hiwot be Saudi
hiwot be Saudi
ፍለጋ
በቅርብ የተከናወኑ
  • *_*
    *_*
    0 Comments 0 Shares
  • የአረብ ሀገር ሴት ትልቅ ድክመት
    ለራሳችን አለማወቃችን ነው

    እራስን መለወጥና ከቤተሰብ ጥገኝነት መውጣት ቤትሰብን መርዳት መስሎ አይታየንም ፣ትተን የወጣነው ቤት ድባብ ሁሌ አእምሮአችን ላይ ይኖራል ፣ እኛ ካልሸመትን ጦም የሚድያሩ፣ እኛ ካላለበስን የሚታረዙ ይመስለናል፣ ከፊታችን የቀረበ ዶሮና እሩዝን እንኳን ለቤተሰቤ ብለን የምንመኝ ነን ፣የምንለብሰውን ኮምፈርትና ብርድልብስ ከላያችን ላይ ገፈን ሁሉንም ጭነን ብንልከው ያስደስተናል፣ለራሳችን 50ብር ለማውጣት ሰስተን ለቤተሰብ 1000ሪያል አውጥተን ሞባይል የምንገዛ ነን ፣ሀገራችን ለእረፍት ስንሄድ እዚህ ያለውን ሱቅ ገፍተን መውሰድና ከቤተሰብ እስከጎረቤት ማልበስ ብንችል የምንመኝ ነን፣ለፍተን ባመጣነው ብር ኮንትራት ታክሲ ስንይዝ ብንታይ የሚሾፍብን ነን፣ ቀሚስ በሸራጫማ ፣ቀይ ቦርሳ ቡትስ ....ወዘተ እያሉ የሚያላግጡብን ነን፡፡ ለመልበስ ፋሽን ለመከተልና ይህኛው የየትኛው ግዜ አለባበስ ነው የሚለውን ለማወቅ ግዜ ሳይኖረን ፣ከማድቤት ወደ ቶይሌት መወልወያና መጥረግያ ይዘን ስንሮጥ አመታት ይነጉዳሉ፣ ዩኒፎርም ወይም ሽቲ እንደለበስን ድፍን 24ወራት ወይም ከዛም በላይ ያልፋሉ ፣እንደሽቁር ማሰሮ ከላይ ስንጨምር ከስር ሲያንጠባጥብ እሱም አይሞላ እኛም ከልጅነታችን፣ካፍላነታችን ጣዕም፣ ከትምህርታችን ፣ከመዝናኛ ከምኑ ሳንል እድሜያችን ይንጉዳል፣ም.....ንይ.....ዤ ል....ግ...ባ?

    ይቅርታ አድጉገልኝ ፣ቤትሰብ ካልን

    እናትም የሚደግፋትን እና የማይደግፋትን ልጅ እኩል አትወድም፣እህትም ወንድምም ስትሰጠውና ሳትሠጠው እኩል አያከብርም፣ጓደኛም እንደቸገረህ ሲያውቅ አይጠጋህም፣ ጋባዡም ሆይ ሆይ የሚልህ እስካለህ ነው፡፡
    አንዳንዷ ለፍታ እንዲጠራቀምላት ወደሀገር የምታሽሸውን ብር አለኝ ብላ ስትገባ ምንም ሳታገኝ ቀርታ በብስጭት በባህር በየብስ ሳትል ትመለሳለች፣አንዳንድ ቤተሰብ ስምሽን እንኳን አቆመጳጵሶ ሲጠራ እንዳልነበር ተመልሰሽ ቤትሽ ስትሄጂ " መቼነው ምትመለሽው ስንትወር ነው ምትቆይው?" ይልሻል፡
    አንዳንድ ወላጅ ጭራሽ ምን ያደገግችልኝ ነው ብሎም ይናራገል ፣(በጆሮዬ የሰማሁት ነው)

