አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ድብርት ከሚያደርሰው ጉዳት አንፃር ብዙ ያልተነገረለት የአዕምሮ ጠንቅ ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በአለም አቀፍ ደረጃ 350 ሚሊየን የሚደርሱ በተለያዩ የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች በድብርት ተጠቅተዋል።
እነዚህ ሰዎች በአፋጣኝ የህክምና እርዳታ ካልተደረገላቸውም ራሳቸውን ወደማጥፋት ይገባሉ ነው የሚለው ድርጅቱ።
በየቀኑ የተለያዩ ችግሮች ሲገጥሙን የድብርት ስሜት ማስተናገዳችን የተለመደ ነው።
ይሁን እንጂ ይህ መጥፎ ስሜት እየተደጋገመ ሲመጣ በህይወታችን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖውን ያሳርፋል።
ድብርት ከጊዜያዊ መጥፎ ስሜት ከፍ ያለ የአዕምሮ መቃወስ ችግር መሆኑን ጥናቶች ያመለክታሉ።
የዕለት ከዕለት ውሏችን ከማበላሸት ባሻገር ግላዊ፣ ማህበራዊ እና ሙያዊ ህይወታችን ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው።
ምንም እንኳን በአለማችን ለድብርት ተጋላጭ የሆኑት 350 ሚሊየን ሰዎች አብዛኞቹ በህክምና መዳን ቢችሉም ከመረጃ እና የተማረ የህክምና ባለሙያ እጥረት፣ በትክክለኛ መንገድ ለድብርት መጋለጥን ካለመለየት እና በማህበረሰቡ ዘንድ ከአዕምሮ ችግር ጋር ለተገናኙ ችግሮች የሚሰጠው የተሳሳተ አመለካከት የተነሳ ከ175 ሚሊየን በታች የሚሆኑ ለችግሩ የተዳረጉ ሰዎች ናቸው የህክምና አገልግሎት የሚያገኙት።
የድብርት ችግርን ለመቅረፍ የመጀመሪያው ነጥብ ምልክቶቹን ማወቅ እና ግንዛቤ ማግኘት ነው።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 10 ነጥቦችም ቸል ልንላቸው የማይገቡ ለድብርት መጋለጥን የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው ተብሏል።
1. ዝቅተኛ በራስ የመተማመን መንፈስ፣ የጥፋተኝነት ስሜት እና ተስፋ ማጣት
በራስ የመተማመን መንፈሳቸው የወረደ፣ ተፈጥሮ በቸረቻቸው ነገሮች የማይረኩ፣ ላለፈ ጥፋታቸው ራሳቸውን አብዝተው የሚወቅሱ እና ለሌሎች ሰዎችም ይቅርታ ማድረግም የማይወዱ ሰዎች ለድብርት የተጋለጡ ሊሆኑ እንደሚችል ይነገራል።
ራስን መጥላት፣ ከፍተኛ የጥፋተኝነት ስሜት እና ሀፍረት የድብርት ዋነኛ ምልክቶች ናቸው ተብሏል።
2. ከፍተኛ የድካም ስሜት
ለድብርት በተጋለጡ ሰዎች ዘንድ በስፋት ከሚታዩ የህመም ምልክቶች ውስጥ ከፍተኛ ድካም ተጠቃሽ ነው ይላል እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2004 በአሜሪካ ሳይካትሪ ጆርናል ላይ የወጣ ጥናት።
ድብርት በአዕምሮ ውስጥ የሚመረተውንና የደስታ ስሜት የሚፈጥረውን ሴሮቶኒን ሆርሞን መመረት ከመቀነስ ባሻገር ሀይል እንዲመረት የሚያደርገውን ኢፒነፍሪን በፍጥነት እንዳይመረት ምክንያት ይሆናል።
