• ኢንተርፕራይዙ በዘጠኝ ወራት ካቀደው በታች 11.8 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል
    የአገሪቱን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ ዓለም አቀፍ ባህሮችን የሚያቆራርጠው ግዙፉ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፐራይዝ፣ በአገሪቱ በተፈጠረው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባቀደው መጠን ገቢ ዕቃዎችን ማጓጓዝ ሳይችል ቀረ፡፡

    ሐሙስ ሚያዝያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለሚመራው የኢንተርፐራይዙ ሥራ አመራር ቦርድ በቀረበው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ አስመጪዎች በቂ የውጭ ምንዛሪ ባለማግኘታቸውና የዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ዘርፍ በመቀዛቀዙ የታሰበውን ያህል አልተሄደም፡፡

    በተለይ የንግዱ ማኅበረሰብ ኤልሲ (L/C) በበቂ ደረጃ መክፈት ባለመቻሉ፣ ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት አገር ውስጥ ለማስገባት ያቀደው 136,116 ኮንቴይነሮችን ቢሆንም፣ በአፈጻጸሙ ግን 131,834 ኮንቴይነሮች ገብተዋል፡፡

    በገቢ ረገድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኢንተርፕራይዙ በአጠቃላይ 14.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ቢያቅድም፣ ማሳካት የቻለው ግን 11.8 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

    የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ተፈራ፣ ረቡዕ ሚያዝያ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 40 ኤጀንቶች ጋር ባካሄዱት ውይይት ወቅት ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የምታመነጨው የውጭ ምንዛሪ ውስን እንደመሆኑ ቅድሚያ የሚሰጠው ለተመረጡ ዘርፎች መሆኑን ገልጸው፣ ከዚህ አንፃር የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመኖሩ በተለይ በወራት ተከፋፍሎ ሲታይ ባለፈው መጋቢት የገቢ ዕቃ ቅናሽ አሳይቷል ብለዋል፡፡ ‹‹በአሁኑ ወቅት ኤልሲ እየተከፈተ በመሆኑ የገቢ ዕቃ ጭማሪ ይኖራል፤›› ሲሉ አቶ መስፍን በቀጣዮቹ ወራት የተሻለ አፈጻጸም ሊኖር እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

    በሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ በተያዘው የበጀት ዓመት የውጭ ምንዛሪ በበቂ ደረጃ አላገኘም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2010 በርካታ መርከቦች ተገንብተው አብዛኛዎቹ ወደ ሥራ በመግባታቸው የሥራ ሽሚያ ተከስቷል፡፡ በዚህ ምክንያት የገበያ መቀዛቀዝ ብቻ ሳይሆን፣ የባህር ትራንስፖርት የመጓጓዣ ዋጋ ላይም ቅናሽ እንዲከሰት አድርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዓለም የንግድ እቅንስቃሴ እየቀዘቀዘ በመሆኑ፣ በርካታ የዘርፉ ተዋናዮች ሥራ እያገኙ አይደለም ሲሉ የወቅቱን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡

    የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ የፕላንና ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሲራጅ አቡዱላሂ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ኢንተርፕራይዙ ባሉት 11 መርከቦችና ከውጭ በሚከራያቸው መርከቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ የባህር ወሽመጦችን እያቋረጠ 309 ወደቦችን ያዳርሳል ብለዋል፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የንግድ መዳረሻ የሆኑት የሩቅ ምሥራቅ አገሮች፣ መካከለኛው ምሥራቅና ቱርክ ዋነኛ መዳረሻዎቹ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

    አቶ መስፍን እንዳሉት፣ ኢንተርፕራይዙ ካለፈው ዓመት የተሸጋገሩ ገቢ ዕቃዎች ስለነበሩ በማጓጓዝ በኩል 98 በመቶ፣ በገቢ በኩል ደግሞ ከጂቡቲ ወደብ የሚነሱ ዕቃዎች ስለነበሩ በአጠቃላይ 90 በመቶ አፈጻጸም አስመዝግቧል፡፡

    ኢንተርፕራይዙ ከባህር ጉዞ በተጨማሪ በአገሪቱ በተገነቡ ሰባት ደረቅ ወደቦች 417 ከባድ ተሽከርካሪዎችን በማሰማራት የማጓጓዝ ሥራዎችን እንደሚያከናውን ታውቋል፡፡