    ታድያ መቼ ነው ለራሳችን የምንኖረው?
    ጋብቻ መጥቶላቸው "ቤተሰቤን ሳለውጥ አላገባም" ብለው የሚመልሱ ሴቶች ብዙ ናቸው፣ ምንድነው ምንለውጠው??? ፣እንኳን በአረብ ሀገር ብር ፣መሬት ቆፍረን ነዳጅ ብናወጣ አይለወጡም ፣የ3ተኛው አለም ያውም የኢትዮጵያ ቤተሰብ በአንድ ልጃቸው ላብ ይለወጣሉ ማለት ቀልድ ነው ፣መርዳት አንድ ነገር ነው ፣የቤተሰብን ችግር ለመቅረፍ ማሰብ ግን የራስን እድሜ መቅጨት ነው፡፡

    ተጎሳቅሎም ይሁን ለፍቶ ልጅን አሳድጎ አስተምሮ ለቁም ነገር ማድረስ የላወጅ ግዴታ ነው፣ ሳይበላ ልጁን ማብላት ፊጥራ ነው፣ ፈጣሪ በወላጅና ልጅ መሃል የፈጠረው ትስስር ነው፣ እኛ ሀበሾች ግን ውለዱን ብለናቸው ለኛ ሲሉ የወለዱን ፣9ወር አርግዙን ብለናቸው ያረገዙን ፣ ማብላት ማስተማር ግዴታ ሳይኖርባቸው ያበሉን ያስተማሩን አይነት ውለታ እንቆጥረዋለን፣ ይህ ውለታ አይደለም ግዴታ ነው ፣ከወለዱ በየትኛውም ስችዌሽን ማሳደግ ግዴታቸው ነው፣ ጭራሽ ካልቻሉ ይጥላሉ ፣አዎ ወልደው የሚጥሉም አሉ፡፡

    ወላጅን መርዳት ግዴታ ሳይሆን ውዴታ ነው፣እኔ እንደእናት ልጄ አድጋ፣ እራሷን ችላ ፣በእግሯ ቆማ ፣ሰው ሆና ማየት እንጂ ደርሳ ብድሯን ልትመልስ አልጠብቅም ፣ምንም ብድርም እዳም የለባትም፣ ፈልጌ ነው የወለድኳት፡፡

    መውለድ ካልቻሉ ተስለው ፣ሺዎች ብሮች ከፍለው ህክምና ወስደው የሚወልዱት ፣እኛን እዝህች ምድር ላይ አምጥተው ፣መሬት ምን እንደምትመስል ሊያሳዩን ጓጉተውልን አይደለም፣መውለድ የሚባል የሆነ እድሜ ላይ መሆን ያለበት ነገር ስላለ ወላጅ ለመሆን ፈልገው ነው፤አቅፈው ለመሳም ነው፤ለስሜታቸውም ይሆናል፡፡

    9ወር ሳረግዝ ለልጄ ብዬ አይደለም፣ሳምጥና ያንን ሊነገር የማያስችል ስቃይ ሳሳልፍ ለልጄ ብዬ አይደለም ለራሴ እንጂ፣አባት ማርገዝና መውለድ ቢችልኮ "በል እንግዲህ ካቻምና እኔ ወልጃለሁ ዘንድሮ እራስህ አርግዝና ውለድ" ብለን በተሟገትን ነበር፣ተፈጥሮ የጣለችብንን አርግዞ አምጦ መውለድ እንደትልቅ ውለታ ልናየው አይገባም፡፡

    ወላጆችን የመርዳት ፍላጎትም እኛ ውስጥ የሚፈጠረው ወላጆቻችን በሰጡን ፍቅር ልክ ነው እንጂ ስላሳደጉን አይደለም፣ ካፋቸው ነጥቀው ስላበሉንም አይደለም ፣እንስሳት ሁሉ ይህን ያደርጋሉ ፣አእዋፍ ለሊት ተነስተው እህል ፈልገው፣ በአፋቸው ይዘው መጥተው ጫጩቶቻቸውን ይመግባሉ፣መብረር እንደጀመረች "ዳይ ብረሪ ኑሪ "ብለው ይተዋታል ፣ይህ ፍቅር ግን ውለታ አይደለም፣ ወላጆች ለልጄቻቸው ትክክለኛ ፍቅር ካላቸው እራስ ወዳድ አይሆኑም፤ልጃቻቸው ሰው ሆነው ማየት ነው ሚያስደስታቸው፣ተደላድለህ ስትኖር እንዳልደገፍካቸው ከፍቶህ እላያቸው ላይ ብትኖር "ይሄ ሸክም" ከማለት የማይመለሱም አሉ፡፡