ይህም አዕምሯችን በተገቢው መንገድ ስራውን እንዳያከናውን በማድረግ ለድካም ስሜት ይዳርጋል።
ለድብርት የተጋለጡ ሰዎች ምንም እንኳን በቂ እንቅልፍ ወስደው ምንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባያደርጉም ሰውነታቸው ከፍተኛ የድካም ስሜት ይሰማዋል፤ ይህም አዕምሯቸው እንዲዝል ምክንያት ይሆናል።
3. የእንቅልፍ እጦት
እንደ አውሮፓውያኑ በ2009 በአለም አቀፉ የሳይካትሪ ጆርናል ላይ የታተመ የጥናት ውጤት፥ ከ531 የድብርት ተጠቂዎች 97 በመቶው ለእንቅልፍ እጦት የተዳረጉ ናቸው ይላል።
ከጥናቱ ተሳታፊዎች 59 በመቶ የሚሆኑት የእንቅልፍ እጦት የስራቸውን ጥራት ክፉኛ እንደጎዳው ተናግረዋል።
40 በመቶው ደግሞ ቀን ላይ ለጥቂት ደቂቃዎች እንደሚተኙ (ናፕ እንደሚወስዱ) እና 34 በመቶ የጥናቱ ተሳታፊዎች የእንቅልፍ እጦት በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳቸው መሆኑን ገልፀዋል።
4. ቁጣ እና ግልፍተኝነት
ቁጣ ከድብርት የመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶች አንዱ ነው።
ከቁጣ ባሻገር ግልፍተኝነት እና አትንኩኝ ባይነት ሌላኛው ለድብርት መጋለጥን የሚያሳይ ምልክት መሆኑ ነው የሚነገረው።
ለድብርት የተጋለጡ ሰዎች በጣም ቀላል በሆነ ነገር ይበሳጫሉ፤ በቤተሰቦቻቸውም ሆነ ጓደኞቻቸው ፊት ለፀብ ይጋበዛሉ።
5. ፍርሃት
ከዚህ ቀደም የተከሰተ እና ገና ይሆናል ተብሎ ለሚጠበቅ ነገር የበዛ የፍርሃት ስሜት የሚነበብቻቸው ሰዎች ምናልባትም ለድብርት ተጋልጠው ሊሆን ስለሚችል ሀኪሞችን ቢያማክሩ ጥሩ ነው።
ቀላል ግላዊ ችግሮች ለድብርት የተጋለጡ ሰዎችን በአንድ ጊዜ አለም ጨለማ መስላ እንድትታያቸው ሊያደርጋቸው ይችላል።
በሚያስተናግዱት የፍርሃት ስሜት ምክንያትም በላብ የሚዘፈቁ ሲሆን፥ የልብ ምታቸውም በጣም ይፈጥናል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2000 በኮምፐርሄንሲቭ ፓይካትሪ ላይ የወጣ ጥናት፥ ከ255 የድብርት ተጠቂዎች 50 ነጥብ 6 በመቶው ለከፍተኛ ፍርሃት መጋለጣቸውን ያሳያል።
ከጥናቱ ተሳታፊዎች 27 በመቶው ለማህበራዊ አጋጣሚዎች ፍርሃት እና 14 በመቶው ህዝብ በተሰበሰበባቸውና መሰል ቦታዎች መገኘት ፍርሃት ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
6. በትኩረት የማሰብ እና የማስታወስ ችሎታ መውረድ
በአስተውሎት የማሰብ ችግር ለድብርት በተጋለጡ ሰዎች በስፋት የሚታይ መሆኑን እንደ አውሮፓውያኑ በ2004 በአሜሪካ ሳይካትሪ ጆርናል ላይ የወጣ ጥናት አመላክቷል።
የድብርት ተጠቂዎች የቅርብ ጊዜ ሁነቶችን የማስታወስ ችሎታቸው አነስተኛ መሆኑንም ነው ጥናቱ የጠቆመው።
7. ስሜትን የመቆጣጠር ችግር
