በ270 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚተገበር የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሊዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

የኢንዱስትሪ ልማት ዘርፉ በሀገሪቱ ከሚፈጥረው ሰፊ የስራ እድል እና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ አቅም አንፃር የካፒታል እጥረት፣ የቴክኖሎጂ እና የንግድ ስራ እውቀት ውስንነት የዘርፉ ተግዳሮቶች ሆነው ቆይተዋል።

መንግስት እነዚህን የዘርፉ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን ቢገልፅም፥ ካለው ፍላጎት አንፃር ሰፊ ክፍተት እንዳለበት ነው በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች የሚያሳዩት።

ዛሬ ይፋ የተደረገው የ270 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ፕሮጀክትም፥ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ ጉድለቶችን በመሙላት ለዘርፉ እንቅስቃሴ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ነው የተባለው።

ፕሮጀክቱ አራት ምእራፎች ያሉት ሲሆን፥ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል የሚከናወን የ269 የአሜሪካ ዶላር በጀት ይኖረዋል።

የንግድ ስራ አገልግሎቱ ደግሞ ለ912 ኢንተርፕራይዞች በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ስልጠና ይሰጣል።

ስራዉንም በፌዴራል አነስተኛ እና መካከለኛ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ልማት ኤጀንሲ ስር የተቋቋመው የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት የሚያከናውነው ሲሆን፥ ለዚህም 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት አለው።

የኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር አቶ አስፋው አበበ፥ ዛሬ ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት ዋና አላማ በማሽን እጦት እና አቅም ውስንነት ምክንያት ወደ ማምረት ያልገቡ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ ክልሎችን ለማሳወቅ ነው ብለዋል።

ዋና ዳሬክተሩ በዚህ ሊዝ ፋይናንስ ተጠቃሚ የሚሆኑት ዘርፎች መለየታቸውን አስረድተዋል።

የሊዝ ፋይናንሱ ከአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በተጨማሪም በንግድ ፣ በአገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ እና አርሶ አደሮች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

ይህ ለአምስት ዓመት በሚቆየው ፕሮጀክት የሚገኘው ገንዘብ፥ 80 በመቶው ለማሽነሪዎች ግዢ፣ 20 በመቶው ደግሞ ለስራ ማስኬጃ የሚሆን የብድር አገልግሎት የሚውል ነው።

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ለኢንተርፕራይዞች የሚቀርብ ሲሆን፥ ለተዘነጉ እና በኢኮኖሚ ውስጥ የሚሳተፉ ኢንተርፕራይዞችን በሁለት መልኩ ተጠቃሚ ያደርጋል ሲሉ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የውጭ ገንዘብ እና ብድር አስተዳደር ዳይሬክተር ዶክተር በሀይሉ ካሴ ገልፀዋል።

ዶክተር በሀይሉ ኢንተርፕራይዞቹ የሊዝ ፋይናንስ ተጠቃሚ ሲሆኑ፥ እንደየ ፕሮጀክቱ የፋይናንስ እንቅስቃሴ የብድር አመላለሱ የሚወሰን ሆኖ እስከ ሰባት ዓመት የጊዜ ገደብ ይኖረዋል ነው ያሉት።

ልማት ባንኩ በፕሮጀክቱ የተገኘውን ገንዘብ የማስተዳደር ስራ ከመስራት ባሻገር፥ በራሱ 12 ሚሊየን ዶላር ወጪ በማድረግ 36 ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረጉንም ነው ዳይሬክተሩ ያብራሩት።

ለፕሮጀክቱ የሚውለው ገንዘብ በዓለም ባንክ ውስጥ ከሚገኘው የዓለም ልማት ማህበር እና ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የተገኘ ነው።
በ270 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚተገበር የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሊዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ ተደርጓል። የኢንዱስትሪ ልማት ዘርፉ በሀገሪቱ ከሚፈጥረው ሰፊ የስራ እድል እና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ አቅም አንፃር የካፒታል እጥረት፣ የቴክኖሎጂ እና የንግድ ስራ እውቀት ውስንነት የዘርፉ ተግዳሮቶች ሆነው ቆይተዋል። መንግስት እነዚህን የዘርፉ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን ቢገልፅም፥ ካለው ፍላጎት አንፃር ሰፊ ክፍተት እንዳለበት ነው በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች የሚያሳዩት። ዛሬ ይፋ የተደረገው የ270 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ፕሮጀክትም፥ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ ጉድለቶችን በመሙላት ለዘርፉ እንቅስቃሴ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ነው የተባለው። ፕሮጀክቱ አራት ምእራፎች ያሉት ሲሆን፥ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል የሚከናወን የ269 የአሜሪካ ዶላር በጀት ይኖረዋል። የንግድ ስራ አገልግሎቱ ደግሞ ለ912 ኢንተርፕራይዞች በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ስልጠና ይሰጣል። ስራዉንም በፌዴራል አነስተኛ እና መካከለኛ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ልማት ኤጀንሲ ስር የተቋቋመው የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት የሚያከናውነው ሲሆን፥ ለዚህም 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት አለው። የኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር አቶ አስፋው አበበ፥ ዛሬ ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት ዋና አላማ በማሽን እጦት እና አቅም ውስንነት ምክንያት ወደ ማምረት ያልገቡ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ ክልሎችን ለማሳወቅ ነው ብለዋል። ዋና ዳሬክተሩ በዚህ ሊዝ ፋይናንስ ተጠቃሚ የሚሆኑት ዘርፎች መለየታቸውን አስረድተዋል። የሊዝ ፋይናንሱ ከአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በተጨማሪም በንግድ ፣ በአገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ እና አርሶ አደሮች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል። ይህ ለአምስት ዓመት በሚቆየው ፕሮጀክት የሚገኘው ገንዘብ፥ 80 በመቶው ለማሽነሪዎች ግዢ፣ 20 በመቶው ደግሞ ለስራ ማስኬጃ የሚሆን የብድር አገልግሎት የሚውል ነው። ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ለኢንተርፕራይዞች የሚቀርብ ሲሆን፥ ለተዘነጉ እና በኢኮኖሚ ውስጥ የሚሳተፉ ኢንተርፕራይዞችን በሁለት መልኩ ተጠቃሚ ያደርጋል ሲሉ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የውጭ ገንዘብ እና ብድር አስተዳደር ዳይሬክተር ዶክተር በሀይሉ ካሴ ገልፀዋል። ዶክተር በሀይሉ ኢንተርፕራይዞቹ የሊዝ ፋይናንስ ተጠቃሚ ሲሆኑ፥ እንደየ ፕሮጀክቱ የፋይናንስ እንቅስቃሴ የብድር አመላለሱ የሚወሰን ሆኖ እስከ ሰባት ዓመት የጊዜ ገደብ ይኖረዋል ነው ያሉት። ልማት ባንኩ በፕሮጀክቱ የተገኘውን ገንዘብ የማስተዳደር ስራ ከመስራት ባሻገር፥ በራሱ 12 ሚሊየን ዶላር ወጪ በማድረግ 36 ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረጉንም ነው ዳይሬክተሩ ያብራሩት። ለፕሮጀክቱ የሚውለው ገንዘብ በዓለም ባንክ ውስጥ ከሚገኘው የዓለም ልማት ማህበር እና ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የተገኘ ነው።
0 Comments 0 Shares