    በልክ እናድርገው ፣እራስን ማሸነፍ ከጥገኝነት መላቀቅ በራሱ ቤተሰብን መርዳት ነው፣8 እና9አመት የለፋቹበትን እየላካቹ ባለቀ እድሜና ሰአት ወላጅ ላይ ከመመለስ አንድ ሱቅ ከፍቶ እራስን መቻል የተሻለ ነው፡፡

    ቤተሰባቹን አትርዱ አላልኩም ግን ከዙርያቹ ተማሩ ፣እዚህ አገር ያልሰማነውና ያላየነው አሰቃቂና አሳዛኝ የየግል ታሪኮች የሉም ፡፡ ዛሬ 10ሺና 20ሺ ስትኩከለት የነበረ ወንድም እህት አጎት ምንትስ ነገ 1ሺብርን መጠየቅ ያሳፍራችኋል፣ ሰጪ መሆን ደስ ይላል ፣ሰዎችን መርዳት እርካንታን ይሰጣል ፣ሰው ደግሞ ብዙ ስትሰጡት ብዙ ይጠብቃል፤ እባችካሁ ለራሳቹም እያሰባችሁ፡፡

    ቢር አልዋሊደይን
    ስለተረገዘበት፣ ስለተማጠበት ፣ስለታዘለበት ....ስታስተምሩ
    ወላጆችንም የልጆቻቸውንም ሀቅ እንዲብቁ አስተምሯቸው

