• “የአሻንቲ ህዝብ ለቡድኑ ጠንካራ ፀሎት አድርጓል ከአላህ ጋር ኢትዮጵያን ከአምስት ጎል ባላነሰ ውጤት እናሸንፋለን” – ሼህ ሀሩን አብዱል ሙሚን

    የጋናዋ አሻንቲ ግዛት የእስልምና መሪ የሆኑት ሼህ ሀሩን አብዱል ሙሚን የአካባቢው የእስልምና ተከታዮች ለብሔራዊ ብድኑ ፀሎት እንዳደረጉና በፈጣሪ እርዳታ ሀገራቸው ጨዋታውን ከአምስት ጎል ባላነሰ ውጤት እንደምታሸንፍ ተናግረዋል። ሼሁ ከፀሎት በኋላ በኩማሲ መስኪድ ለተገኙት የቡድኑ ተጫዋቾች ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ለብሔራዊ ቡድኑ ተገቢው ፀሎት መደረጉንና ከፈጣሪ ጋር ሀገራቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ተሳትፎዋን በድል እንደምትጀምር ያላቸውን በራስ መተማመን አጉልተው አሳይተዋል። በዚህ በኩማሲ መስኪድ በተደረገው የፀሎት ስነስርአት ላይ ሁለቱ ወንድማማቾች አንድሬ እና ጆርዳን አዩ፣ ረሺድ ሱማይላና አብዱል መጂድ ዋሪስ አይነት የቡድኑ ኮከቦች ተካፋይ ነበሩ። ከቡድኑ ተጫዋቾች በተጨማሪ የቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ኢብራሂም አንያራስ ታንኮ እና የህዝብ ግንኙነቱ ኢብራሂም ሳኔ ዳራ በፀሎቱ ተካፍለዋል። ከዛሬ ምሽቱ ትንቅንቅ በፊት ብዙዎች የማሸነፉን ግምት ለጥቋቁሮቹ ኮከቦች የሰጡ ቢሆንም ዋልያዎቹ በተሰጣቸው ያነሰ ግምት እንደማይደናገጡና በጨዋታው ላይ ውጤት ለማግኘት የተቻላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ እየገለፁ ይገኛል። የቡድኑ አሰልጣኝ አሸናፊ ከበደ ከአንድ የጋና ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ “እናውቃለን ጋና ጠንካራ ቡድን ነው። ነገርግን እኛ እነሱን ስንገጥም የምናስደምምበት የራሳችን እቅድ አለን።” ሲሉ ተጋጣሚያቸው ጠንካራ ቢሆንም ለጨዋታው ዝግጁ እንደሆኑ አውስተዋል። ጋና ከ 1963 የአፍሪካ ዋንጫ ጀምሮ ዋሊያዎቹን ለሶስት ጊዜያት የገጠመች ሲሆን በሁለቱ ስታሸንፍ በአንዱ ሽንፈት ቀምሳለች። የሁለቱ ቡድኖች የመጨረሻ የቅርብ ጊዜ ግንኙነት በ 2014 ጋና 1-0 ያሸነፈችበት የቻን ውድድር መሆኑ ይታወሳል።
    “የአሻንቲ ህዝብ ለቡድኑ ጠንካራ ፀሎት አድርጓል ከአላህ ጋር ኢትዮጵያን ከአምስት ጎል ባላነሰ ውጤት እናሸንፋለን” – ሼህ ሀሩን አብዱል ሙሚን የጋናዋ አሻንቲ ግዛት የእስልምና መሪ የሆኑት ሼህ ሀሩን አብዱል ሙሚን የአካባቢው የእስልምና ተከታዮች ለብሔራዊ ብድኑ ፀሎት እንዳደረጉና በፈጣሪ እርዳታ ሀገራቸው ጨዋታውን ከአምስት ጎል ባላነሰ ውጤት እንደምታሸንፍ ተናግረዋል። ሼሁ ከፀሎት በኋላ በኩማሲ መስኪድ ለተገኙት የቡድኑ ተጫዋቾች ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ለብሔራዊ ቡድኑ ተገቢው ፀሎት መደረጉንና ከፈጣሪ ጋር ሀገራቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ተሳትፎዋን በድል እንደምትጀምር ያላቸውን በራስ መተማመን አጉልተው አሳይተዋል። በዚህ በኩማሲ መስኪድ በተደረገው የፀሎት ስነስርአት ላይ ሁለቱ ወንድማማቾች አንድሬ እና ጆርዳን አዩ፣ ረሺድ ሱማይላና አብዱል መጂድ ዋሪስ አይነት የቡድኑ ኮከቦች ተካፋይ ነበሩ። ከቡድኑ ተጫዋቾች በተጨማሪ የቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ኢብራሂም አንያራስ ታንኮ እና የህዝብ ግንኙነቱ ኢብራሂም ሳኔ ዳራ በፀሎቱ ተካፍለዋል። ከዛሬ ምሽቱ ትንቅንቅ በፊት ብዙዎች የማሸነፉን ግምት ለጥቋቁሮቹ ኮከቦች የሰጡ ቢሆንም ዋልያዎቹ በተሰጣቸው ያነሰ ግምት እንደማይደናገጡና በጨዋታው ላይ ውጤት ለማግኘት የተቻላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ እየገለፁ ይገኛል። የቡድኑ አሰልጣኝ አሸናፊ ከበደ ከአንድ የጋና ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ “እናውቃለን ጋና ጠንካራ ቡድን ነው። ነገርግን እኛ እነሱን ስንገጥም የምናስደምምበት የራሳችን እቅድ አለን።” ሲሉ ተጋጣሚያቸው ጠንካራ ቢሆንም ለጨዋታው ዝግጁ እንደሆኑ አውስተዋል። ጋና ከ 1963 የአፍሪካ ዋንጫ ጀምሮ ዋሊያዎቹን ለሶስት ጊዜያት የገጠመች ሲሆን በሁለቱ ስታሸንፍ በአንዱ ሽንፈት ቀምሳለች። የሁለቱ ቡድኖች የመጨረሻ የቅርብ ጊዜ ግንኙነት በ 2014 ጋና 1-0 ያሸነፈችበት የቻን ውድድር መሆኑ ይታወሳል።
    0 Comments 0 Shares
  • የቀድሞው የኤሲ ሚላን ፣ ሮማ ፣ ጁቬንቱስና ሪያልማድሪድ አሰልጣኝ ውጤታማው ፋቢዮ ካፔሎ ወደክለብ ማሰልጠን ስራቸው በመመለስ የቻይናው ክለብ ጂያንሱ ሰኒንግ አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡ በ2007 ሪያል ማድሪድን ከለቀቁ በኋላ ከክለብ አሰልጣኝነት ርቀው የቆዩት ካፔሎ በበሔራዊ ቡድን ደረጃ የእንግሊዝና የሩሲያን ብሔራዊ ቡድን ሲያሰለጥኑ ቆይተዋል፡፡ በ 2015 ከሩሲያ ኃላፊነታቸው የለቀቁት አሰልጣኙ እስከአሁን ስራ ፈትተው የሰነበቱ ቢሆንም አሁን ግን በረብጣ ሚልዮን ዶላሮች የበለፀገው የቻይና ሱፐር ሊግ ማረፊያቸው ሆኗል፡፡ የጣልያናዊውን ግልጋሎት ለማግኘት የተስማማው ሰኒንግ በ2016 የውድድር ዘመን በሊጉ ሁለተኛ ሆኖ መጨረስ ችሎ የነበረ ቢሆንም በዘንድሮው የውድድር ዘመን ግን በወራጅ ቀጠናው ውስጥ እየዳከረ ይገኛል፡፡ የስምምነት ስርአቱን ተከትሎ የክለቡ ይፋዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን”አሰልጣኝ ካፔሎን ለማስፈረም የተደረሰው ውሳኔ የክለቡ የለውጥና የዕድገት ፍላጎት እንቅስቃሴ አካል ነው” የሚል ቃል ይገኝበታል፡፡ በተጨማሪም”ክለቡን ከመምራት በተጓዳኝ በክለብ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ዘመናዊ አሰራርና የተሻሉ ሃሳቦችን ማስረጽ ሌላኛው ኃላፊነቱ ነው ፤ በዚህም የኛ ክለብ ላይ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው የቻይና እግር ኳስ ላይ ለውጥ መፍጠር እንችላለን” ይላል፡፡ ጣልያናዊው ቆፍጣና በልዕልና ዘመናቸው አምስት የሴሪ አ ፣ ሁለት የላሊጋና አንድ የሻምፒዮንስ ሊግ ክብርን በማግኘት ደማቅ ታሪክን ፅፈዋል
    የቀድሞው የኤሲ ሚላን ፣ ሮማ ፣ ጁቬንቱስና ሪያልማድሪድ አሰልጣኝ ውጤታማው ፋቢዮ ካፔሎ ወደክለብ ማሰልጠን ስራቸው በመመለስ የቻይናው ክለብ ጂያንሱ ሰኒንግ አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡ በ2007 ሪያል ማድሪድን ከለቀቁ በኋላ ከክለብ አሰልጣኝነት ርቀው የቆዩት ካፔሎ በበሔራዊ ቡድን ደረጃ የእንግሊዝና የሩሲያን ብሔራዊ ቡድን ሲያሰለጥኑ ቆይተዋል፡፡ በ 2015 ከሩሲያ ኃላፊነታቸው የለቀቁት አሰልጣኙ እስከአሁን ስራ ፈትተው የሰነበቱ ቢሆንም አሁን ግን በረብጣ ሚልዮን ዶላሮች የበለፀገው የቻይና ሱፐር ሊግ ማረፊያቸው ሆኗል፡፡ የጣልያናዊውን ግልጋሎት ለማግኘት የተስማማው ሰኒንግ በ2016 የውድድር ዘመን በሊጉ ሁለተኛ ሆኖ መጨረስ ችሎ የነበረ ቢሆንም በዘንድሮው የውድድር ዘመን ግን በወራጅ ቀጠናው ውስጥ እየዳከረ ይገኛል፡፡ የስምምነት ስርአቱን ተከትሎ የክለቡ ይፋዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን”አሰልጣኝ ካፔሎን ለማስፈረም የተደረሰው ውሳኔ የክለቡ የለውጥና የዕድገት ፍላጎት እንቅስቃሴ አካል ነው” የሚል ቃል ይገኝበታል፡፡ በተጨማሪም”ክለቡን ከመምራት በተጓዳኝ በክለብ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ዘመናዊ አሰራርና የተሻሉ ሃሳቦችን ማስረጽ ሌላኛው ኃላፊነቱ ነው ፤ በዚህም የኛ ክለብ ላይ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው የቻይና እግር ኳስ ላይ ለውጥ መፍጠር እንችላለን” ይላል፡፡ ጣልያናዊው ቆፍጣና በልዕልና ዘመናቸው አምስት የሴሪ አ ፣ ሁለት የላሊጋና አንድ የሻምፒዮንስ ሊግ ክብርን በማግኘት ደማቅ ታሪክን ፅፈዋል