ሰዎች ከቀደመ ባህሪያቸው በተቃራኒው ከሌሎች ሰዎች ጋር መግባባት ከተቸገሩ እና ህይወትን በአንድ ጫፍ ብቻ የሚመለከቱ ከሆነ ምናልባትም ለድብርት ተጋልጠው ሊሆን ይችላል ይላል በ2015 በጀነራል ሳይካትሪ ላይ የታተመ ጥናት።
ከመጥፎ ስሜት ለመውጣት አልኮል አብዝተው የሚጠጡ፣ በዝርፊያ እና በአደገኛ ወሲባዊ ጥቃቶች ላይ የሚሳተፉ ሰዎችም ድብርት ውስጥ ገብተው ይሆናል ይላል ጥናቱ።
እነዚህ አዲስ መጥፎ ልማዶች ጊዜያዊ እረፍት ከመስጠት ይልቅ የድብርት ችግራቸውን ያባብሱታል።
8. ደስታን በሚፈጥሩ ነገሮች ለመሳተፍ ፍላጎት አለማሳየት
በማንኛውም ማህበራዊ እንቅስቃሴ እና መስተጋብር ለመሳተፍ እና ደስታን ለመፍጠር ፍላጎት ማጣት በህክምና አጠራር አንሄዶኒያ ይሰኛል።
አንሄዶኒያ የድብርት ቅድመ ምልክት መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ።
ለድብርት የተጋለጡ ሰዎች ከማንኛውም ተግባር ደስታን ማግኘት እንደሚቻል ሰለማያምኑ ራሳቸውን የማግለል እና አብዛኛውን ጊዜያቸውን ያለምንም ስራ በዝምታ ማሳለፍን ይመርጣሉ።
9. የክብደት ለውጥ
ድንገተኛ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ሌላኛው ለድብርት መጋለጥ ምልክት ነው።
የምግብ ፍላጎታቸው ከመቀነሱም በተጨማሪ የምመገበው ምግብ አይስማማኝም የሚል አስተሳሰብ ስላላቸውም በአጭር ጊዜ ጤናማ ባልሆነ መንገድ ክብደታቸው ይቀንሳል።
በ2002 በኒዩሮሳይኮ ፋርማኮሎጂ እና ባዮሎጂካል ሳይካትሪ ጆርናል ላይ የወጣ ጥናት የምግብ ፍላጎት ከድብርት ተጠቂዎች ጋር ዝምድና እንዳለው አመላክቷል።
ከዚህ በተቃራኒ በብዛት ባይከሰትም ለድብርት የተጋለጡ አንዳንድ ሰዎች ከመጥፎ ስሜታቸው ለመውጣት አብዝተው ስለሚመገቡ ከልክ ላለፈ ውፍረት ሊጋለጡ ይችላሉ የሚሉም አሉ።
በጣም ከባድ ድብርት ያጠቃቸው ሰዎች አጠቃላይ ክብደት በሂደት እየጨመረ እንደሚሄድ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2009 በአሜሪካ የማህበራዊ ጤና ጆርናል ላይ የወጣ ጥናት አመላክቷል።
በአጠቃላይ ድንገተኛ የክብደት መቀነስም ሆነ መጨመር የድብርት ምልክት ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
10. ራስን የማጥፋት ሀሳብ
ለድብርት የተጋለጡ ሰዎች ራስን የማጥፋት ሙከራ በተደጋጋሚ የሚታይ ነው።
ሰዎች ራሳቸውን እንዲያጠፉ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ለከፍተኛ ድብርት መጋለጥ በዋነኛ ምክንያትነት ይጠቀሳል።
ከዘወትራዊው ቀላል የሚባል መጥፎ ስሜት ወጣ ያለ እና በህይወት የመኖር ጣዕምን የሚያሳጣ ጭንቀት፣ ውጥረት፣ ፍርሃት እና በራስ የመተማመን ስሜት መመናመን ለድብርት መጋለጥን ሊያመላክት ስለሚችል ችግሩ ስር ሳይሰድ ወደ ህክምና ተቋማት ማምራት አልያም የስነ ልቦና ባለሙያዎችን ማማከር ተገቢ ነው።
ምንጭ፦ www.top10homeremedies.com