    እንዳትቀየሙኝ አፍወን
    መልካም ቀን
    የአረብ ሀገር ሴት ትልቅ ድክመት ለራሳችን አለማወቃችን ነው እራስን መለወጥና ከቤተሰብ ጥገኝነት መውጣት ቤትሰብን መርዳት መስሎ አይታየንም ፣ትተን የወጣነው ቤት ድባብ ሁሌ አእምሮአችን ላይ ይኖራል ፣ እኛ ካልሸመትን ጦም የሚድያሩ፣ እኛ ካላለበስን የሚታረዙ ይመስለናል፣ ከፊታችን የቀረበ ዶሮና እሩዝን እንኳን ለቤተሰቤ ብለን የምንመኝ ነን ፣የምንለብሰውን ኮምፈርትና ብርድልብስ ከላያችን ላይ ገፈን ሁሉንም ጭነን ብንልከው ያስደስተናል፣ለራሳችን 50ብር ለማውጣት ሰስተን ለቤተሰብ 1000ሪያል አውጥተን ሞባይል የምንገዛ ነን ፣ሀገራችን ለእረፍት ስንሄድ እዚህ ያለውን ሱቅ ገፍተን መውሰድና ከቤተሰብ እስከጎረቤት ማልበስ ብንችል የምንመኝ ነን፣ለፍተን ባመጣነው ብር ኮንትራት ታክሲ ስንይዝ ብንታይ የሚሾፍብን ነን፣ ቀሚስ በሸራጫማ ፣ቀይ ቦርሳ ቡትስ ....ወዘተ እያሉ የሚያላግጡብን ነን፡፡ ለመልበስ ፋሽን ለመከተልና ይህኛው የየትኛው ግዜ አለባበስ ነው የሚለውን ለማወቅ ግዜ ሳይኖረን ፣ከማድቤት ወደ ቶይሌት መወልወያና መጥረግያ ይዘን ስንሮጥ አመታት ይነጉዳሉ፣ ዩኒፎርም ወይም ሽቲ እንደለበስን ድፍን 24ወራት ወይም ከዛም በላይ ያልፋሉ ፣እንደሽቁር ማሰሮ ከላይ ስንጨምር ከስር ሲያንጠባጥብ እሱም አይሞላ እኛም ከልጅነታችን፣ካፍላነታችን ጣዕም፣ ከትምህርታችን ፣ከመዝናኛ ከምኑ ሳንል እድሜያችን ይንጉዳል፣ም.....ንይ.....ዤ ል....ግ...ባ? ይቅርታ አድጉገልኝ ፣ቤትሰብ ካልን እናትም የሚደግፋትን እና የማይደግፋትን ልጅ እኩል አትወድም፣እህትም ወንድምም ስትሰጠውና ሳትሠጠው እኩል አያከብርም፣ጓደኛም እንደቸገረህ ሲያውቅ አይጠጋህም፣ ጋባዡም ሆይ ሆይ የሚልህ እስካለህ ነው፡፡ አንዳንዷ ለፍታ እንዲጠራቀምላት ወደሀገር የምታሽሸውን ብር አለኝ ብላ ስትገባ ምንም ሳታገኝ ቀርታ በብስጭት በባህር በየብስ ሳትል ትመለሳለች፣አንዳንድ ቤተሰብ ስምሽን እንኳን አቆመጳጵሶ ሲጠራ እንዳልነበር ተመልሰሽ ቤትሽ ስትሄጂ " መቼነው ምትመለሽው ስንትወር ነው ምትቆይው?" ይልሻል፡ አንዳንድ ወላጅ ጭራሽ ምን ያደገግችልኝ ነው ብሎም ይናራገል ፣(በጆሮዬ የሰማሁት ነው) ታድያ መቼ ነው ለራሳችን የምንኖረው? ጋብቻ መጥቶላቸው "ቤተሰቤን ሳለውጥ አላገባም" ብለው የሚመልሱ ሴቶች ብዙ ናቸው፣ ምንድነው ምንለውጠው??? ፣እንኳን በአረብ ሀገር ብር ፣መሬት ቆፍረን ነዳጅ ብናወጣ አይለወጡም ፣የ3ተኛው አለም ያውም የኢትዮጵያ ቤተሰብ በአንድ ልጃቸው ላብ ይለወጣሉ ማለት ቀልድ ነው ፣መርዳት አንድ ነገር ነው ፣የቤተሰብን ችግር ለመቅረፍ ማሰብ ግን የራስን እድሜ መቅጨት ነው፡፡ ተጎሳቅሎም ይሁን ለፍቶ ልጅን አሳድጎ አስተምሮ ለቁም ነገር ማድረስ የላወጅ ግዴታ ነው፣ ሳይበላ ልጁን ማብላት ፊጥራ ነው፣ ፈጣሪ በወላጅና ልጅ መሃል የፈጠረው ትስስር ነው፣ እኛ ሀበሾች ግን ውለዱን ብለናቸው ለኛ ሲሉ የወለዱን ፣9ወር አርግዙን