ከሳዑዲ አረቢያ የተባረሩ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ በነበሩ ወቅት በደል
እንደደረሰባቸው ተናገሩ። አዲስ አበባ በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ አሶሴትድ
ፕሬስ ያነጋገራቸው ኢትዮጵውያን እንደሚሉት፤ ተደብድበዋል። ተዘርፈዋልም።
«የሳዑዲ አረቢያ ፖሊሶች ንብረቶቻችንን ዘርፈው ተከፋፍለውታል» ሲሉም
ወንጅለዋል። ከፖሊስ ከበባ ለማምለጥ የሞከሩ ኢትዮጵውያን በጥይት
ተመትተው፣ መቁስላቸውን አይተናል ሲሉ እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። ተመላሾቹ
በሳዑዲ በቆሸሹ የእስር ክፍሎች እንዲቆዩ መደረጋቸውንም ተናግረዋል። ወደ
400 ሺህ ገደማ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ እንደሚኖሩ የሚገመት ሲሆን
ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ 14 ሺህ ያህሉ መባረራቸውን የኢትዮጵያ መንግስት
አስታውቋል። ሰባ ሺህ ያህሉ ደግሞ በፍቃደኝነት ተመልሰዋል ብለዋል።
ዓለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ሳዑዲ አረቢያ የሰጠችው የምህረት
ጊዜ ካበቃ ካለፈው ሰኔ ወር ወዲህ ወደሀገራቸው በውዴታም ሆነ በግዴታ
የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 96 ሺህ ደርሷል ብሏል። የተመላሾቹ ቁጥር
በቀጣይ ሳምንታት ሊጨምር እንደሚችልም ገልጿል።

0 Comments
0 Shares