• 0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎች በዘጠና ቀናት ውስጥ እንዲወጡ ካዘዛ በኋላ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳያጋጥማቸው የፌደራል ተቋማት እና የክልል መንግስታት በቅንጅት እንዲሰሩ መመሪያ ተላለፈ።

    የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ከመጋቢት 21 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በሀገሪቱ የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች ለቀው እንዲወጡ ያወጀው የ90 ቀናት የምህረት አዋጅ መተግበር ከጀመረ ዛሬ 26 ቀናት ሆኖታል።

    በዚህ የምህረት አዋጅ ውስጥም የኢፌዴሪ መንግስት ኢዮጵያውያን እንግልት ሳይደርስባቸው በ90 ቀናት ውስጥ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ፥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚከታተል ብሄራዊ ኮሚቴ አቋቁሟል።

    ዛሬም ይሄው ኮሚቴ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበዬሁ ሰብሳቢነት የእስካሁኑን እንቅስቃሴ ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

    የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በስብሰባው ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመጡ ዜጎችን ለመቀበል የፌደራል ተቋማትና ክልሎች በትብብር እንዲሰሩ ተወስኗል።

    ከዚህ ባለፈም ክልሎች የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን እንደገና እንዲቋቋሙ እና ከክልል ከተሞች እስከ ወረዳ ከተሞች ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ እንዲያደርጉ የቀረበው ሀሳብም ፀድቋል።

    በዚህም አዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ገቢወች እና ጉምሩክ፣ ፖሊስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ አጠናክረው በመቀጠል እንግልት እንዳይደርስባቸው መስራት እንደሚገባቸውም ኮሚቴው አጽንኦት ሰጥቷል።

    ክልሎች ደግሞ ወደእነርሱ ለሚመጡ ዜጎች ትራንስፖርትን እንዲያመቻቹ ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል አቶ መለስ።

    ከሳዑዲ ዓረቢያ የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ስራቸውን ትተው እንደመመለሳቸው መጠንም፥ አሁን ላይ እየተተገበረ ባለው የወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋልም ነው ያሉት።

    ቃል አቀባዩ ሪያድ ያወጣችው አዋጅ አሁን ላይ 26 ቀናት እንደሆኑት ጠቅሰው፥ አዋጁ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም አንስተዋል።

    የተመላሾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፥ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በየቀኑ በአማካይ 400 ሰዎች እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል።

    በስላባት ማናዬ
    አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎች በዘጠና ቀናት ውስጥ እንዲወጡ ካዘዛ በኋላ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳያጋጥማቸው የፌደራል ተቋማት እና የክልል መንግስታት በቅንጅት እንዲሰሩ መመሪያ ተላለፈ። የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ከመጋቢት 21 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በሀገሪቱ የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች ለቀው እንዲወጡ ያወጀው የ90 ቀናት የምህረት አዋጅ መተግበር ከጀመረ ዛሬ 26 ቀናት ሆኖታል። በዚህ የምህረት አዋጅ ውስጥም የኢፌዴሪ መንግስት ኢዮጵያውያን እንግልት ሳይደርስባቸው በ90 ቀናት ውስጥ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ፥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚከታተል ብሄራዊ ኮሚቴ አቋቁሟል። ዛሬም ይሄው ኮሚቴ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበዬሁ ሰብሳቢነት የእስካሁኑን እንቅስቃሴ ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በስብሰባው ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመጡ ዜጎችን ለመቀበል የፌደራል ተቋማትና ክልሎች በትብብር እንዲሰሩ ተወስኗል። ከዚህ ባለፈም ክልሎች የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን እንደገና እንዲቋቋሙ እና ከክልል ከተሞች እስከ ወረዳ ከተሞች ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ እንዲያደርጉ የቀረበው ሀሳብም ፀድቋል። በዚህም አዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ገቢወች እና ጉምሩክ፣ ፖሊስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ አጠናክረው በመቀጠል እንግልት እንዳይደርስባቸው መስራት እንደሚገባቸውም ኮሚቴው አጽንኦት ሰጥቷል። ክልሎች ደግሞ ወደእነርሱ ለሚመጡ ዜጎች ትራንስፖርትን እንዲያመቻቹ ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል አቶ መለስ። ከሳዑዲ ዓረቢያ የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ስራቸውን ትተው እንደመመለሳቸው መጠንም፥ አሁን ላይ እየተተገበረ ባለው የወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋልም ነው ያሉት። ቃል አቀባዩ ሪያድ ያወጣችው አዋጅ አሁን ላይ 26 ቀናት እንደሆኑት ጠቅሰው፥ አዋጁ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም አንስተዋል። የተመላሾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፥ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በየቀኑ በአማካይ 400 ሰዎች እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል። በስላባት ማናዬ
    WWW.FANABC.COM
    FBC - ከሳዑዲ ተመላሾች ችግር እንዳያጋጥማቸው የፌደራል ተቋማት እና የክልል መንግስታት በቅንጅት እንዲሰሩ መመሪያ ተላለፈ
    አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎች በዘጠና ቀናት ውስጥ እንዲወጡ ካዘዛ በኋላ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር እን...
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኩረጃን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የህብረተሰበ ክፍል የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አሳሰበ።