    ኢንተርፕራይዙ በዘጠኝ ወራት ካቀደው በታች 11.8 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል የአገሪቱን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ ዓለም አቀፍ ባህሮችን የሚያቆራርጠው ግዙፉ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፐራይዝ፣ በአገሪቱ በተፈጠረው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባቀደው መጠን ገቢ ዕቃዎችን ማጓጓዝ ሳይችል ቀረ፡፡ ሐሙስ ሚያዝያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለሚመራው የኢንተርፐራይዙ ሥራ አመራር ቦርድ በቀረበው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ አስመጪዎች በቂ የውጭ ምንዛሪ ባለማግኘታቸውና የዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ዘርፍ በመቀዛቀዙ የታሰበውን ያህል አልተሄደም፡፡ በተለይ የንግዱ ማኅበረሰብ ኤልሲ (L/C) በበቂ ደረጃ መክፈት ባለመቻሉ፣ ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት አገር ውስጥ ለማስገባት ያቀደው 136,116 ኮንቴይነሮችን ቢሆንም፣ በአፈጻጸሙ ግን 131,834 ኮንቴይነሮች ገብተዋል፡፡ በገቢ ረገድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኢንተርፕራይዙ በአጠቃላይ 14.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ቢያቅድም፣ ማሳካት የቻለው ግን 11.8 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ተፈራ፣ ረቡዕ ሚያዝያ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 40 ኤጀንቶች ጋር ባካሄዱት ውይይት ወቅት ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የምታመነጨው የውጭ ምንዛሪ ውስን እንደመሆኑ ቅድሚያ የሚሰጠው ለተመረጡ ዘርፎች መሆኑን ገልጸው፣ ከዚህ አንፃር የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመኖሩ በተለይ በወራት ተከፋፍሎ ሲታይ ባለፈው መጋቢት የገቢ ዕቃ ቅናሽ አሳይቷል ብለዋል፡፡ ‹‹በአሁኑ ወቅት ኤልሲ እየተከፈተ በመሆኑ የገቢ ዕቃ ጭማሪ ይኖራል፤›› ሲሉ አቶ መስፍን በቀጣዮቹ ወራት የተሻለ አፈጻጸም ሊኖር እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ በሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ በተያዘው የበጀት ዓመት የውጭ ምንዛሪ በበቂ ደረጃ አላገኘም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2010 በርካታ መርከቦች ተገንብተው አብዛኛዎቹ ወደ ሥራ በመግባታቸው የሥራ ሽሚያ ተከስቷል፡፡ በዚህ ምክንያት የገበያ መቀዛቀዝ ብቻ ሳይሆን፣ የባህር ትራንስፖርት የመጓጓዣ ዋጋ ላይም ቅናሽ እንዲከሰት አድርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዓለም የንግድ እቅንስቃሴ እየቀዘቀዘ በመሆኑ፣ በርካታ የዘርፉ ተዋናዮች ሥራ እያገኙ አይደለም ሲሉ የወቅቱን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ የፕላንና ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሲራጅ አቡዱላሂ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ኢንተርፕራይዙ ባሉት 11 መርከቦችና ከውጭ በሚከራያቸው መርከቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ የባህር ወሽመጦችን እያቋረጠ 309 ወደቦችን ያዳርሳል ብለዋል፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የንግድ መዳረሻ የሆኑት የሩቅ ምሥራቅ አገሮች፣ መካከለኛው ምሥራቅና ቱርክ ዋነኛ መዳረሻዎቹ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ አቶ መስፍን እንዳሉት፣ ኢንተርፕራይዙ ካለፈው ዓመት የተሸጋገሩ ገቢ ዕቃዎች ስለነበሩ በማጓጓዝ በኩል 98 በመቶ፣ በገቢ በኩል ደግሞ ከጂቡቲ ወደብ የሚነሱ ዕቃዎች ስለነበሩ በአጠቃላይ 90 በመቶ አፈጻጸም አስመዝግቧል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ከባህር ጉዞ በተጨማሪ በአገሪቱ በተገነቡ ሰባት ደረቅ ወደቦች 417 ከባድ ተሽከርካሪዎችን በማሰማራት የማጓጓዝ ሥራዎችን እንደሚያከናውን ታውቋል፡፡