    0 Comments 0 Shares
  • የአርሰናሉ ተከላካይ ሌዮሬንት ኮስሌኒይ ወደ ማርሴ አይዘዋወርም::

    ሌዮሬንት ኮስሌኒይ በአርሰናል ውስጥ መቆየቱ ጥሩ ስሜት እንዲሰማው እንዳደረገው ተቀብሏል ነገር ግን የልጅነት ክለቡ ማርሴ የእንውሰድህ ጥያቄ ቢያቀርብለት አይሆንም ለማለት እንደሚቸገርና ምክንያታዊ እንደሆነ ተናግሯል ጊዜው አልታወቀም እንጂ ሊሆንም እንደሚችልም ጭምር:: ይህ ፈረንሳዊ በ 2010 ባልተገለፀ የዝውውር ሂሳብ ከሎሬንት መድፈኞቹን ከተቀላቀለ ጀምሮ ለቡድኑ የኃላ መስመር የልብ ትርታ ሆኗል:: አሁን ላይ በአሜሪካው ቢሊየነር የበጀት ድጋፍ ስር የሚገኘው ክለብ ማርሴ ያለውን የቡድን ጥልቀት በጥንቃቄ በመገምገም በቀጣዩ የውድድር ዘመን ለሚገጥመው ፋክክር ከመሪዎቹ ተርታ ለመሰለፍ ይህንን የ 31 ዓመት ፈረንሳዊ ዒላማ አድርጎ ብቅ ብሏል:: ኮስሌኒይ ግን ወደ ቬሌድሮም ስታዲየም ያመራል የሚባለውን ተቃውማል:: ኮስሌኒይ ለቴሌፋት እንደተናገረው ” አሁንም ድረስ ከአርሰናል ጋር ውል አለኝ እንዲያውም ባለፈው ሕዳር ወር እስከ 2020 የሚያቆየኝን ፊርማ አስቀምጫለሁ:: ” በአርሰናል ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው:: ይሄ ሁልግዜም የምናገረው ነው በልጅነቴ የማርሴ ደጋፊ ነበርኩ:: እንደማርሴ ባለ ታሪካዊ ክለብ መፈለግ ጥሩ ነው:: ነገር ግን እኔ ፊርማዬን አኖራለሁ??? አላውቅም!!! በአርሰናል በጣም ደስተኛ ነኝ ” ሲል ተናግሯል:: የቡድን አጋሩ ኦሊቪዬ ዢሩ እና በቶተነሀም የተገፋው ሙሳ ሲሶኮ በቅርብ ቀናት በዝውውር ገበያው ስማቸው ከፈረንሳዩ ክለብ ጋር የተያያዘ ተጫዋቾች ናቸው::
    የአርሰናሉ ተከላካይ ሌዮሬንት ኮስሌኒይ ወደ ማርሴ አይዘዋወርም:: ሌዮሬንት ኮስሌኒይ በአርሰናል ውስጥ መቆየቱ ጥሩ ስሜት እንዲሰማው እንዳደረገው ተቀብሏል ነገር ግን የልጅነት ክለቡ ማርሴ የእንውሰድህ ጥያቄ ቢያቀርብለት አይሆንም ለማለት እንደሚቸገርና ምክንያታዊ እንደሆነ ተናግሯል ጊዜው አልታወቀም እንጂ ሊሆንም እንደሚችልም ጭምር:: ይህ ፈረንሳዊ በ 2010 ባልተገለፀ የዝውውር ሂሳብ ከሎሬንት መድፈኞቹን ከተቀላቀለ ጀምሮ ለቡድኑ የኃላ መስመር የልብ ትርታ ሆኗል:: አሁን ላይ በአሜሪካው ቢሊየነር የበጀት ድጋፍ ስር የሚገኘው ክለብ ማርሴ ያለውን የቡድን ጥልቀት በጥንቃቄ በመገምገም በቀጣዩ የውድድር ዘመን ለሚገጥመው ፋክክር ከመሪዎቹ ተርታ ለመሰለፍ ይህንን የ 31 ዓመት ፈረንሳዊ ዒላማ አድርጎ ብቅ ብሏል:: ኮስሌኒይ ግን ወደ ቬሌድሮም ስታዲየም ያመራል የሚባለውን ተቃውማል:: ኮስሌኒይ ለቴሌፋት እንደተናገረው ” አሁንም ድረስ ከአርሰናል ጋር ውል አለኝ እንዲያውም ባለፈው ሕዳር ወር እስከ 2020 የሚያቆየኝን ፊርማ አስቀምጫለሁ:: ” በአርሰናል ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው:: ይሄ ሁልግዜም የምናገረው ነው በልጅነቴ የማርሴ ደጋፊ ነበርኩ:: እንደማርሴ ባለ ታሪካዊ ክለብ መፈለግ ጥሩ ነው:: ነገር ግን እኔ ፊርማዬን አኖራለሁ??? አላውቅም!!! በአርሰናል በጣም ደስተኛ ነኝ ” ሲል ተናግሯል:: የቡድን አጋሩ ኦሊቪዬ ዢሩ እና በቶተነሀም የተገፋው ሙሳ ሲሶኮ በቅርብ ቀናት በዝውውር ገበያው ስማቸው ከፈረንሳዩ ክለብ ጋር የተያያዘ ተጫዋቾች ናቸው::
