በቅርብ የተቀጠርኩበት ቢሮ ውስጥ!
(አሳዬ ደርቤ)
ከአንድ ወንድና ከአንዲት ሴት የስራ ባልደረባዎቼ ጋር ያለ ስራ ተቀምጨ ሳስተውላቸው እውላለሁ፡፡
ወንዱ ስልጣን ይፈልጋል፡፡ ሴቲቱ ደግሞ ባለ-ስልጣን፡፡ አካሄዳቸው ቢለያይም አላማቸው አንድ ነው፡፡ መንገስ!
ከኮምፒውተራችን ላይ ቀና ብለን ዐይናችን ወደ ልጅዬው ጠረጴዛ ስንልከው ከባጁ ጎን ‹‹ትናንት ምን ሰራሁ? ዛሬ ምን ልስራ? ለነገስ ምን አቀድኩ?›› የሚል ደረቅ ጥያቄ በነጭ ወረቀት ላይ በትልቁ ለጥፎልን እናገኘዋለን፡፡
የለጠፈውን ነገር ከማንበብ አልፈን ‹‹እስኪ የእለቱን ቀርቶ የአመቱን እቅድህን አምጣ?›› ስንለው ግን… የወረቀት ክምር ሲንድ ይቆይና… ዐይኑን ሌላ ቦታ ላይ አስቀምጦ ‹‹እቅድ እንኳን የለኝም›› የሚል መልስ ይሰጠናል፡፡
እይታችንን ከልጁ ላይ አንስተን ወደ ሴቷ መቀመጫ ስንሰደው ጠረጴዛና ወንበሯን እንጂ ልጂቱን አናገኛትም፡፡ ከአንዱ ሚኒስቴር ዲኤታ ወይም ደግሞ ከአንዱ ዳይሬክተር ቢሮ ሄዳለች ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ኮረዳዋ ወፍራም ጭኗቿንና ድቡልቡል ጡቷቿን፣ አስጎብኝታ እስክትመጣ ድረስ ቅኝታችንን ወደ ልጁ ስንመልስ ከጀርባው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴራችንን ፎቶ በትልቁ ለጥፎ… ከፊት ለፊቱ በግራና በቀኝ ሁለት ባንድራዎች ሰክቶ… ወንበሩ ላይ ተጎልቶና አዲስ ራዕይ መጽሔት ላይ ተደፍቶ ጭንቅላቱን በግርምት እየወዘወዘ እናገኘዋለን፡፡
ይሄ ልጅ ሰውን የሚመለከተው በዐይኑ ሳይሆን በግንባሩ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ እንደ እኔ አይነቱን የአስመሳይነት ጥበቡን የባነነበት ሰው ሲያጋጥመው ሰውዬውን የሚያየው እንደ በሬ ከማንጅራቱ ወደ ታች ተቀልብሶ በመሆኑ… ‹‹እዚህ ልጅ ጭንቅላት ላይ የተቀመጠው ኮፊያ ቢነሳ ጸጉሩ መሃከል… ሰውን ለመውጋት ያቆጠቆጡ ‹ቡቃያ ቀንዶች› አይጠፉም!›› ብለን ብናስብ ሐጢያት አይሆንብንም፡፡
‹ልጁ› የአሁን ዘመን ስልጣን ከበረሃ ወጥታ መድረክ ላይ እንደተሰየመች ጠንቅቆ የተረዳ ነው፡፡ ስለዚህ እያንዳንዷን መድረክ ሳይጠቀምባት እንዲታልፈው አይፈልግም፡፡
ለምሳሌ ባለፈው የጥልቅ ተሃድሶ ስብሰባ ያደረግን ጊዜ የመጀመሪያው ተናጋሪ እሱ ነበረ፡፡ በቀረበው ሰነድ ላይ ተመስርቶ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ከሊበራል ዲሞክራሲና ከሶሻል ዲሞክራሲ የሚልቅበትን ሁኔታዎች ያስረዳል ተብሎ ሲጠበቅ የማይክራፎኑን ጫፍ እንደ ልጃገረድ ጡት በፍቅር እየደባበሰ ‹ለተሰጠኝ እድል አመሰግናለሁ› እያለ አስር ጊዜ መደጋገሙን ስንሰማ… መድረኩን የሚመሩት ሚኒስቴር ለልጁ የሰጡት ‹‹የአርባ ቀን እድሉን›› እንጂ ‹‹ማይክራፎኑን›› አይመስለንም፡፡
ከዚያ በኋላ ብዙ ትንታኔ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ ምንም ጭብጥ ያለው ነገር ሳይናገር ‹‹በሕይወቴ እንደዚህ ያለ ጣፋጭ የመወያያ ሰነድ እና ጣፋጭ የሆነ መንግስት አጋጥሞኝ አያውቅም›› ብሎ ሃሳቡን አበቃ፡፡ (ከዚህም ጋር ተያይዞ አንዳንድ ተሰብሳቢዎች ‹‹በህይወቱ ስንት መንግስት እንዳሳለፈ ቢያብራራልን ጥሩ ነበር›› በማለት አንሾካሾኩ!)
