ወሎ ♥
የወሎ ሰው ማለት ምድነው ቅመሙ ??
የሚያስደነግጠው ገና ሲያዩት ደሙ ።
አድልቷል ፈጣሪ ሲሰራ ወሎየን
አቤት ውበታቸው እንግዳ ያላምዳል አቀባበላቸው

ከልብ የመነጨ ካንደበት የመጣ
ማር የተሸከመ ከሰው ሰው የወጣ
ቁም ነገር አዋቂ የወሎ ልጅ ማኛ
በፍቅር ያደገ ተጭዋች ቀልደኛ
የወሎ ልጅ ብርቱ ፍቅር የሰው ማኛ

ቱሉ ለሚ ሆኖ ይታያል ወለቃ :
አንገቷም ይመስላል የማሽላ መቃ ።
የወሎ ልጅና የጣት ወርቅ አንድ ነው
ሹልክ ያሉ እደሆን ፈላጊው ብዙ ነው

ለቦረና ልጆች እደህ እል ነበር
የውሎ ልጅ ባልሆን ይቆጨኝ ነበር

የፍቅር እጎቻ የሚቋደሱብሽ ♥
ሳቅና ጭዋታ ውበት ያደረብሽ
ይብላኝ ላላወቀሽ
መንፈሴ ይርካልሽ ሁሌም በትዝታሽ ።

ቁንጅናዋ ግሩም አደበቷ ለዛ
ያች የወሎ ልጅ ባለ ቁም ነገሯ ።
ወሎ ከአፈሩ ? ወይንስ ከአየሩ ?
መገን የወሎ ልጅ ትትናው ማማሩ
ፈገግታ አይለየው ሁሌ ከግባሩ ።

እኔስ ስለወሎ ምን ምኑን ልናገር
አጀብ ጉድ ያሰኛል ሁሉንም ብናገር
እንደው እቀር ነበር ሆደ እደነደደ
ምንኛ ደስ አለኝ ወሎ መወለዴ ።

አይቻለሁ ባይኔ ውበትና ፍቅር
እኔስ ለወሎ ልጅ አፈር ሁኜ ልቅር ።
እኔስ ከወሎ ልጅ ፈሪ ቢገኝብኝ
ከምሀል አገቴ ላይ ጋሪ ይነዳብኝ ።

ምን ያደርግልሻል ይህ ሁሉ መኳኳል
ወሎየ ነኝ ብትይ ስሙ ይበቃሻል ።
አውቄ ነውጂ እደው ስግደረደር
እኔስ ለወሎ ልጅ ውሀ ሺጨ ልደር

l . LOVE . WOIIO ♥♥
  • Public Group
  • 0 Posts
  • 0 Photos
  • News and Politics
Search
    No data to show