• 0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • TEWNET.COM
    Yetekema Hiwot - Part 55 (Kana TV Drama)
    Yetekema Hiwot - Part 55 (Kana TV Drama) 3681...
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታዋቂው የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይክ የማራቶን ሩጫ ከሁለት ሰዓት በታች እንዲገባ ለማስቻል ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።

    ናይክ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች ለማጠናቀቅ እንደሚቻል ለመሞከርም ሶስት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አትሌቶችን መርጦ ነበር ዝግጅት ሲያደርግ የመነረው።

    በሙከራ ሩጫው ላይም ኢትዮጵያዊው አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ፣ ኬኒያዊው አትሌት ኤሉዪድ ኪፕቾጌ እና ኤርትራዊው ዘረሰናይ ታደሰ ተካፍለዋል።

    ሆኖም ግን ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች ለማግባት የተደረገው ጥረት ለ26 ሰከንድ ብቻ ሳይሳካ ቀርቷል።

    በዛሬው እለት የተደረገውን የማራቶን ሩጫ የ32 ዓመቱ ኬኒያዊ አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጌ 2 ሰዓት ከ00 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ በመግባት ያጠናቀቀ ሲሆን፥ በናይክ የተቀመጠውን እቅድ ለማሳካትም 26 ሰከንዶች ብቻ ነበር የቀሩት።

    ኤርትራዊው አትሌት ዘረሰናይ ታደሰ እና ኢትዮጵያዊው ሌሊሳ ዴሲሳ ኪፕቾጌን ተከትለው መግባት ችለዋል።

    ኤሉድ ኪፕቾጌ በዛሬው እለት የማራቶን ሩጫን ያጠናቀቀበት ሰዓት በዓለም ክበረ ወሰንነት አይመዘገብም የተባለ ሲሆን፥ የማራቶን ሩጫ የዓለም

    ክብረ ወሰን በ2 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ በኬኒያዊው አትሌት ዴኒስ ኬሚዬቶ እጅ ይገኛል።

    ውጤቱ በዓለም ክበረ ወሰንነት ባይመዘገብም የ32 ዓመቱ ኪፕቾጌ ሩጫውን ታሪካዊ ብሎታል።

    ምንጭ፦ ቢቢሲ
    አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታዋቂው የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይክ የማራቶን ሩጫ ከሁለት ሰዓት በታች እንዲገባ ለማስቻል ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። ናይክ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች ለማጠናቀቅ እንደሚቻል ለመሞከርም ሶስት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አትሌቶችን መርጦ ነበር ዝግጅት ሲያደርግ የመነረው። በሙከራ ሩጫው ላይም ኢትዮጵያዊው አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ፣ ኬኒያዊው አትሌት ኤሉዪድ ኪፕቾጌ እና ኤርትራዊው ዘረሰናይ ታደሰ ተካፍለዋል። ሆኖም ግን ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች ለማግባት የተደረገው ጥረት ለ26 ሰከንድ ብቻ ሳይሳካ ቀርቷል። በዛሬው እለት የተደረገውን የማራቶን ሩጫ የ32 ዓመቱ ኬኒያዊ አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጌ 2 ሰዓት ከ00 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ በመግባት ያጠናቀቀ ሲሆን፥ በናይክ የተቀመጠውን እቅድ ለማሳካትም 26 ሰከንዶች ብቻ ነበር የቀሩት። ኤርትራዊው አትሌት ዘረሰናይ ታደሰ እና ኢትዮጵያዊው ሌሊሳ ዴሲሳ ኪፕቾጌን ተከትለው መግባት ችለዋል። ኤሉድ ኪፕቾጌ በዛሬው እለት የማራቶን ሩጫን ያጠናቀቀበት ሰዓት በዓለም ክበረ ወሰንነት አይመዘገብም የተባለ ሲሆን፥ የማራቶን ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰን በ2 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ በኬኒያዊው አትሌት ዴኒስ ኬሚዬቶ እጅ ይገኛል። ውጤቱ በዓለም ክበረ ወሰንነት ባይመዘገብም የ32 ዓመቱ ኪፕቾጌ ሩጫውን ታሪካዊ ብሎታል። ምንጭ፦ ቢቢሲ
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ደደቢት እና ሀዋሳ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል።

    ደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም ፋሲል ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል።

    ለደደቢት ሁለቱንም ግቦች ጌታነህ ከበደ ሲያስቆጥር ለፋሲል ኤደም ኮድዞ ከመረብ አዋህዷል።

    ሀዋሳ ከተማም በተመሳሳይ ወልዲያ ከተማን 2 ለ 1 የረታ ሲሆን፥ ፍሬው ሰለሞን እና ጃኮ አራፋት የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። ለወልዲያ ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ አንዱአለም ንጉሴ ማስቆጠር ችሏል።

    አርባ ምንጭ ከተማ ከአዳማ ከተማ ያደረጉት ያለው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቋል።

    ጅማ ላይ ከጅማ አባቡና ጋር ጨዋታውን ያደረገው የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳላዲን ሰይድ በ56ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ አሸንፏል።

