በኢትዮጵያ የሚከበሩ በዓላትን ለመታደም ከውጪ የሚመጡ ጎብኝዎች ከመጡበት ዋናው የበዓል ስነ ስርዓት በተጨማሪ የሚዘጋጁ ልዩ ልዩ የባህል ዝግጅቶች የቆይታ ጊዜያቸውን እንዲያራዝሙ እያደረጋቸው መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት ከ256 ሺህ በላይ የውጪ ሀገራት ጎብኝዎችን አስተናግዳ፥ ከ959 ሚሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ገቢ አግኝታለች።

ይህ የጎብኝዎች ቁጥር ከ2 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረ መሆኑን ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከጉልበት ሰራተኞች እስከ ባለሀብቱ፣ ከትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እስከ አየር መንገድ የቱሪዝም ዘርፉ ከሚፈጥረው የስራ እድል ተጠቃሚዎች ናቸው።

በታህሳስ ወር መጨረሻ የሚከበረው የገና በዓልን ጨምሮ በጥምቀት በዓል ላይ በርካታ የውጪ ሀገራት ጎብኝዎች ይታደማሉ።

በዓላትን ምክንያት አድርገው ወደ ሀገር ከሚገቡ ጎብኝዎችም የቱሪዝም ዘርፉ የሚጠበቀውን ገቢ እንዲያስገኝ የሚያስችሉ ስራዎች በክልሎች እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስቴሩ ይገልጻል።

የጥምቀት በዓል በድምቀት በሚከበርባት ጎንደር ዘንድሮ የጎብኝዎችን ቆይታ የሚያራዝሙ፥ አዳዲስ ባህላዊ ዝግጅቶችን ለማቅረብ ዝግጅት መጀመሩን የአማራ ክልል ቅርስ ጥበቃ ባልስጣን አስታውቋል።

በባለስልጣኑ የቅርስ ጥበቃ እና ልማት ዳይሬክተር አቶ የሽዋስ ደሳለኝ ከባህል ሳምንት አውደ ርዕይና ባዛር በተጨማሪ የጥምቀት የቁንጅና ውድድር በማዘጋጀት የበዓሉን ባህላዊ ይዘት ለማጉላት ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

የጎብኝዎች ቁጥር እንዲጨምር እና ህብረተሰቡ ከዘርፉ የሚያገኘውን ተጠቃሚነት ማሳደግ የሚያስችሉ የመስህብ ስፍራዎችን የማስተዋወቅ ስራዎች በስፋት መሰራታቸውንም ተናግረዋል።

ከዚህ አንጻርም ጎብኝዎች ለጉብኝት በሚሄዱባቸው ስፍራዎች ቆይታቸውን እንዲያራዝሙ የሚያደርጉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ነው የገለፁት።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በዓላትን ተከትሎ አውደ ርዕይ፣ የንግድ ትርኢትና ባዛር፣ የባህላዊ ሙዚቃ ዝግጅትና የባህል ሳምንት በሚል የጎብኝዎችን ቆይታ ለማራዘም የሚደረጉ ጥረቶች ሊበረታቱ ይገባቸዋል ይላል።

በሚኒሰቴሩ የዓለም አቀፍና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ፥ ክልሎች የጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም በሚያከናውኗቸው የፈጠራ ስራዎች የአካባቢውን ዜጎች ተጠቃሚነት በቀላሉ ማሳደግ ያስችላቸዋል ነው ያሉት።

አቶ ገዛኸኝ በፈጠራ ስራዎቻቸው በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ውጤት የሚያመጡ ክልሎች የሚበረታቱበት አሰራር እየታሰበ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በባህል ልማት እና በመስህብ መዳረሻዎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች አጥጋቢ አለመሆናቸው የፈጠሩት ክፍተት፥ ሃገሪቱ ከቱሪዝም ዘርፉ እንዳትጠቀም እንዳደረጋት ይነገራል።