    0 Comments 0 Shares
  • ኢማኑኤል አዴባዮር በህይወቱ ፀፀት የሆነበትን ውሳኔ ይፋ አደረገ

    ሪያል ማድሪድን ጨምሮ በአርሰናል ፣ በማንችስተር ሲቲና ቶተንሐም ቆይታ ማድረግ የቻለው ቶጎአዊ የፊት አጥቂ ኢማኑኤል አዴባዮር በእግር ኳስ ህይወቱ ከሚያስፀፅቱት ውሳኔዎች ዋነኛው በ2016 ለክሪስታል ፓላስ ለመጫወት መስማማቱ መሆኑን ገልጿል፡፡ . ተጫዋቹ በወቅቱ ክለብ አልባ የነበረ በመሆኑ የቀረበለትን የፈርምልን ጥያቄ ሳያቅማማ የተቀበለ ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ 15 ጨዋታዎች አንድ ጎል ብቻ ካስቆጠረ በኋላ ወደተጠባባቂ ወንበር ወርዶ ውሉን ለመጨረስ ተገዷል፡፡. ተጫዋቹ ለ ለኪፕ እንደተናገረው “በእንግሊዝ ከታላላቅ ክለቦች ጋር መልካም ጊዜያትን አሳልፌአለሁ ፤ እኔና ቤተሰቤ ደስተኛ ነበርን፡፡ የሰራሁት ብቸኛ ስህተት ለፓላስ ለመጫወት መስማማቴ ነው፡፡ ይህን ያደረኩት ለኔ ሰዎች ስል ነው፡፡ ሁሌም ‘ወደሜዳ ተመለስ እንጂ!’ ይሉኝ ነበር፡፡ የጨዋታ ዘመኔ መጥፎ ውሳኔ ነበር”ብሏል፡፡ ተጫዋቹ ወደቱርክ በማቅናት ለባሳክሺር ከፈረመ በኋላ ወደቀድሞ ብቃቱ የተመለሰ ሲሆን ክለቡን ለቱርክ ዋንጫ ፍፃሜ ማድረስ ችሏል፡፡ አዴባዮር ጨምሮም የቱርክ ቆይታው እንደተመቸውና ወደሌላ ክለብ የመዘዋወር ዕቅድ እንደሌለው አሳውቋል፡፡
    ኢማኑኤል አዴባዮር በህይወቱ ፀፀት የሆነበትን ውሳኔ ይፋ አደረገ ሪያል ማድሪድን ጨምሮ በአርሰናል ፣ በማንችስተር ሲቲና ቶተንሐም ቆይታ ማድረግ የቻለው ቶጎአዊ የፊት አጥቂ ኢማኑኤል አዴባዮር በእግር ኳስ ህይወቱ ከሚያስፀፅቱት ውሳኔዎች ዋነኛው በ2016 ለክሪስታል ፓላስ ለመጫወት መስማማቱ መሆኑን ገልጿል፡፡ . ተጫዋቹ በወቅቱ ክለብ አልባ የነበረ በመሆኑ የቀረበለትን የፈርምልን ጥያቄ ሳያቅማማ የተቀበለ ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ 15 ጨዋታዎች አንድ ጎል ብቻ ካስቆጠረ በኋላ ወደተጠባባቂ ወንበር ወርዶ ውሉን ለመጨረስ ተገዷል፡፡. ተጫዋቹ ለ ለኪፕ እንደተናገረው “በእንግሊዝ ከታላላቅ ክለቦች ጋር መልካም ጊዜያትን አሳልፌአለሁ ፤ እኔና ቤተሰቤ ደስተኛ ነበርን፡፡ የሰራሁት ብቸኛ ስህተት ለፓላስ ለመጫወት መስማማቴ ነው፡፡ ይህን ያደረኩት ለኔ ሰዎች ስል ነው፡፡ ሁሌም ‘ወደሜዳ ተመለስ እንጂ!’ ይሉኝ ነበር፡፡ የጨዋታ ዘመኔ መጥፎ ውሳኔ ነበር”ብሏል፡፡ ተጫዋቹ ወደቱርክ በማቅናት ለባሳክሺር ከፈረመ በኋላ ወደቀድሞ ብቃቱ የተመለሰ ሲሆን ክለቡን ለቱርክ ዋንጫ ፍፃሜ ማድረስ ችሏል፡፡ አዴባዮር ጨምሮም የቱርክ ቆይታው እንደተመቸውና ወደሌላ ክለብ የመዘዋወር ዕቅድ እንደሌለው አሳውቋል፡፡
    0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • “ተዉ አታበላሹ እንጂ…”

    ኤፍሬም እንዳለ

    እንዴት ሰነበታችሁሳ!
    በዛ ሰሞን ነው…በተቆፈረው የከተማው አንድ ክፍል፡፡ በአሥራዎቹ መጀመሪያ የሚሆኑ ልጆች የተቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ከርቀት ድንጋይ እየወረወሩ ይፎካከራሉ፡፡ ይሄኔ አንድ አዛውንት ምን ቢሉ ጥሩ ነው…
    “ልጆች ተዉ አታበላሹ እንጂ፣ ለእናንተ ነው እኮ የተቆፈረው፡፡”
    እንግዲህ ምን ያስቡ፣ ምን እግዚአብሔር ይወቀው፡፡ ግን ነገርዬዋ…አለ አይደል…ለሌላውም ታገለግላለች፡፡
    “ተዉ አታበላሹ እንጂ…” ሊባልላቸው የሚገባ መአት ነገሮች አሉ፡፡
    ስሙኝማ…ሰኔ ገባ አይደል፣ በጀት መዝጊያ ጊዜ!… እኔ የምለው… ያለአግባብ ምን ሆነ የተባለ ስንት ቢሊዮን ብር ነው! እንዴት ነው…ነገርዬው ሁሉ ሀዲዱን የሳተ ባቡር እየሆነ ያለው! በሚሊዮኖች ስንገረም፣ በመቶ ሚሊዮኖች ስንገረም፣ ጭራሽ ቢሊዮኖች ገባና አረፈው!