    በሊጉ 12ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ተጫውቶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

    ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተክሉ ተስፋዬ በ27ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችልም ሳሙኤል ሳኑሚ በ48ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያ ቡናን አቻ አድርጓል።

    የ27ኛው ሳምንት መርሃ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ሰኞ አዲስ አበባ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ወላይታ ዲቻን ያስተናግዳል።

    ትናንት በተደረጉ የሊጉ መርሃ ግብሮች መከላከያ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ፥ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ መጠናቀቁ ይታወሳል።
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ደደቢት እና ሀዋሳ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል። ደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም ፋሲል ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል። ለደደቢት ሁለቱንም ግቦች ጌታነህ ከበደ ሲያስቆጥር ለፋሲል ኤደም ኮድዞ ከመረብ አዋህዷል። ሀዋሳ ከተማም በተመሳሳይ ወልዲያ ከተማን 2 ለ 1 የረታ ሲሆን፥ ፍሬው ሰለሞን እና ጃኮ አራፋት የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። ለወልዲያ ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ አንዱአለም ንጉሴ ማስቆጠር ችሏል። አርባ ምንጭ ከተማ ከአዳማ ከተማ ያደረጉት ያለው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቋል። ጅማ ላይ ከጅማ አባቡና ጋር ጨዋታውን ያደረገው የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳላዲን ሰይድ በ56ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ አሸንፏል። በሊጉ 12ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ተጫውቶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል። ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተክሉ ተስፋዬ በ27ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችልም ሳሙኤል ሳኑሚ በ48ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያ ቡናን አቻ አድርጓል። የ27ኛው ሳምንት መርሃ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ሰኞ አዲስ አበባ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ወላይታ ዲቻን ያስተናግዳል። ትናንት በተደረጉ የሊጉ መርሃ ግብሮች መከላከያ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ፥ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ መጠናቀቁ ይታወሳል።
    0 Comments 0 Shares
  • በሀድያ ሆሳዕና ላይ የተጣለው የ6 ነጥቦች ቅነሳ ተነሳ

    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀድያ ሆሳዕና በፌዴሬሽኑ የተጣለበት የስድስት ነጥብ ቅነሳ ቅጣት ተነሳለት።

    የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ ከሁለት ሳምንት በፊት ባስተላለፈው ውሳኔ፥ የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ሀድያ ሆሳዕና ደጋፊዎች በተደጋጋሚ በፈጸሙት የዲሲፕሊን ጥሰት ቡድኑ ከሰበሰበው ነጥብ ላይ ስድስት ነጥቦች እንዲቀነሱበት ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው።

    ከቅጣት ውሳኔው በኋላ ሀድያ ሆሳዕና ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን ጉዳዩን ያየው የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴም ቅጣቱን መሻሩ ታውቋል፡፡

    በዚህም ሀድያ ሆሳዕና ከነበረው 30 ነጥብ ላይ የተቀነሰው ስድስት ነጥብ ተጨምሮለት ነጥቡን ወደ 36 በማድረስ ከመሪዎቹ ጅማ ከተማ እና ሀላባ ከተማ ጋር በነጥብ መስተካከል ችሏል።

    ሀድያ ሆሳዕና ነጥቡ ቢመለስለትም በምትኩ ሌላ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡

    በቀጣይ በአቢዮ አርሳሞ ስታዲየም የሚያደርጋቸው ሁለት ጨዋታዎችንም ያለ ደጋፊ በዝግ ስታዲየም እንዲያካሂድ ተወስኖበታል ብሏል የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ።
    በሀድያ ሆሳዕና ላይ የተጣለው የ6 ነጥቦች ቅነሳ ተነሳ አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀድያ ሆሳዕና በፌዴሬሽኑ የተጣለበት የስድስት ነጥብ ቅነሳ ቅጣት ተነሳለት። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ ከሁለት ሳምንት በፊት ባስተላለፈው ውሳኔ፥ የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ሀድያ ሆሳዕና ደጋፊዎች በተደጋጋሚ በፈጸሙት የዲሲፕሊን ጥሰት ቡድኑ ከሰበሰበው ነጥብ ላይ ስድስት ነጥቦች እንዲቀነሱበት ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው። ከቅጣት ውሳኔው በኋላ ሀድያ ሆሳዕና ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን ጉዳዩን ያየው የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴም ቅጣቱን መሻሩ ታውቋል፡፡ በዚህም ሀድያ ሆሳዕና ከነበረው 30 ነጥብ ላይ የተቀነሰው ስድስት ነጥብ ተጨምሮለት ነጥቡን ወደ 36 በማድረስ ከመሪዎቹ ጅማ ከተማ እና ሀላባ ከተማ ጋር በነጥብ መስተካከል ችሏል። ሀድያ ሆሳዕና ነጥቡ ቢመለስለትም በምትኩ ሌላ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡ በቀጣይ በአቢዮ አርሳሞ ስታዲየም የሚያደርጋቸው ሁለት ጨዋታዎችንም ያለ ደጋፊ በዝግ ስታዲየም እንዲያካሂድ ተወስኖበታል ብሏል የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ።
    0 Comments 0 Shares
  • 10 የተሽከርካሪ ምርመራና አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ተዘጉ