በዓመቱ መጨረሻ ከቱሪዝም ዘርፉ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፥ ሚኒስቴሩም የታቀደውን ገቢ ማግኘት እንዲቻል ዘላቂ የመሰረተ ልማት ግንባታ እና የመስህብ ስፍራዎች ጥበቃ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ይገልጻል።
በኢትዮጵያ የሚከበሩ በዓላትን ለመታደም ከውጪ የሚመጡ ጎብኝዎች ከመጡበት ዋናው የበዓል ስነ ስርዓት በተጨማሪ የሚዘጋጁ ልዩ ልዩ የባህል ዝግጅቶች የቆይታ ጊዜያቸውን እንዲያራዝሙ እያደረጋቸው መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት ከ256 ሺህ በላይ የውጪ ሀገራት ጎብኝዎችን አስተናግዳ፥ ከ959 ሚሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ገቢ አግኝታለች። ይህ የጎብኝዎች ቁጥር ከ2 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረ መሆኑን ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ከጉልበት ሰራተኞች እስከ ባለሀብቱ፣ ከትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እስከ አየር መንገድ የቱሪዝም ዘርፉ ከሚፈጥረው የስራ እድል ተጠቃሚዎች ናቸው። በታህሳስ ወር መጨረሻ የሚከበረው የገና በዓልን ጨምሮ በጥምቀት በዓል ላይ በርካታ የውጪ ሀገራት ጎብኝዎች ይታደማሉ። በዓላትን ምክንያት አድርገው ወደ ሀገር ከሚገቡ ጎብኝዎችም የቱሪዝም ዘርፉ የሚጠበቀውን ገቢ እንዲያስገኝ የሚያስችሉ ስራዎች በክልሎች እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስቴሩ ይገልጻል። የጥምቀት በዓል በድምቀት በሚከበርባት ጎንደር ዘንድሮ የጎብኝዎችን ቆይታ የሚያራዝሙ፥ አዳዲስ ባህላዊ ዝግጅቶችን ለማቅረብ ዝግጅት መጀመሩን የአማራ ክልል ቅርስ ጥበቃ ባልስጣን አስታውቋል። በባለስልጣኑ የቅርስ ጥበቃ እና ልማት ዳይሬክተር አቶ የሽዋስ ደሳለኝ ከባህል ሳምንት አውደ ርዕይና ባዛር በተጨማሪ የጥምቀት የቁንጅና ውድድር በማዘጋጀት የበዓሉን ባህላዊ ይዘት ለማጉላት ጥረት ይደረጋል ብለዋል። የጎብኝዎች ቁጥር እንዲጨምር እና ህብረተሰቡ ከዘርፉ የሚያገኘውን ተጠቃሚነት ማሳደግ የሚያስችሉ የመስህብ ስፍራዎችን የማስተዋወቅ ስራዎች በስፋት መሰራታቸውንም ተናግረዋል። ከዚህ አንጻርም ጎብኝዎች ለጉብኝት በሚሄዱባቸው ስፍራዎች ቆይታቸውን እንዲያራዝሙ የሚያደርጉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ነው የገለፁት። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በዓላትን ተከትሎ አውደ ርዕይ፣ የንግድ ትርኢትና ባዛር፣ የባህላዊ ሙዚቃ ዝግጅትና የባህል ሳምንት በሚል የጎብኝዎችን ቆይታ ለማራዘም የሚደረጉ ጥረቶች ሊበረታቱ ይገባቸዋል ይላል። በሚኒሰቴሩ የዓለም አቀፍና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ፥ ክልሎች የጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም በሚያከናውኗቸው የፈጠራ ስራዎች የአካባቢውን ዜጎች ተጠቃሚነት በቀላሉ ማሳደግ ያስችላቸዋል ነው ያሉት። አቶ ገዛኸኝ በፈጠራ ስራዎቻቸው በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ውጤት የሚያመጡ ክልሎች የሚበረታቱበት አሰራር እየታሰበ መሆኑንም ጠቁመዋል። በባህል ልማት እና በመስህብ መዳረሻዎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች አጥጋቢ አለመሆናቸው የፈጠሩት ክፍተት፥ ሃገሪቱ ከቱሪዝም ዘርፉ እንዳትጠቀም እንዳደረጋት ይነገራል። በዓመቱ መጨረሻ ከቱሪዝም ዘርፉ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፥ ሚኒስቴሩም የታቀደውን ገቢ ማግኘት እንዲቻል ዘላቂ የመሰረተ ልማት ግንባታ እና የመስህብ ስፍራዎች ጥበቃ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ይገልጻል።
0 Comments 0 Shares