    በዛሬው እለት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከኤጀንሲዉ ጋር በመተባበር በፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ላይ የሚመክር ጉባኤ አካሂዷል።

    የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት፥ ትክክለኛ የምዘና ስርዓት በመተግበር የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ተቋሙ እየሰራ ነው።

    ሆኖም በተማሪዎች ዘንድ በስፋት የሚስተዋለውን የኩረጃ ተግባር ለማስቀረት፥ ወላጆች፣ መምህራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

    የጉባኤዉ ተሳታፊዎቸ በበኩላቸው ከታችኛው የክፍል ደረጃ ጀምሮ፥ ጥብቅ የፈተና ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኩረጃን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የህብረተሰበ ክፍል የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አሳሰበ። በዛሬው እለት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከኤጀንሲዉ ጋር በመተባበር በፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ላይ የሚመክር ጉባኤ አካሂዷል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት፥ ትክክለኛ የምዘና ስርዓት በመተግበር የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ተቋሙ እየሰራ ነው። ሆኖም በተማሪዎች ዘንድ በስፋት የሚስተዋለውን የኩረጃ ተግባር ለማስቀረት፥ ወላጆች፣ መምህራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል። የጉባኤዉ ተሳታፊዎቸ በበኩላቸው ከታችኛው የክፍል ደረጃ ጀምሮ፥ ጥብቅ የፈተና ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡
    WWW.FANABC.COM
    FBC - ኩረጃን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የህብረተሰበ ክፍል የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኩረጃን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የህብረተሰበ ክፍል የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አሳሰበ። በዛሬው እለት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮ...
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ሀይቅ ህገወጥ አሳ አስጋሪዎች ተገቢ ባልሆነ መረብ በማስገር በሀይቁ ዓሳ ሀብት ላይ ተጽእኖ እየፈጠሩ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎችና በሀይቁ ዙሪያ አገልግሎት በመስጠት እየተጠቀሙ የሚገኙ ግለሰቦች ተናገሩ።

    አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ አስተያየት ሰጪዎች እንደተናገሩት፥ ህገወጥ ዓሳ አስጋሪዎቹ ባልተገባ ሁኔታ ዓሳዎችን እንቁላል ሳይጥሉ ማስገራቸው የሀይቁ የዓሳ ሃብት እንዲቀንስ አድርጎታል።

    የማጥመድ ስራውም ማንኛውንም አሳ ለማጥመድ ከውጭ ሀገር በመጣ ማጥመጃ እያከናወኑ መሆኑም ጫና እየፈጠረ መሆኑ ተነግሯል።

    ይህ ደግሞ ትናንሽ አሳዎችን ከሀይቁ በማውጣት ተተኪ እንዳይኖር ያደርገዋል ነው የተባለው።

    የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በሀይቁ ላይ የተሰማሩ ህጋዊ እና ህገወጥ አስጋሪዎች፥ የሚያሰግሩበትን መንገድ እንዲያስተካክሉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

