በአገሪቱ የተከሰተውን ቀውስ ለማስቆም የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉ ተጠቆመ
ዘመኑ ተናኘ
Sun, 01/07/2018 - 11:35
በአገሪቱ የተከሰተውን ቀውስ ለማስቆም የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉ ተጠቆመ ዘመኑ ተናኘ Sun, 01/07/2018 - 11:35
WWW.ETHIOPIANREPORTER.COM
በአገሪቱ የተከሰተውን ቀውስ ለማስቆም የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉ ተጠቆመ | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic
በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰና በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለውን ቀውስ ለማስቆም፣ በርካታ የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉ ተጠቆመ፡፡ የአገር መከላከያ ሚኒስትርና የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጸሐፊ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ዓርብ ታኅሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የፌዴራልና የክልል የፀጥታ ምክር ቤቶች የተካሄደው የጋራ ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን ያሉት፡፡ ከአንድ ወር በፊት በአገሪቱ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት በፌዴራልና በክልሎች የጋራ ምክር ቤት ዕቅድ ወጥቶና መግባባት ተፈጥሮ ወደ ሥራ በመግባት በርካታ ለውጦች ቢመዘገቡም፣ ሕገወጦችን በቁጥጥር ሥር ከማዋል አኳያ የሚቀሩ ሥራዎች አሉ ብለዋል፡፡
Like
2
0 Comments 0 Shares