.
.
ልጂቱ ከንፈሯን በቀይ ቀለም አፍክታ፣ ማስቲካዋን አፈንድታ ወደ ቢሮ ስለተመለሰች ይሄን አሰልች ሰውዬ ወንበሩ ላይ በተወዘፈበት ትተነው ወደ ኮረዳዋ እንለፍ፡፡
ስሟን ላስተዋውቃሁ መሰል! ‹‹ዘመናይ ትባላለች››
ያ ‹የHip hop› የሙዚቃ ስልትን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ባህር-ዛፍ ፍሬ በጫማው አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ያስተዋወቀው ዘፋኝ ማን ነበር? ይሄ እንኳን…..
ዘመናይ ናት እሷ…. ኧኸ
ዘመናይ ናት እሷ…. ኧኸ
ጫማዋ ጥልፍልፍ… ኧኸ
አጭር ነው ቀሚሷ… ኧኸ
ብሎ የዘፈነው…. ኧኸ
ይመስለኛል ለእሷ!..ኧኸ…… ብለን በግጥም ሃሳባችንን እንግለጽና ዘመናይን ከግርጌ ጀምረን እያየናት ወደ ራስጌዋ እንዝለቅ፡፡
ዓመቱን ሙሉ ለጸሐይና ለንፋስ ተጋልጦ የሚኖረው እግሯን ስንመለከት በዐይናችን የሚገባው ቅላቱና ጥራቱ ብቻ ሳይሆን የኮባ ግንድ የመሰለው ልስላሴውም ጭምር ነው፡፡
(አንዳንዴ ባለትዳር ባልሆን ኖሮ አራት ኪሎ ለመግባት ሳይሆን ከዘመናይ ባት ውስጥ ለመግባት ስል ባለስልጣን መሆንን እመኛለሁ፡፡)
ከእግሯ ከፍ ብለን ወደ መቀመጫዋ ስንዘልቅ ‹‹እንስራሽን ባደረገኝ›› ብሎ ያንጎራጎረው ብላቴና ዘፋኝ ይታወሰናል፡፡ እስኪ እንደው በሞቴ አሁን ካልጠፋ ቃላትና ካልጠፋ ምኞት ‹‹ከጀርባሽ እንዲውል እንስራሽን ልሁን›› ብሎ መመኘት ምን ይሉታል? ከዚህ ይልቅ ባንድ ፊቱ ‹ቂጥሽን ባ’ረገኝ› ብሎ ማጠቃለል አይሻልም?... (መቼም የፈለገ ነገር ቢሆን ‹ገል› ከመሆን ‹ገላ› መሆን ሳይሻል አይቀርም፡፡)
ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ስተን… ወደላይ ከፍ ስንል አዝራር ለመበጠስና ትዳር ለማፍረስ የተፈጠሩ ሁለት መንትያ ጡቶች ዘመናይ ደረት ላይ ተንጠልጥለው እና አብጠው እናገኛለን፡፡ በታላቅ ተመስጦ ውስጥ ሆኜ ለእነዚህ ጡቶች ቤት ብቻ ሳይሆን ማንጅራትንም ጭምር የሚመታ ግጥም ደርድሬ… ከማሻሸቱ ይልቅ መጥባቱ ላይ ትኩረቱን ያደረገውን ‹‹ልጅሽን ባረገኝ›› የሚል ስያሜ የሰጠሁትን ነጠላ ዘፈኔን ‹በናሁ ቴሌቪዥን› ለመልቀቅ ድምፄ የሚጠራበትንና ፒያኖ የማገኝበትን ቀን እየተጠባበኩ እገኛለሁ፡፡
.
አንባቢ ሆይ ከጡቷ ከፍ ብለን ወደ ፊቷ ስንዘልቅ ልክ እንደኛው ሁላ ዘመናይም በግርምት ውስጥ ሆና ስትመለከተን ዐይን ለዐይን እንገጣጠማለን፡፡ ‹‹እንኳን አይተሺኝ እንዲሁም በርግግ፣ በርግግ ይለኛል›› አለ ሰውዬው፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ይሄ የስልጣን ጥመኛም በአንክሮ ሲከታተለኝ ቆይቶ ኖሮ ‹‹ምነው እንደ መቀሌ ሰማዕታት ሀውልት በግርምት ፈዘህ አየሃት’ሳ?›› በማለት ይበልጥ ያደናግጠኛል፡፡
እናም… ‹ምራቃችን ድርቅ፣ ላባችን ፍልቅ› ስላለብን ‹‹የዘንድሮ ሙቀት ገደለን…›› እያልን ወደ ውጭ ስንወጣ ሃይለኛ ንፋስ እና ውርጭ ያጋጠመን ቢሆንም… ወደ ቢሮ ተመልሰን ትረካችንን ከመጨረስ ይልቅ በዚያው መሄዱን መረጥን…