    0 Comments 0 Shares
  • የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና በመባል የምትታወቀው አዲስ አበባ ደረጃቸውን የጠበቁ በቂ ሆቴሎች እንደሌላት ሲነገር ቆይቷል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በርካታ ሆቴሎች እየተገነቡ በሮቻቸውን ለእንግዶች እየከፈቱ ነው። እንደ አዲስ አበባ ሆቴሎች ማኅበር ገለጻ በየሁለት ወራት ሦስት ሆቴሎች ገበያውን እየተቀላቀሉ
    ነው። በአሁኑ ወቅት 52 የሆቴል ፕሮጀክት በሒደት ላይ እንደሆኑ ታውቋል። ወደ ገበያ ለመግባት ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁ ሆቴሎች መካከል ሳፋየር አዲስ ሆቴል አንዱ ነው። ሳፋየር አዲስ ሆቴል ቴሌ መድኃኔዓለም አካባቢ በ1,300
    ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ነው። 130 የመኝታ ክፍሎች፣ ሁለት ሬስቶራንቶች ሦስት ባሮች፣ ጂምናዚየም፣ ስፓና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን አሟልቶ መያዙ ተገልጿል። አቶ ፍስሐ ዓባይ በተባሉ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት የተገነባው
    አዲስ ሳፋየር ሆቴል ግንቦት 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል። በምሥሉ ላይ የሚታየው ባለ አሥር ፎቅ ሕንፃ አዲስ ሳፋየር ሆቴል ነው።
    የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና በመባል የምትታወቀው አዲስ አበባ ደረጃቸውን የጠበቁ በቂ ሆቴሎች እንደሌላት ሲነገር ቆይቷል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በርካታ ሆቴሎች እየተገነቡ በሮቻቸውን ለእንግዶች እየከፈቱ ነው። እንደ አዲስ አበባ ሆቴሎች ማኅበር ገለጻ በየሁለት ወራት ሦስት ሆቴሎች ገበያውን እየተቀላቀሉ ነው። በአሁኑ ወቅት 52 የሆቴል ፕሮጀክት በሒደት ላይ እንደሆኑ ታውቋል። ወደ ገበያ ለመግባት ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁ ሆቴሎች መካከል ሳፋየር አዲስ ሆቴል አንዱ ነው። ሳፋየር አዲስ ሆቴል ቴሌ መድኃኔዓለም አካባቢ በ1,300 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ነው። 130 የመኝታ ክፍሎች፣ ሁለት ሬስቶራንቶች ሦስት ባሮች፣ ጂምናዚየም፣ ስፓና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን አሟልቶ መያዙ ተገልጿል። አቶ ፍስሐ ዓባይ በተባሉ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት የተገነባው አዲስ ሳፋየር ሆቴል ግንቦት 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል። በምሥሉ ላይ የሚታየው ባለ አሥር ፎቅ ሕንፃ አዲስ ሳፋየር ሆቴል ነው።
    WWW.ETHIOPIANREPORTER.COM
    አዲስ ሳፋየር ሆቴል አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው
    የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና በመባል የምትታወቀው አዲስ አበባ ደረጃቸውን የጠበቁ በቂ ሆቴሎች እንደሌላት ሲነገር ቆይቷል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በርካታ ሆቴሎች እየተገነቡ በሮቻቸውን ለእንግዶች እየከፈቱ ነው። እንደ አዲስ አበባ ሆቴሎች ማኅበር ገለጻ በየሁለት ወራት ሦስት ሆቴሎች ገበያውን እየተቀላቀሉነው። በአሁኑ ወቅት 52 የሆቴል ፕሮጀክት በሒደት ላይ እንደሆኑ ታውቋል። ወደ ገበያ ለመግባት ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁ ሆቴሎች መካከል ሳፋየር አዲስ ሆቴል አንዱ ነው። ሳፋየር አዲስ ሆቴል ቴሌ መድኃኔዓለም አካባቢ በ1,300ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ነው። 130 የመኝታ ክፍሎች፣ ሁለት ሬስቶራንቶች ሦስት ባሮች፣ ጂምናዚየም፣ ስፓና
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    3
    0 Comments 2 Shares
  • Like
    1
    0 Comments 1 Shares
  • Like
    4
    1 Comments 0 Shares
  • እነኝህን የሀገርኛ ፊልም ርዕሶች ልብ በሉልኝማ፦

