በደቡብ ክልል የመንግስት ተሸከርካሪዎች ለግል ጥቅም የማዋል ተግባር እየተበራከተ ነው ተባለ
በክልሉ በህግ ከተፈቀደላቸው የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ውጪ የመንግስት ተሸከርካሪዎች ለግል ጥቅም የማዋል ተግባር እየተበራከተ መምጣቱን ታዛቢዎች ይናገራሉ።

ከስራ ተግባር ውጪ ለግል ጉዳይ ከመገልገል በዘለለ ሳይፈቀድላቸው መሪ የሚጨብጡ፣ ያለ ጥንቃቄ በማሽከርከር አሽከርካሪ ከስራ ውጪ በማድረግ ንብረቱንም የሚጎዱ ሃላፊዎች እንዳሉም ተገልጿል።

አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የጠሱ የክልሉ ነዋሪዎች፥ የህዝብ እና የመንግስት ሀብት የሆኑ ተሽከርካሪዎች ህጉ ከሚፈቅድላቸው ተግባራት ውጪ መሰማራታቸው ሊፈተሽ ይገባል ብለዋል።

የክልሉ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ናቹላ፥ ችግሩ በክልሉ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።

ይህ ተግባር አመራሩ ባለፈው ዓመት በተከናወነ የጥልቅ ተሀድሶ በተደጋጋሚ ግለ ሂስ ያወረደው የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን ዳይሬክተሩ ይናገራሉ።

በዚህም ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የመንግስትን ንብረቶች ለግል ጥቅም ማዋል የሚያስጠይቅ ህገወጥ ድርጊት ቢሆንም አመራሩ ከደርጊቱ አልተቆጠበም ብለዋል።

የመንግስት ተሽከርካሪ ለመንግስት ስራ ሲመደብ የአጠቃቀም ደምብ እንዳለው የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፥ አሁን ላይ በደንቡ አተገባበር ችግር እየተስተዋለ መሆኑን ይናገራሉ።

በዚህም ለችግሩ መፈትሔ ለመስጠት በክልሉ አዲስ መመርያ በዝግጅት ላይ ይገኛል ነው ያሉት።

አሁን የሚወጣው መመርያ ወቅቱ ከሚፈልገው፣ ህብረተሰቡ ከሚያቀርበው ጥያቄ እንዲሁም የመንግስት በጀት ለታለመለት ዓላማ ማዋል በሚያስቸል ሁኔታ በህግ በማስደገፍ እንደሚዘጋጅ ተነግሯል።
በደቡብ ክልል የመንግስት ተሸከርካሪዎች ለግል ጥቅም የማዋል ተግባር እየተበራከተ ነው ተባለ በክልሉ በህግ ከተፈቀደላቸው የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ውጪ የመንግስት ተሸከርካሪዎች ለግል ጥቅም የማዋል ተግባር እየተበራከተ መምጣቱን ታዛቢዎች ይናገራሉ። ከስራ ተግባር ውጪ ለግል ጉዳይ ከመገልገል በዘለለ ሳይፈቀድላቸው መሪ የሚጨብጡ፣ ያለ ጥንቃቄ በማሽከርከር አሽከርካሪ ከስራ ውጪ በማድረግ ንብረቱንም የሚጎዱ ሃላፊዎች እንዳሉም ተገልጿል። አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የጠሱ የክልሉ ነዋሪዎች፥ የህዝብ እና የመንግስት ሀብት የሆኑ ተሽከርካሪዎች ህጉ ከሚፈቅድላቸው ተግባራት ውጪ መሰማራታቸው ሊፈተሽ ይገባል ብለዋል። የክልሉ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ናቹላ፥ ችግሩ በክልሉ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል። ይህ ተግባር አመራሩ ባለፈው ዓመት በተከናወነ የጥልቅ ተሀድሶ በተደጋጋሚ ግለ ሂስ ያወረደው የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን ዳይሬክተሩ ይናገራሉ። በዚህም ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የመንግስትን ንብረቶች ለግል ጥቅም ማዋል የሚያስጠይቅ ህገወጥ ድርጊት ቢሆንም አመራሩ ከደርጊቱ አልተቆጠበም ብለዋል። የመንግስት ተሽከርካሪ ለመንግስት ስራ ሲመደብ የአጠቃቀም ደምብ እንዳለው የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፥ አሁን ላይ በደንቡ አተገባበር ችግር እየተስተዋለ መሆኑን ይናገራሉ። በዚህም ለችግሩ መፈትሔ ለመስጠት በክልሉ አዲስ መመርያ በዝግጅት ላይ ይገኛል ነው ያሉት። አሁን የሚወጣው መመርያ ወቅቱ ከሚፈልገው፣ ህብረተሰቡ ከሚያቀርበው ጥያቄ እንዲሁም የመንግስት በጀት ለታለመለት ዓላማ ማዋል በሚያስቸል ሁኔታ በህግ በማስደገፍ እንደሚዘጋጅ ተነግሯል።
0 Comments 0 Shares