    ዓሳ የሚያሰግሩበት ማስገሪያ በተቀመጠለት ደረጃ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ ሲሆን፥ እርምጃ ለመውሰድም ታቅዷል።

    ሀይቁ የኦሮሚያ ክፍል አዋሳኝ በምዕራብ አርሲ ዞን ከ300 በላይ ወጣቶች በማህበር የስራ እድል ተፈጥሮላቸው፥ በቢሻን ጉራቻ ሐይቅ ዳርቻ ተሰማርተው እየሰሩ ሲሆን፥ በህገወጥ መንገድ አሳ የማስገሩም በእነሱ በኩልም እየተከናወነ ነው።

    የዞኑ የእንስሳትና አሳ ሃብት መምሪያ ሃላፊ ዶክተር አብዱላሂ ቤካ፥ የወጣቶቹን በህገወጥ መንገድ አሳ የማስገር ችግር አምነው፥ ከፌደራልና ከደቡብ ክልል የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እየወሰድን ነው ብለዋል።
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ሀይቅ ህገወጥ አሳ አስጋሪዎች ተገቢ ባልሆነ መረብ በማስገር በሀይቁ ዓሳ ሀብት ላይ ተጽእኖ እየፈጠሩ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎችና በሀይቁ ዙሪያ አገልግሎት በመስጠት እየተጠቀሙ የሚገኙ ግለሰቦች ተናገሩ። አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ አስተያየት ሰጪዎች እንደተናገሩት፥ ህገወጥ ዓሳ አስጋሪዎቹ ባልተገባ ሁኔታ ዓሳዎችን እንቁላል ሳይጥሉ ማስገራቸው የሀይቁ የዓሳ ሃብት እንዲቀንስ አድርጎታል። የማጥመድ ስራውም ማንኛውንም አሳ ለማጥመድ ከውጭ ሀገር በመጣ ማጥመጃ እያከናወኑ መሆኑም ጫና እየፈጠረ መሆኑ ተነግሯል። ይህ ደግሞ ትናንሽ አሳዎችን ከሀይቁ በማውጣት ተተኪ እንዳይኖር ያደርገዋል ነው የተባለው። የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በሀይቁ ላይ የተሰማሩ ህጋዊ እና ህገወጥ አስጋሪዎች፥ የሚያሰግሩበትን መንገድ እንዲያስተካክሉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። ዓሳ የሚያሰግሩበት ማስገሪያ በተቀመጠለት ደረጃ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ ሲሆን፥ እርምጃ ለመውሰድም ታቅዷል። ሀይቁ የኦሮሚያ ክፍል አዋሳኝ በምዕራብ አርሲ ዞን ከ300 በላይ ወጣቶች በማህበር የስራ እድል ተፈጥሮላቸው፥ በቢሻን ጉራቻ ሐይቅ ዳርቻ ተሰማርተው እየሰሩ ሲሆን፥ በህገወጥ መንገድ አሳ የማስገሩም በእነሱ በኩልም እየተከናወነ ነው። የዞኑ የእንስሳትና አሳ ሃብት መምሪያ ሃላፊ ዶክተር አብዱላሂ ቤካ፥ የወጣቶቹን በህገወጥ መንገድ አሳ የማስገር ችግር አምነው፥ ከፌደራልና ከደቡብ ክልል የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እየወሰድን ነው ብለዋል።
    WWW.FANABC.COM
    FBC - ህገወጥ አስጋሪዎች በሀዋሳ ሀይቅ የዓሳ ሀብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እየፈጠሩ ነው
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ሀይቅ ህገወጥ አሳ አስጋሪዎች ተገቢ ባልሆነ መረብ በማስገር በሀይቁ ዓሳ ሀብት ላይ ተጽእኖ እየፈጠሩ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎችና በሀይቁ ዙሪያ አገልግሎት በመስጠት እየተጠቀሙ የሚ...
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አስትሮ ፊዚስት ዶክተር ለገሰ ወትሮ በ67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

    ዶክተር ለገሰ በቀድሞ አጠራር በአሩሲ ክፍለ ሀገር ስሬ ወረዳ በ1942 ዓ.ም ነበር የተወለዱት፡፡

    የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩንቨርሲቲ ያገኙት ዶክተር ለገሰ፥ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በፊዚክስ ትምህርት አግኝተዋል፡፡