ብለናቸው ያረገዙን ፣ ማብላት ማስተማር ግዴታ ሳይኖርባቸው ያበሉን ያስተማሩን አይነት ውለታ እንቆጥረዋለን፣ ይህ ውለታ አይደለም ግዴታ ነው ፣ከወለዱ በየትኛውም ስችዌሽን ማሳደግ ግዴታቸው ነው፣ ጭራሽ ካልቻሉ ይጥላሉ ፣አዎ ወልደው የሚጥሉም አሉ፡፡ ወላጅን መርዳት ግዴታ ሳይሆን ውዴታ ነው፣እኔ እንደእናት ልጄ አድጋ፣ እራሷን ችላ ፣በእግሯ ቆማ ፣ሰው ሆና ማየት እንጂ ደርሳ ብድሯን ልትመልስ አልጠብቅም ፣ምንም ብድርም እዳም የለባትም፣ ፈልጌ ነው የወለድኳት፡፡ መውለድ ካልቻሉ ተስለው ፣ሺዎች ብሮች ከፍለው ህክምና ወስደው የሚወልዱት ፣እኛን እዝህች ምድር ላይ አምጥተው ፣መሬት ምን እንደምትመስል ሊያሳዩን ጓጉተውልን አይደለም፣መውለድ የሚባል የሆነ እድሜ ላይ መሆን ያለበት ነገር ስላለ ወላጅ ለመሆን ፈልገው ነው፤አቅፈው ለመሳም ነው፤ለስሜታቸውም ይሆናል፡፡ 9ወር ሳረግዝ ለልጄ ብዬ አይደለም፣ሳምጥና ያንን ሊነገር የማያስችል ስቃይ ሳሳልፍ ለልጄ ብዬ አይደለም ለራሴ እንጂ፣አባት ማርገዝና መውለድ ቢችልኮ "በል እንግዲህ ካቻምና እኔ ወልጃለሁ ዘንድሮ እራስህ አርግዝና ውለድ" ብለን በተሟገትን ነበር፣ተፈጥሮ የጣለችብንን አርግዞ አምጦ መውለድ እንደትልቅ ውለታ ልናየው አይገባም፡፡ ወላጆችን የመርዳት ፍላጎትም እኛ ውስጥ የሚፈጠረው ወላጆቻችን በሰጡን ፍቅር ልክ ነው እንጂ ስላሳደጉን አይደለም፣ ካፋቸው ነጥቀው ስላበሉንም አይደለም ፣እንስሳት ሁሉ ይህን ያደርጋሉ ፣አእዋፍ ለሊት ተነስተው እህል ፈልገው፣ በአፋቸው ይዘው መጥተው ጫጩቶቻቸውን ይመግባሉ፣መብረር እንደጀመረች "ዳይ ብረሪ ኑሪ "ብለው ይተዋታል ፣ይህ ፍቅር ግን ውለታ አይደለም፣ ወላጆች ለልጄቻቸው ትክክለኛ ፍቅር ካላቸው እራስ ወዳድ አይሆኑም፤ልጃቻቸው ሰው ሆነው ማየት ነው ሚያስደስታቸው፣ተደላድለህ ስትኖር እንዳልደገፍካቸው ከፍቶህ እላያቸው ላይ ብትኖር "ይሄ ሸክም" ከማለት የማይመለሱም አሉ፡፡ በልክ እናድርገው ፣እራስን ማሸነፍ ከጥገኝነት መላቀቅ በራሱ ቤተሰብን መርዳት ነው፣8 እና9አመት የለፋቹበትን እየላካቹ ባለቀ እድሜና ሰአት ወላጅ ላይ ከመመለስ አንድ ሱቅ ከፍቶ እራስን መቻል የተሻለ ነው፡፡ ቤተሰባቹን አትርዱ አላልኩም ግን ከዙርያቹ ተማሩ ፣እዚህ አገር ያልሰማነውና ያላየነው አሰቃቂና አሳዛኝ የየግል ታሪኮች የሉም ፡፡ ዛሬ 10ሺና 20ሺ ስትኩከለት የነበረ ወንድም እህት አጎት ምንትስ ነገ 1ሺብርን መጠየቅ ያሳፍራችኋል፣ ሰጪ መሆን ደስ ይላል ፣ሰዎችን መርዳት እርካንታን ይሰጣል ፣ሰው ደግሞ ብዙ ስትሰጡት ብዙ ይጠብቃል፤ እባችካሁ ለራሳቹም እያሰባችሁ፡፡ ቢር አልዋሊደይን ስለተረገዘበት፣ ስለተማጠበት ፣ስለታዘለበት ....ስታስተምሩ ወላጆችንም የልጆቻቸውንም ሀቅ እንዲብቁ አስተምሯቸው እንዳትቀየሙኝ አፍወን መልካም ቀን
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    2
    1 Comments 0 Shares
More Stories