    ወንድሜ ያዕቆብ፣ የገጠር ልጅ፣ አስረሽ ፍቺው (ከጭፍራ)፣ የሰርጌ ለታ፣ 400 ፍቅር፣ መሐረቤን…፣ ቦምቡ ፍቅርሽ፣ ዛከረ፣ ባዶ ነበር፣ ፍቅሬን ያያችሁ፣ እያንጓለለ፣ ኢቫንጋዲ፣ ጊዜ ለኩሉ፣ የወደዱ ሰሞን፣ ከመጠን በላይ፣ ከባቢሎን ማዶ (ከእንግሊዝኛው)፣ ሔዋን እንደዋዛ፣ የማትበላ ወፍ፣ የሎስ፣ ወደ ሀገር ቤት፣ ባትመጪም ቅጠሪኝ (ግጥም)፣ አይራቅ፣ አኩኩሉ፣ ቁልፉን ስጪኝ፣ የፍቅር ነገር፣ ቼ በለው፣ እቴጌ፣ሰምታ ይሆን እንዴ፣ አትሂጂብኝ፣ አፋጀሽኝ፣ ወዘተ።

    ሁሉም የሀገርኛ ዘፈን ርዕሶች ወይም አካላት ናቸው። ቀጣዮቹ ደግሞ ፋሽን የሆኑ ይመስላል።

    ቀሚስ የለበስኩ‘ለት፣ የነገርኩሽ ዕለት፣ ያበድኩ‘ለት፣ ወዘተ።

    አጋጣሚ ወይስ "ያጣ ሰው ሌባ ነው" እየተባለ የተፈጸመ ዓይን ያወጣ ዝርፊያ።
    እነኝህን የሀገርኛ ፊልም ርዕሶች ልብ በሉልኝማ፦ ወንድሜ ያዕቆብ፣ የገጠር ልጅ፣ አስረሽ ፍቺው (ከጭፍራ)፣ የሰርጌ ለታ፣ 400 ፍቅር፣ መሐረቤን…፣ ቦምቡ ፍቅርሽ፣ ዛከረ፣ ባዶ ነበር፣ ፍቅሬን ያያችሁ፣ እያንጓለለ፣ ኢቫንጋዲ፣ ጊዜ ለኩሉ፣ የወደዱ ሰሞን፣ ከመጠን በላይ፣ ከባቢሎን ማዶ (ከእንግሊዝኛው)፣ ሔዋን እንደዋዛ፣ የማትበላ ወፍ፣ የሎስ፣ ወደ ሀገር ቤት፣ ባትመጪም ቅጠሪኝ (ግጥም)፣ አይራቅ፣ አኩኩሉ፣ ቁልፉን ስጪኝ፣ የፍቅር ነገር፣ ቼ በለው፣ እቴጌ፣ሰምታ ይሆን እንዴ፣ አትሂጂብኝ፣ አፋጀሽኝ፣ ወዘተ። ሁሉም የሀገርኛ ዘፈን ርዕሶች ወይም አካላት ናቸው። ቀጣዮቹ ደግሞ ፋሽን የሆኑ ይመስላል። ቀሚስ የለበስኩ‘ለት፣ የነገርኩሽ ዕለት፣ ያበድኩ‘ለት፣ ወዘተ። አጋጣሚ ወይስ "ያጣ ሰው ሌባ ነው" እየተባለ የተፈጸመ ዓይን ያወጣ ዝርፊያ።
    0 Comments 0 Shares
  • ታሪክን የኋሊት
    (አሌክስ አብርሃም)
    በአገራችን ትልቁ የህዝብ ሽንት ቤት ፒያሳ ላይ የተሰራው ልክ የዛሬ ብዙ አመት ነበር (በግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት) ….የሽንት ቤቱን ህንፃ ለመስራት የፈረንሳይ የሥነ-ሽንት ቤት (የሥነ -ህንፃ ባለሙያዎች ) ወደኢትዮጲያ መጥተው ነበር (እውነተኛ ታሪክ ነው)
    ታዲያ የገረመኝ ይሄ አይደለም በዘመኑ የነበረ አንድ ጋዜጠኛ ስለሽንት ቤቱ በኢትዮጲያ ሬዲዮ ያቀረበው ዘገባ ነበር
    ‹‹ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሰ ነገስት ኢትዮጲያ በጎ ፈቃድ ለህዝባቸው በማሰብ እና በመቆርቆር የውጭ አገር ማሃንዲሶችን ከፈረንሳይ አገር በማስመጣት ያስገነቡት (((በትልቅነቱ ከአፍሪካአንደኛ ከአለም ሁለተኛ የሆነ መፀዳጃ ቤት ዛሬ ለህዝብ ጥቅም ይውል ዘንድ ተመርቆ ተከፍቷል )))
    ጋዜጠኝነት ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ዛሬ ላይ የት ደረሰ ብለን ስንጠይቅ??????????????????????????????????????????????????????????????????????