    ከሼፊልድ ዩናይት በድጋሚ በፊዚክስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፥ ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ከኮሎምቢያ ስቴት ዩንቨርሲቲ በአስትሮ ፊዚክስ አግኝተዋል፡፡

    በንፋስ ስልክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለአራት ዓመታት ያስተማሩት ዶክተር ለገሰ፥ ለ40 ዓመታት ያህል በመምህርነትና በተመራማሪነት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አገልግለዋል፡፡

    ዶክተር ለገሰ ወትሮ በአስትሮ ፊዚክስ ምርምር የሚታወቁ እና አዳዲስ ጽንሰ ሃሳቦችን ያበረከቱ ታላቅ ሰው ነበሩ ብሏል አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በመግለጫው፡፡

    በተወለዱ በ67 ዓመታቸው ያረፉት ዶ/ር ለገሰ የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

    የዶ/ር ለገሰ ወትሮ ስርዓተ ቀብር ነገ ሚያዚያ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት በጴጥሮስ መካነ መቃብር እንደሚፈፀም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
    አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አስትሮ ፊዚስት ዶክተር ለገሰ ወትሮ በ67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ዶክተር ለገሰ በቀድሞ አጠራር በአሩሲ ክፍለ ሀገር ስሬ ወረዳ በ1942 ዓ.ም ነበር የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩንቨርሲቲ ያገኙት ዶክተር ለገሰ፥ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በፊዚክስ ትምህርት አግኝተዋል፡፡ ከሼፊልድ ዩናይት በድጋሚ በፊዚክስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፥ ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ከኮሎምቢያ ስቴት ዩንቨርሲቲ በአስትሮ ፊዚክስ አግኝተዋል፡፡ በንፋስ ስልክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለአራት ዓመታት ያስተማሩት ዶክተር ለገሰ፥ ለ40 ዓመታት ያህል በመምህርነትና በተመራማሪነት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አገልግለዋል፡፡ ዶክተር ለገሰ ወትሮ በአስትሮ ፊዚክስ ምርምር የሚታወቁ እና አዳዲስ ጽንሰ ሃሳቦችን ያበረከቱ ታላቅ ሰው ነበሩ ብሏል አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በመግለጫው፡፡ በተወለዱ በ67 ዓመታቸው ያረፉት ዶ/ር ለገሰ የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡ የዶ/ር ለገሰ ወትሮ ስርዓተ ቀብር ነገ ሚያዚያ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት በጴጥሮስ መካነ መቃብር እንደሚፈፀም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
    WWW.FANABC.COM
    FBC - ኢትዮጵያዊው አስትሮ ፊዚስት ዶክተር ለገሰ ወትሮ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
    አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አስትሮ ፊዚስት ዶክተር ለገሰ ወትሮ በ67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ዶክተር ለገሰ በቀድሞ አጠራር በአሩሲ ክፍለ ሀገር ስሬ ወረዳ በ1942 ዓ.ም ነበር የተወለ...
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሩዋንዳ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በምስራቃዊ ግዛት በሩዋማጋና የሚገኘውን ኢንቴቤ የተቀናጀ ሞዴል መንደር ጎብኝተዋል።

    ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ሞዴል መንደሩ በሀገሪቱ በገጠራማ ስፍራ የሚገኙ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች በአንድ ላይ በማስፈር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል።

    እንደ አውሮፓውያኑ በ2008 የተጀመረው የኢንቴቤ የተቀናጀ ሞዴል መንደር ልማት ከ2009 ጀምሮ ነዋሪዎችን ማስተናገድ ጀምሯል፤ በአሁኑ ወቅትም ከ204 በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦችን ይዟል።