    እናማ…“ተዉ አታበላሹ እንጂ…” ሊባልላቸው የሚገባ መአት ነገሮች አሉ፡፡
    ዘንድሮ…አለ አይደል…ሁሉም ነገሮችን የሚያየው ከራሱ ሆኗል፡፡ እሱ ከደላው ሁሉም ሰው የደላው ይመስለዋል፣ እሱ አሼሼ ገዳሜ ካለ ሁሉም ሰው አሼሼ ገዳሜ የሚል ይመስለዋል፡፡ በሆነ ነገር ‘ሙያተኛ’ የሆኑት ሰዎች ሙያው የሚጠይቀውን ማብራሪያ ከመስጠት እንደራሳቸው ጓዳ ብቻ ሲያስቡት አስቸጋሪ ነው፡፡
    “ቲማቲም እንዲህ የተወደደችበትን ምክንያት ልታስረዳኝ ትችላለህ?…”
    “መሠረታዊ የሆነ ጥያቄ ነው ያመጣኸው፡፡ ይገርምሀል፣ ይሄን ጥያቄ መቼ ነው የምጠየቀው ብዬ አስብ ነበር፡፡ ዋናው ነገር በመጀመሪያ ቲማቲም ምን አይነት ጥቅም እንደሚሰጥ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡”
    ሰውየው ምን ነካው! የቲማቲም እርሻ አለው እንዴ!
    ስለ ዋጋው መወደድ ጠየቅሁት እንጂ የካሎሪና የቪታሚን ዝርዝር አቅርብልኝ አልኩት!
    “ይቅርታ፣ መቼም ስለ ቲማቲም ጥቅም የማያውቅ አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ አሁን ማወቅ የምፈልገው ዋጋው እንደ ጠፈር መንኮራኩር ሽቅብ ለምን እንደተተኮሰ ነው፡፡
    “እኮ መወደዱ ከሚሰጠው ጥቅም ጋር መያዝ አለበት፡፡ ቲማቲም ተወደደ ማለት ብቻ ሳይሆን ዋናው ማወቅ የሚገባን ከሚሰጠው ጥቅም አንጻር ለምን ኪሎ መቶ ብር አይገባም…”
    ይቺን ይወዳል! “ኧረ አንተኑ መቶ…” ብላችሁ ትጀምሩና ትተዉታላችሁ፡፡ ልክ እኮ ቲማቲም አዲስ የተገኘች ግኝት ሆና ገና “ጉድ! ጉድ!” እየተባለላት ያለች ነገር ያስመስላታል፡፡
    “ተዉ አታበላሹ እንጂ…” ሊባልላቸው የሚገባ መአት ነገሮች አሉ፡፡
    እናላችሁ… ስንት ዘመን ስንጠቀምባቸው የኖርናቸው ነገሮች…አለ አይደል… በፈረንጂኛ ስለተጻፈላቸው ብቻ የሆነ አዲስ ግኝት የተገኘ ይመስል ስናደርገው የሆነ ችግር አለ፡፡
    “ስለ ጤፍስ ምን ታስባለህ?”
    “ጤፍማ አሁን ዓለም አቀፋዊ ሆናለች፣ በእውነት ደስ የሚል ነው፡፡”
    “ደስ የሚል ነው የሚለውን ብታስረዳኝ…”
    “ፈረንጆች ጤፍን መውደዳቸው በጣም ደስ ይላል፣ ይህ ጤፍ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኘ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡”
    “ፈረንጅ ወደደው አልወደደው የጤፍን ደረጃ የሚቀንሰው ነገር አለ እንዴ! ለምንድነው ስንት ሺህ ዓመት ስንጠቀምበት ኖረን አሁን የምንዘምርለትን ያህል ሳንዘምርለት የኖርነው!”
    “አልገባህም፣ ዋናው ነገር ጤፍ ዓለም አቀፍ መሆኗ ለመልካም ገጽታ ግንባታ ያግዛል፡፡ ‘ጤፍ’ የሚለው ነገር ሲነሳ የኢትዮዽያም ስም አብሮ ይነሳል…”
    ቆይማ…የኢትዮዽያ ስም እንዲነሳ የሚያደርጉ መአት ነገሮች አሉ እኮ! ስንት በአንድ ወይ በሌላ ምክንያት ላያቸው ላይ የተቀመጥንባቸው… አለ አይደል… የፈረደበት ፈረንጅ ‘እስኪያወራላቸው’ የምንጠብቃቸው ስንት ነገሮች አሉ እኮ!
    እኔ የምለው…እንግዲህ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ… ይቺ ‘የመልካም ገጽታ ግንባታ’ የሚሏት ነገር እንዴት ነው እንዲህ መጫወቻ የሆነችው! አሸር በአሸር የሆነውን ‘ዲስኩር’ ሁሉ ማሳመሪያ ሆና ‘ኩል፣’ ‘ፋውንዴሽን’ ምናምን አስመሰልናት እኮ!
    “ድርጅታችን የአገሪቱን መልካም ገጽታ በውጪ ለመገንባት አቅዶ እየሠራ ነው…” አይነት ‘ወሬ’ ማሳመሪያ ተለምዷል፡፡ ድርጀቱ እኮ እንኳን የአገር ገዕታ ሊገነባ ራሱ ገጽታ የሚባል ነገር የለውም! ቂ…ቂ…ቂ… ግን በዚህ የአገር ገጽታ ለመገንባት መካከለኛ ገቢ ለመድረስ ምናምን የሚባሉ ‘ዲስኩር’ ማሳመሪያዎች ላይ “እንዴት?” “ለምን?” አይነት ጥያቄዎች ስለማይነሱ እንደተፈለገው መደጋገም ይቻላል፡፡ እናማ… ይቺ ‘መልካም ገፅታ ግንባታ’ የምትለዋ ሀረግ… ጠቃሚነቷ ሳስቶ ትርጉም አልባ እንዳትሆንማ!”