    ታሪክን የኋሊት (አሌክስ አብርሃም) በአገራችን ትልቁ የህዝብ ሽንት ቤት ፒያሳ ላይ የተሰራው ልክ የዛሬ ብዙ አመት ነበር (በግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት) ….የሽንት ቤቱን ህንፃ ለመስራት የፈረንሳይ የሥነ-ሽንት ቤት (የሥነ -ህንፃ ባለሙያዎች ) ወደኢትዮጲያ መጥተው ነበር (እውነተኛ ታሪክ ነው) ታዲያ የገረመኝ ይሄ አይደለም በዘመኑ የነበረ አንድ ጋዜጠኛ ስለሽንት ቤቱ በኢትዮጲያ ሬዲዮ ያቀረበው ዘገባ ነበር ‹‹ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሰ ነገስት ኢትዮጲያ በጎ ፈቃድ ለህዝባቸው በማሰብ እና በመቆርቆር የውጭ አገር ማሃንዲሶችን ከፈረንሳይ አገር በማስመጣት ያስገነቡት (((በትልቅነቱ ከአፍሪካአንደኛ ከአለም ሁለተኛ የሆነ መፀዳጃ ቤት ዛሬ ለህዝብ ጥቅም ይውል ዘንድ ተመርቆ ተከፍቷል ))) ጋዜጠኝነት ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ዛሬ ላይ የት ደረሰ ብለን ስንጠይቅ??????????????????????????????????????????????????????????????????????
    0 Comments 0 Shares
  • ሐመልማል አባተን ከልቤ ነው የማከብራት
    (አሌክስ አብርሃም)
    ሐመልማል አባተን የሚያስተዋውቀኝ ሰው ቢኖር እመርቀዋለሁ !(ኧረ ማስተዋወቁ ይቅር በጣም እንደምገረምባት የሚነግርልኝ ቢኖር ከወዲሁ እድሜውን ይስጥህ ብየ በቀብድ ነበር የማንበሸብሸው) ከልቤ የማከብራት ድምፃዊት ነች ! የሆነ የሽልማት ድርጅት ምናምን ቢኖረኝ ‹‹ ያለፉት 15 ዓመታት ሃቅ ተነጋሪ ›› ብየ ነበር አስር ዋንጫ አስራአምስት ሜዳሊያ የምሸልማት ! እስኪ የሃመልማልን ኢንተርቪውአዳምጦ የሚያውቅ ሰው አበዛሃው ይበለኝ ! በቃ ማንንም አትፈራም ! የተሰማትን እንደወረደ ቁጭ ነው !! ረዥዥዥም እድሜ ይስጣት !(እንደውም በቃ ዝም ብላ ብትኖርስ ያለቁጥር ያለስፍር)
    ሐመልማል አባተን ከልቤ ነው የማከብራት (አሌክስ አብርሃም) ሐመልማል አባተን የሚያስተዋውቀኝ ሰው ቢኖር እመርቀዋለሁ !(ኧረ ማስተዋወቁ ይቅር በጣም እንደምገረምባት የሚነግርልኝ ቢኖር ከወዲሁ እድሜውን ይስጥህ ብየ በቀብድ ነበር የማንበሸብሸው) ከልቤ የማከብራት ድምፃዊት ነች ! የሆነ የሽልማት ድርጅት ምናምን ቢኖረኝ ‹‹ ያለፉት 15 ዓመታት ሃቅ ተነጋሪ ›› ብየ ነበር አስር ዋንጫ አስራአምስት ሜዳሊያ የምሸልማት ! እስኪ የሃመልማልን ኢንተርቪውአዳምጦ የሚያውቅ ሰው አበዛሃው ይበለኝ ! በቃ ማንንም አትፈራም ! የተሰማትን እንደወረደ ቁጭ ነው !! ረዥዥዥም እድሜ ይስጣት !(እንደውም በቃ ዝም ብላ ብትኖርስ ያለቁጥር ያለስፍር)
    0 Comments 0 Shares