WWW.ETHIOPIANREPORTER.COM
ለኢንዱስትሪ ፓርኮች 1,600 ሜጋ ዋት ኃይል እንዲቀርብ ተወሰነ
 በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በመገንባት ላይ ለሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች 1,600 ሜጋ ዋት ኃይል እንዲቀርብ መንግሥት ወሰነ፡፡መንግሥት በተለያዩ ክልሎች እያስገነባቸው ለሚገኙ ዘጠኝ ግዙፍ የኢንዱስትሪ ፓርኮች 1,600 ሜጋ ዋት ኃይል እንዲቀርብ ውሳኔውን ያሳለፈው ብሔራዊ የኢኮኖሚ ኮሚቴ ነው፡፡ ለሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲከፋፈል የተወሰነው 1,600 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል አገሪቱ በአሁኑ ወቅት ካላት 4,288 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም 37 በመቶ እንደሚሆን ሪፖርተር ያገኛቸው መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡መንግሥት ለዘመናት የቆየውን የአገሪቱን ኋላቀር የኢኮኖሚ መሠረት በመቀየር ወደ ኢንዱስትሪያል ኢኮኖሚ ለማሸጋገርና ወደፊትም ኢትዮጵያ የአፍሪካ የቀላል ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማዕከል እንድትሆን
0 Comments 0 Shares