    “እኔ እንዲህ የሚሉ ብዙ ሰዎች ከልባቸው ሳይሆን ‘እነ እከሌ ብለውት እኔ ሳልለው እንዳልቀር’ ብለው ይመስለኛል፡፡ ጤፍን ከአገር መልካም ገፅታ ጋር ማያያዝ…”
    “ቆይ! ቆይ! እንዲህ ስትል ምን ማለትህ ነው? አንተ እንደ ጠላቶቻችን የዚችን አገር እድገት አትፈልግም እንዴ? አንተ…”
    አሁን ነገር መጣ! አሁን ገና ዋናው ነገር መጣ! አሁን ገና የአገር በሽታ እየሆነ ያለ ነገር መጣ! በሆነ አቋም ላይ ጠንከር ብላችሁ ከተከራከራችሁ…እንዲህ አይነት ነገር እንደሚመጣ ጠብቁ፡፡ ሀሳቦቻችሁን የምታራምዱ ሳይሆን ከጀርባ ሌላ ዓላማ ያላችሁ አስመስለው ‘ጎመን በጤና’ እንድትሉ ያደርጓችኋል፡፡
    “ተዉ አታበላሹ እንጂ…” ሊባልላቸው የሚገባ መአት ነገሮች አሉ፡፡
    “እሺ በአጠቃላይ የዋጋ መወደድ ምክንያት ምንድነው ትላለህ?”
    “እሱ እንኳን የእድገት ምልክት ነው፡፡”
    “ይቅርታ የብዙ ነገሮች ዋጋ ተወደደ፣ ከአቅማችን በላይ ሆነ፣ ኑሮ ከፋ እያልኩህ እኮ ነው!”
    “እኮ እኔስ ምንድነው የምልህ…ይሀ ሁሉ ምን ያህል እያደግን እንደሆንን የሚያሳይ ነው፡፡”
    “በነገራችን ላይ እየሠራኸው የነበረው ቤት ምን ደረሰ?”
    “እሱማ አለቀና አከራየሁት እኮ፡፡ እንደውም ሲ.ኤም.ሲ. የተጀመረ ጂ ፕላስ ቱ ገዝቼ እየሠራሁ ነው፡፡”
    “ታዲያ መጀመሪያውኑ እንዲህ አትለኝም!” ትላላችሁ በሆዳችሁ፡፡ ግን ደግሞ ዝም ብሎ ማለፉም አላስችል ይላል፡፡
    “ለምሳሌ እኛ ቤት ቁርስ መብላት ትተናል። የምሳ ፍጆታችንም በአርባ ስምንት በመቶ አቆልቁሏል። ይቅርታ እዚህ አገር ሁሉንም ነገር በመቶኛ ማስላት የማይሸረፍ ሰብዊ መብት ስለሆነ ነው ቁጥር የጠቀስኩት፡፡”
    “ምን እያልክ ነው…”
    “እኔም፣ የማውቃቸውም ሰዎች የምንበላው እየቸገረን እንዴት የእድገት ምልክት ነው ትለኛለህ!”
    “እሱ የአንተ ጉዳይ ነው፡፡”
    “ለምሳሌ ድሮ ለምሳዬ ሁለት አይነት ምግብ እበላ ነበር፡ ዘንድሮ ግን አልሆነም፡፡”
    “እሱ እንግዲህ…”
    “ለምሳሌ በፊት ግፋ ቢል ፓራሳይቷ ምናምን ብታስቸግረኝ ነው…አሁን ግን የበሽታ አይነት በሙሉ ሰፍሮብናል፣ ይሄም የእድገት ምልክት ነው?…”
    እግረ መንገዴን ይቺን ስሙኝማ…ሰዓሊው ሴትዮዋን እየሳላት ነበር፡፡ ሲጨርስም አቀረበላትና…
    “ምን ይመስልሻል…” ይላታል፡፡
    እሷም ግንባሯን ቋጥራ “ምን በደልኩህ! ምን ብበድልህ ነው እንዲህ አድርገህ የምትስለኝ…” ትለዋለች፡፡
    ሰዓሊው ይደነግጥና “ምነው፣ ምን አጠፋሁ!” ይላታል፡፡ እሷ እየተንገሸገሸች…
    “ጦጣ ነው እኮ ያስመሰልከኝ!…” ትላለች፡፡
    ይሄኔ ሰዓሊው ሳቅ ብሎ ምን ቢላት ጥሩ ነው… “እሱ የእኔ ሳይሆን የወላጆችሽ ጥፋት ነው…” ብሏት አረፈው፡፡
    ሰው ከመውቀስ በፊት ጥፋቱ የማን እንደሆነ ይለይማ!
    እናማ…“ተዉ አታበላሹ እንጂ…” ሊባልላቸው የሚገባ መአት ነገሮች አሉ፡፡
    ደህና ሰንብቱልኝማ!