    መንደሮቹ የተለያዩ ማህበረሰቦች በግብርና እና ሌሎች መስኮች በመስራት በጋራ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
    በእነዚህ መንደሮች የሚኖሩ ሰዎች የትምህርት፣ የውሃ እና ፅዳጅ፣ የጤና፣ የኤሌክትሪክ እና ሌሎች አገልግሎቶችን በጋራ ያገኛሉ።
    የሀገሪቱ መንግስት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 70 በመቶ የገጠሩን ህዝብ በእነዚህ ሞዴል መንደሮች ለማስፈር አቅዷል፡፡
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሩዋንዳ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በምስራቃዊ ግዛት በሩዋማጋና የሚገኘውን ኢንቴቤ የተቀናጀ ሞዴል መንደር ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ሞዴል መንደሩ በሀገሪቱ በገጠራማ ስፍራ የሚገኙ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች በአንድ ላይ በማስፈር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2008 የተጀመረው የኢንቴቤ የተቀናጀ ሞዴል መንደር ልማት ከ2009 ጀምሮ ነዋሪዎችን ማስተናገድ ጀምሯል፤ በአሁኑ ወቅትም ከ204 በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦችን ይዟል። መንደሮቹ የተለያዩ ማህበረሰቦች በግብርና እና ሌሎች መስኮች በመስራት በጋራ ተጠቃሚ ይሆናሉ። በእነዚህ መንደሮች የሚኖሩ ሰዎች የትምህርት፣ የውሃ እና ፅዳጅ፣ የጤና፣ የኤሌክትሪክ እና ሌሎች አገልግሎቶችን በጋራ ያገኛሉ። የሀገሪቱ መንግስት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 70 በመቶ የገጠሩን ህዝብ በእነዚህ ሞዴል መንደሮች ለማስፈር አቅዷል፡፡
    WWW.FANABC.COM
    FBC - ጠ/ሚ ኃይለማርያም የኢንቴቤ የተቀናጀ ሞዴል መንደርን ጎበኙ
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሩዋንዳ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በምስራቃዊ ግዛት በሩዋማጋና የሚገኘውን ኢንቴቤ የተቀናጀ ሞዴል መንደር ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው...
    0 Comments 0 Shares
  • #Ethiopia ገሊላ የፈጠራ ስራዋን የራሱ አድርጎ ባቀረበው መምህር እርር ድብን ብያለሁ አለች | Ethiopian women disenchants over art plagiarism
    -
    ገሊላ መስፍን በኒው ዮርክ የስዕል ጥበብ (አርት) ተማሪ ስትሆን፣ የቀድሞዋን ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማን እንደጥንታውያን የግብጽ ነገስታት አስመስላ የሳለችውን የፈጠራ ስራዋን የራሱ አድርጎ በማቅረብ ወደ12000 ዶላር ባሰባሰበው መምህር ላይ ሰሞኑን ከፍተኛ ተቃውሞዋን ስትገልጽ ሰንብታለች...
    Like
    3
    0 Comments 0 Shares
  • #Ethiopia ገሊላ የፈጠራ ስራዋን የራሱ አድርጎ ባቀረበው መምህር እርር ድብን ብያለሁ አለች | Ethiopian women disenchants over art plagiarism
    -
    ገሊላ መስፍን በኒው ዮርክ የስዕል ጥበብ (አርት) ተማሪ ስትሆን፣ የቀድሞዋን ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማን እንደጥንታውያን የግብጽ ነገስታት አስመስላ የሳለችውን የፈጠራ ስራዋን የራሱ አድርጎ በማቅረብ ወደ12000 ዶላር ባሰባሰበው መምህር ላይ ሰሞኑን ከፍተኛ ተቃውሞዋን ስትገልጽ ሰንብታለች...
    #Ethiopia ገሊላ የፈጠራ ስራዋን የራሱ አድርጎ ባቀረበው መምህር እርር ድብን ብያለሁ አለች | Ethiopian women disenchants over art plagiarism - ገሊላ መስፍን በኒው ዮርክ የስዕል ጥበብ (አርት) ተማሪ ስትሆን፣ የቀድሞዋን ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማን እንደጥንታውያን የግብጽ ነገስታት አስመስላ የሳለችውን የፈጠራ ስራዋን የራሱ አድርጎ በማቅረብ ወደ12000 ዶላር ባሰባሰበው መምህር ላይ ሰሞኑን ከፍተኛ ተቃውሞዋን ስትገልጽ ሰንብታለች...
    0 Comments 1 Shares