ለታክሲ ተጠቃሚዎች የካርድ ክፍያ ስርዓት ይፋ ተደረገ
ኢታ ሶሉሽን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከዳሸን ባንክ ጋር በመተባበር ለታክሲ ትራንስፖርት ፈላጊዎች የካርድ ክፍያ አሰራርን ይፋ አድርጓል።
ትናንት በሸራተን አዲስ ሆቴል የክፍያ ስርዓቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት የማህበሩ መስራች እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ገብረ ህይወት እንደገለፀው፤ የኢታ ኮርፖሬት እና ቅድመ ክፍያ እንዲሁም «የሎያሊቲ ካርዶችን» በኢንተርኔት አማካኝነት የመተግበሪያ «አፕ» በመጠቀም አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል። በኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን አፕሊኬሽን የመጀመሪያው «የሜትር ታክሲ» አገልግሎት መስጫ አፕሊኬሽን ሲሆን፤ አሁን ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት የበኩሉን ድርሻ ይወጣል።
የዳሸን ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው አለሙ በበኩላቸው አንደተናገሩት፤ ባንኩ የዚህን የክፍያ አገልግሎት ካርድ በቅርንጫፎቹ አማካኝነት ይሰጣል። በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለታገዘ አገልግሎት «ከኢታ ሶሉሽን» ጋር በጋራ መስራታቸው አስደስቷቸዋል።
ማህበሩ በኢትዮ ቴሌኮም የ8707 በነፃ የጥሪ ማእከል፣ በፌስቡክ፣በቴሌግራም እንዲሁም በመሰል የማህበራዊ ድረገፅ አማካኝነት የታክሲ አገልግሎት ለሚፈለጉ ደንበኞች ተደራሽ እንደሆነ ገልጿል። እስካሁን 53 ሺ 500 ደንበኞችን ከቦታ ወደ ቦታ እንዲጓጓዙ እድሉን ማመቻቸቱንም ተጠቅሷል።
ምንጭ:ጌጡ ተመስገን