    “ተዉ አታበላሹ እንጂ…” ኤፍሬም እንዳለ እንዴት ሰነበታችሁሳ! በዛ ሰሞን ነው…በተቆፈረው የከተማው አንድ ክፍል፡፡ በአሥራዎቹ መጀመሪያ የሚሆኑ ልጆች የተቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ከርቀት ድንጋይ እየወረወሩ ይፎካከራሉ፡፡ ይሄኔ አንድ አዛውንት ምን ቢሉ ጥሩ ነው… “ልጆች ተዉ አታበላሹ እንጂ፣ ለእናንተ ነው እኮ የተቆፈረው፡፡” እንግዲህ ምን ያስቡ፣ ምን እግዚአብሔር ይወቀው፡፡ ግን ነገርዬዋ…አለ አይደል…ለሌላውም ታገለግላለች፡፡ “ተዉ አታበላሹ እንጂ…” ሊባልላቸው የሚገባ መአት ነገሮች አሉ፡፡ ስሙኝማ…ሰኔ ገባ አይደል፣ በጀት መዝጊያ ጊዜ!… እኔ የምለው… ያለአግባብ ምን ሆነ የተባለ ስንት ቢሊዮን ብር ነው! እንዴት ነው…ነገርዬው ሁሉ ሀዲዱን የሳተ ባቡር እየሆነ ያለው! በሚሊዮኖች ስንገረም፣ በመቶ ሚሊዮኖች ስንገረም፣ ጭራሽ ቢሊዮኖች ገባና አረፈው! እናማ…“ተዉ አታበላሹ እንጂ…” ሊባልላቸው የሚገባ መአት ነገሮች አሉ፡፡ ዘንድሮ…አለ አይደል…ሁሉም ነገሮችን የሚያየው ከራሱ ሆኗል፡፡ እሱ ከደላው ሁሉም ሰው የደላው ይመስለዋል፣ እሱ አሼሼ ገዳሜ ካለ ሁሉም ሰው አሼሼ ገዳሜ የሚል ይመስለዋል፡፡ በሆነ ነገር ‘ሙያተኛ’ የሆኑት ሰዎች ሙያው የሚጠይቀውን ማብራሪያ ከመስጠት እንደራሳቸው ጓዳ ብቻ ሲያስቡት አስቸጋሪ ነው፡፡ “ቲማቲም እንዲህ የተወደደችበትን ምክንያት ልታስረዳኝ ትችላለህ?…” “መሠረታዊ የሆነ ጥያቄ ነው ያመጣኸው፡፡ ይገርምሀል፣ ይሄን ጥያቄ መቼ ነው የምጠየቀው ብዬ አስብ ነበር፡፡ ዋናው ነገር በመጀመሪያ ቲማቲም ምን አይነት ጥቅም እንደሚሰጥ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡” ሰውየው ምን ነካው! የቲማቲም እርሻ አለው እንዴ! ስለ ዋጋው መወደድ ጠየቅሁት እንጂ የካሎሪና የቪታሚን ዝርዝር አቅርብልኝ አልኩት! “ይቅርታ፣ መቼም ስለ ቲማቲም ጥቅም የማያውቅ አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ አሁን ማወቅ የምፈልገው ዋጋው እንደ ጠፈር መንኮራኩር ሽቅብ ለምን እንደተተኮሰ ነው፡፡ “እኮ መወደዱ ከሚሰጠው ጥቅም ጋር መያዝ አለበት፡፡ ቲማቲም ተወደደ ማለት ብቻ ሳይሆን ዋናው ማወቅ የሚገባን ከሚሰጠው ጥቅም አንጻር ለምን ኪሎ መቶ ብር አይገባም…” ይቺን ይወዳል! “ኧረ አንተኑ መቶ…” ብላችሁ ትጀምሩና ትተዉታላችሁ፡፡ ልክ እኮ ቲማቲም አዲስ የተገኘች ግኝት ሆና ገና “ጉድ! ጉድ!” እየተባለላት ያለች ነገር ያስመስላታል፡፡ “ተዉ አታበላሹ እንጂ…” ሊባልላቸው የሚገባ መአት ነገሮች አሉ፡፡ እናላችሁ… ስንት ዘመን ስንጠቀምባቸው የኖርናቸው ነገሮች…አለ አይደል… በፈረንጂኛ ስለተጻፈላቸው ብቻ የሆነ አዲስ ግኝት የተገኘ ይመስል ስናደርገው የሆነ ችግር አለ፡፡ “ስለ ጤፍስ ምን ታስባለህ?” “ጤፍማ አሁን ዓለም አቀፋዊ ሆናለች፣ በእውነት ደስ የሚል ነው፡፡” “ደስ የሚል ነው የሚለውን ብታስረዳኝ…” “ፈረንጆች ጤፍን መውደዳቸው በጣም ደስ ይላል፣ ይህ ጤፍ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኘ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡” “ፈረንጅ ወደደው አልወደደው የጤፍን ደረጃ የሚቀንሰው ነገር አለ እንዴ! ለምንድነው ስንት ሺህ ዓመት ስንጠቀምበት ኖረን አሁን የምንዘምርለትን ያህል ሳንዘምርለት የኖርነው!” “አልገባህም፣ ዋናው ነገር ጤፍ ዓለም አቀፍ መሆኗ ለመልካም ገጽታ ግንባታ ያግዛል፡፡ ‘ጤፍ’ የሚለው ነገር ሲነሳ የኢትዮዽያም ስም አብሮ ይነሳል…” ቆይማ…የኢትዮዽያ ስም እንዲነሳ የሚያደርጉ መአት ነገሮች አሉ እኮ! ስንት በአንድ ወይ በሌላ ምክንያት ላያቸው ላይ የተቀመጥንባቸው… አለ አይደል… የፈረደበት ፈረንጅ ‘እስኪያወራላቸው’ የምንጠብቃቸው ስንት