ሜርኩሪ የተባለውን ቁስ ከጣቱ ቀለበት ጋር አንድ ላይ በመያዝ እና የተለያዩ ድምጾችን ጮክ ብሎ በማሰማት ሜርኩሪው ሰርቷል በማለት ጨብጠዋቸዋል ነው የተባለው።
ሙክታር የተባለው ግለሰብ፥ ከዚህ በኋላ ስራውን ከአረቦቹ ጋር ጨርስ በማለት ከቤቱ የወጣ ሲሆን፥ የግል ተባዳይም ባዩት ነገር ተስማምተው 500 ሺህ ብር ከባንክ አውጥተው ለ1ኛ ተከሳሽ እና መሀመድ አብደላ ለተባለ ግለሰብ እንደሰጧቸውም በክሱ ተጠቅሷል።
ግለሰቦቹ ገንዘቡን ከወሰዱ በኋላም በድጋሜ መጋቢት ወር 2008 ዓ.ም ሜርኩሪውን የሚገዛው አረብ ብሩን የሚልክልህ ባንተ ስም ስለሆነ ከሱ ላይ የሚቀነስ 4 ነጥብ 5 ሚልየን ብር ስጠን በማለት 1ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ገንዘቡን ከግል ተበዳዩ ግለሰብ ወስደዋል።
በዚህ ያላበቁት ግለሰቦቹ ከወራቶች ቆይታ በኋላ የጠፋነው አረብ አገር ለስራ ሄደን ነበር በማለት 1ኛ ተከሳሽ ስሙን በመቀየር ዶክተር ሪያድ በማለይ ግለሰቡን ከተዋወቀው በኋላ በስራ ጉዳይ አውርተዋል።
1ኛ ተከሳሽ ግለሰቡን ጅቡቲ ወደብ ላይ የውሃ መቆፈሪያ ማሽኖች አሉኝ በማለት ካሳመነው በኋላ፥ አንተ ሱሉልታ ለውሃ ምርት የሚሆን መሬት ፈልግ በማለት እንደተናገረው አቃቤ ህግ በክሱ አብራርቶታል።
ማሽኖቹንም ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሚል የ700 ሺህ ብር ቼክ እና 1 ነጥብ 2 ሚልየን ብር በአጠቃላይ ከ9 ሚልየን ብር በላይ ከግለሰቡ በማታለል ወስደዋል ነው ያለው አቃቤ ህግ በክሱ።
ከሳሽ አቃቤ ህግም ግለሰቦቹ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት የማታለል ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል።
ተከሳሾቹም ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛው የወንጀል ችሎት የዋስትና ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፥ አቃቤ ህግም ከወንጀሉ ክብደት እና 3ኛ ተከሳሽ የውጭ ዜግነት ያላቸው በመሆኑ በዋስትና ቢለቀቁ ላይቀርቡ ይችላሉ በማለት ዋስትናውን ተቃውሟል።
ፍርድ ቤቱም በዋስትናው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለከሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።