ኢትዮጵያ በተያዘው የአውሮፓዊያኑ 2018 ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ፈጣን እድገት እንደምታስመዘግብ ተገለፀ
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2018 ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ቀዳሚ እንደምትሆን ፎከስ ኢኮኖሚክስ የተባለ ተቋም ተነበየ፡፡ አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ትንታኔና ትንበያ በመስጠት የሚታወቀው ‹‹ፎከስ ኢኮኖሚ›› የተባለ ተቋም ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው እ.ኤ.አ በ2018 ኢትዮጵያ 7 ነጥብ 5 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ እንደምትሆን አመላክቷል፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም የአገሪቱ ጥቅል የምጣኔ ሀብት እድገት ባለ ሁለት አሃዝ ሆኖ እንደሚቀጥል ማስታወቁ ይታወቃል፡፡ በአንፃሩ በተመሳሳይ ጊዜ ጋና 6 ነጥብ 8 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ኢትዮጵያን የምትከተል ሀገር ናት ብሏል፡፡ በቀጠናው ሁለተኛ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እንደምታስመዘግብ የተነገረላት ጋናን በመከተል ታንዛኒያ 6 ነጥብ 5 በመቶ እድገት ይኖራታል ተብሏል፡፡ በቅድም ተከተልም ኬንያ፣ ሞዛምቢክ፣ ኮንጎ፣ ናይጄሪያ፣ አንጎላና ደቡብ አፍሪካ በቀጠናው ያላቸውን የኢኮኖሚ እድገት ደረጃ በትንበያው ተቀምጧል፡፡በ2018 ከሰሃራ በታች ያለው ክፍለ አህጉር አማካኝ የኢኮኖሚ እድገት 3 ነጥብ 3 በመቶ እንደሚሆን ትንበያው አስቀምጧል፡፡ ምንጭ፦ ጋና ቢዝነስ ኒውስ እና ኢቢሲ