ነገሮች አሉ እኮ! እኔ የምለው…እንግዲህ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ… ይቺ ‘የመልካም ገጽታ ግንባታ’ የሚሏት ነገር እንዴት ነው እንዲህ መጫወቻ የሆነችው! አሸር በአሸር የሆነውን ‘ዲስኩር’ ሁሉ ማሳመሪያ ሆና ‘ኩል፣’ ‘ፋውንዴሽን’ ምናምን አስመሰልናት እኮ! “ድርጅታችን የአገሪቱን መልካም ገጽታ በውጪ ለመገንባት አቅዶ እየሠራ ነው…” አይነት ‘ወሬ’ ማሳመሪያ ተለምዷል፡፡ ድርጀቱ እኮ እንኳን የአገር ገዕታ ሊገነባ ራሱ ገጽታ የሚባል ነገር የለውም! ቂ…ቂ…ቂ… ግን በዚህ የአገር ገጽታ ለመገንባት መካከለኛ ገቢ ለመድረስ ምናምን የሚባሉ ‘ዲስኩር’ ማሳመሪያዎች ላይ “እንዴት?” “ለምን?” አይነት ጥያቄዎች ስለማይነሱ እንደተፈለገው መደጋገም ይቻላል፡፡ እናማ… ይቺ ‘መልካም ገፅታ ግንባታ’ የምትለዋ ሀረግ… ጠቃሚነቷ ሳስቶ ትርጉም አልባ እንዳትሆንማ!” “እኔ እንዲህ የሚሉ ብዙ ሰዎች ከልባቸው ሳይሆን ‘እነ እከሌ ብለውት እኔ ሳልለው እንዳልቀር’ ብለው ይመስለኛል፡፡ ጤፍን ከአገር መልካም ገፅታ ጋር ማያያዝ…” “ቆይ! ቆይ! እንዲህ ስትል ምን ማለትህ ነው? አንተ እንደ ጠላቶቻችን የዚችን አገር እድገት አትፈልግም እንዴ? አንተ…” አሁን ነገር መጣ! አሁን ገና ዋናው ነገር መጣ! አሁን ገና የአገር በሽታ እየሆነ ያለ ነገር መጣ! በሆነ አቋም ላይ ጠንከር ብላችሁ ከተከራከራችሁ…እንዲህ አይነት ነገር እንደሚመጣ ጠብቁ፡፡ ሀሳቦቻችሁን የምታራምዱ ሳይሆን ከጀርባ ሌላ ዓላማ ያላችሁ አስመስለው ‘ጎመን በጤና’ እንድትሉ ያደርጓችኋል፡፡ “ተዉ አታበላሹ እንጂ…” ሊባልላቸው የሚገባ መአት ነገሮች አሉ፡፡ “እሺ በአጠቃላይ የዋጋ መወደድ ምክንያት ምንድነው ትላለህ?” “እሱ እንኳን የእድገት ምልክት ነው፡፡” “ይቅርታ የብዙ ነገሮች ዋጋ ተወደደ፣ ከአቅማችን በላይ ሆነ፣ ኑሮ ከፋ እያልኩህ እኮ ነው!” “እኮ እኔስ ምንድነው የምልህ…ይሀ ሁሉ ምን ያህል እያደግን እንደሆንን የሚያሳይ ነው፡፡” “በነገራችን ላይ እየሠራኸው የነበረው ቤት ምን ደረሰ?” “እሱማ አለቀና አከራየሁት እኮ፡፡ እንደውም ሲ.ኤም.ሲ. የተጀመረ ጂ ፕላስ ቱ ገዝቼ እየሠራሁ ነው፡፡” “ታዲያ መጀመሪያውኑ እንዲህ አትለኝም!” ትላላችሁ በሆዳችሁ፡፡ ግን ደግሞ ዝም ብሎ ማለፉም አላስችል ይላል፡፡ “ለምሳሌ እኛ ቤት ቁርስ መብላት ትተናል። የምሳ ፍጆታችንም በአርባ ስምንት በመቶ አቆልቁሏል። ይቅርታ እዚህ አገር ሁሉንም ነገር በመቶኛ ማስላት የማይሸረፍ ሰብዊ መብት ስለሆነ ነው ቁጥር የጠቀስኩት፡፡” “ምን እያልክ ነው…” “እኔም፣ የማውቃቸውም ሰዎች የምንበላው እየቸገረን እንዴት የእድገት ምልክት ነው ትለኛለህ!” “እሱ የአንተ ጉዳይ ነው፡፡” “ለምሳሌ ድሮ ለምሳዬ ሁለት አይነት ምግብ እበላ ነበር፡ ዘንድሮ ግን አልሆነም፡፡” “እሱ እንግዲህ…” “ለምሳሌ በፊት ግፋ ቢል ፓራሳይቷ ምናምን ብታስቸግረኝ ነው…አሁን ግን የበሽታ አይነት በሙሉ ሰፍሮብናል፣ ይሄም የእድገት ምልክት ነው?…” እግረ መንገዴን ይቺን ስሙኝማ…ሰዓሊው ሴትዮዋን እየሳላት ነበር፡፡ ሲጨርስም አቀረበላትና… “ምን ይመስልሻል…” ይላታል፡፡ እሷም ግንባሯን ቋጥራ “ምን በደልኩህ! ምን ብበድልህ ነው እንዲህ አድርገህ የምትስለኝ…” ትለዋለች፡፡ ሰዓሊው ይደነግጥና “ምነው፣ ምን አጠፋሁ!” ይላታል፡፡ እሷ እየተንገሸገሸች… “ጦጣ ነው እኮ ያስመሰልከኝ!…” ትላለች፡፡ ይሄኔ ሰዓሊው ሳቅ ብሎ ምን ቢላት ጥሩ ነው… “እሱ የእኔ ሳይሆን የወላጆችሽ ጥፋት ነው…” ብሏት አረፈው፡፡ ሰው ከመውቀስ በፊት ጥፋቱ የማን እንደሆነ ይለይማ! እናማ…“ተዉ አታበላሹ እንጂ…” ሊባልላቸው የሚገባ መአት ነገሮች አሉ፡፡ ደህና ሰንብቱልኝማ!
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    1
    0 Comments 0 Shares