    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 10 የተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማትና አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት መዘጋታቸውን የትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል።

    ተቋማቱ እንዲዘጉ የተደረገው በአቅም ማነስ፣ ግብአት አለመሟላት እና የስነ ምግባር መጓደል ምክንያት መሆኑንም ባለስልጣኑ ገልጿል።

    የትራንስፖርት ባለስልጣን እንዳስታወቀው፥ በአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ፣ በተሽከርካሪ የምርመራ ተቋማት እና የመንጃ ፍቃድ አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

    የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ኃይለማርያም፥ በየጊዜው ቅሬታ የሚነሳባቸውን ቸግሮች ከግምት ያስገባ የህግ ማሻሻያ እቅድ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

    በተለይ በየጊዜው የሚደረጉ ቁጥጥሮችን ከማጠናከር እና እርምጃዎችን ከመውሰድ በተጨማሪ አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት።

    እስካሁንም ባለስልጣኑ በአቅም ማነስ፣ ግብአት አለመሟላት እና የስነምግባር መጓደል ምክንያት 10 የተሽከርካሪ ምርመራ እና አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲዘጉ አድርጓል ብለዋል።

    ከዚህ በተጨማሪም የአመለካከት ችግርን ለመቅረፍ ከ400 በላይ አሰልጣኝ መምህራን የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ጠቁመዋል።
    10 የተሽከርካሪ ምርመራና አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ተዘጉ አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 10 የተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማትና አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት መዘጋታቸውን የትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል። ተቋማቱ እንዲዘጉ የተደረገው በአቅም ማነስ፣ ግብአት አለመሟላት እና የስነ ምግባር መጓደል ምክንያት መሆኑንም ባለስልጣኑ ገልጿል። የትራንስፖርት ባለስልጣን እንዳስታወቀው፥ በአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ፣ በተሽከርካሪ የምርመራ ተቋማት እና የመንጃ ፍቃድ አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ነው። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ኃይለማርያም፥ በየጊዜው ቅሬታ የሚነሳባቸውን ቸግሮች ከግምት ያስገባ የህግ ማሻሻያ እቅድ ተዘጋጅቷል ብለዋል። በተለይ በየጊዜው የሚደረጉ ቁጥጥሮችን ከማጠናከር እና እርምጃዎችን ከመውሰድ በተጨማሪ አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት። እስካሁንም ባለስልጣኑ በአቅም ማነስ፣ ግብአት አለመሟላት እና የስነምግባር መጓደል ምክንያት 10 የተሽከርካሪ ምርመራ እና አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲዘጉ አድርጓል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም የአመለካከት ችግርን ለመቅረፍ ከ400 በላይ አሰልጣኝ መምህራን የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ጠቁመዋል።
    0 Comments 0 Shares
  • የፖላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አንድሬ ዱዳ አዲስ አበባ ገቡ

    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፖላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አንድሬ ሴባስቲያን ዱዳ በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

    ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክሩ ይሆናል።

    የፖላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ ማመቻቸት የጉብኝታቸው አንድ አካል መሆኑ ተገልጿል።

    ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ
    ጉብኝቱ ፖላንድ በፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት ከአፍሪካ ድጋፍ ለማሰባሰብ እንደሚያግዛትም ነው የተነገረው።

    ፕሬዚዳንት ዱዳ በኢትዮጵያ የሶሰት ቀናት ቆይታ አንደሚኖራቸው የተገለፀ ሲሆን፥ በቆይታቸው በፖላንዳውያን የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችን ይጎበኛሉ ተብሏል።

    ፕሬዚዳንቱ በኢትዮ-ፖሊሽ የንግድ ግንኙነት ጉባኤ ላይ እንደሚገኙም ተጠቅሷል።
    የፖላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አንድሬ ዱዳ አዲስ አበባ ገቡ አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፖላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አንድሬ ሴባስቲያን ዱዳ በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክሩ ይሆናል። የፖላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ ማመቻቸት የጉብኝታቸው አንድ አካል መሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ ጉብኝቱ ፖላንድ በፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት ከአፍሪካ ድጋፍ ለማሰባሰብ እንደሚያግዛትም ነው የተነገረው። ፕሬዚዳንት ዱዳ በኢትዮጵያ የሶሰት ቀናት ቆይታ አንደሚኖራቸው የተገለፀ ሲሆን፥ በቆይታቸው በፖላንዳውያን የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችን ይጎበኛሉ ተብሏል። ፕሬዚዳንቱ በኢትዮ-ፖሊሽ የንግድ ግንኙነት ጉባኤ ላይ እንደሚገኙም ተጠቅሷል።
    0 Comments 0 Shares