• በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር አዲስአበባ ስታዲየም ላይ ወልዋሎ ዓ.ዩ እና ወልዲያ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

    ወልዋሎ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ጅማ አቅንቶ በጅማ አባጅፋር 3-0 ከተረታው የቡድን ስብስብ ውስጥ ተከላካዩ ሮቤል ግርማን በተከላካይ አማካዩ ብርሃኑ አሻሞ ፣ በጉዳት በዛሬው ጨዋታ ላይ ያልነበረው አጥቂውን ሙሉአለም ጥላሁንን በእዮብ ወልደማርያም እንዲሁም ግብጠባቂው በረከት አማረን በዘውዱ መስፍን በመተካት በተመሳሳይ የ4-3-3 ቅርጽ ጨዋታውን ጀምረዋል፡፡ በአንጻሩ ወልዲያ ባሳለፍነው ሳምንት በሜዳው አርባምንጭ ከተማን 2-0 ከረታው የቡድን ስብስብ ውስጥ በተመሳሳይ የ4-3-3 ቅርፅ የፊት አጥቂውን አንዱአለም ንጉሴን ብቻ በኤደሞ ኮድዞ በመተካት ጨዋታውን ጀምረዋል፡፡

    በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ፍፁም የሆነ የኳስ ቁጥጥር እንዲሁም ከተጋጣሚያቸው በተሻለ የግብ ሙከራዎችን የማድረግ ብልጫ መውሰድ የቻሉት ወልዋሎዎች የመጀመሪያ አስደንጋጭ ሙከራቸውን ለማድረግ የፈጀባቸው 3 ደቂቃዎች ነበሩ። የመስመር አጥቂው ከድር ሳሊህ በፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ የተገኘችውን ኳስ 2 የወልዲያ ተከላካዮች ለ4 የወልዋሎ ተጫዋቾች ሆነው ያገኘውን አጋጣሚ በቀላሉ ለቤሌንጌ ያሳቀፈው ኳስ የመጀመሪያ ሙከራቸው ነበረች፡፡

    የወልዋሎዎች ጠንካራ የማጥቃት አማራጭ በሆነውና የመስመር አጥቂው ፕሪንስ ሴቪሪንሆ ዋንኛ ተዋናይ በሆነበት የወልዋሎዎች የቀኝ መስመር በኩል ባጋደለ መልኩ ጥቃቶችን በተደጋጋሚ ሲሰነዝሩ የነበሩ ሲሆን በተለይም በ10ኛውና በ14ኛው ደቂቃ ፕሪንስ ከቀኝ መስመር አደገኛ ኳሶችን ወደ ሳጥን ውስጥ ቢጥልም እዮብ ወልደማርያም ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል፡፡

    የወልዲያ ሁለቱ የመስመር አጥቂዎች እንዲሁም ከተከላካይ አማካዩ ዳንኤል ደምሴ ፊት የነበሩት ሁለቱ አማካዮች ቡድኑ ከማጥቃት ወደ መከላከል በሚያደርገው ሽግግር ላይ ያላቸው እጅግ ዘገምተኛ ሽግግር የወልዲያን የተከላካይ ክፍል በእጅጉ ተጋላጭ ሆኖ ተስተውሏል፡፡ በአንጻሩ በወልዋሎዎች በኩል እንደወትሮው ሁሉ ጠበብ ባለ የቦታ አያያዝ የሚጫወቱት ሶስቱ አማካዮች እንዲሁም ሁለቱ የመስመር አጥቂዎች በወልዲያ የተከላካይና የአማካይ መስመሮች መካከል የነበሩትን እጅግ ሰፋፊ ክፍተቶችን በጥቂት አጋጣሚዎች እዮብ ተጎድቶ እስኪወጣ ድረስ ካደረጋቸው የተወሰኑ ጥረቶች በስተቀር በአግባቡ መጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡

    ፈጥን ባለ የማጥቃት እንቅስቃሴ ወደተጋጣሚያቸው የግብ ክልል መድረሳቸውን የቀጠሉት ወልዋሎዎች በደቂቃዎች ልዩነት አከታትለው አስደንጋጭ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል፡፡ በ24ኛው ደቂቃ መኩሪያ ደሱ ከሳጥን ውጪ አክርሮ ወደ ግብ የላካት በወልዲያው የመሀል ተከላካይ ስትመለስ በቅርብ ርቀት የነበረው አፍወርቅ ሀይሉ በድጋሚ ወደ ግብ የላካት ኳስ በሚያስገርም ሁኔታ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል። ከአንድ ደቂቃ በኃላ ደግሞ ወደ መሀል ሜዳ ተጠግተው ለመከላካል ሲሞክሩ የነበሩት የወልዲያ ተከላካዮች ባልተደራጁበት ሁኔታ በቀጥታ ከተከላካዮች የተላከውን ኳስ ተጠቅሞ እዮብ ወልደማርያም ከኤሚክሬል ቤሊንጌ ጋር 1ለ1 ተገናኝቶ በግብ ጠባቂው አናት በላይ ለማስቆጠር የሞከረውን ኳስ ቤሌንጌ ለጥቂት አድኖበታል፡፡ ከዚች ሙከራ በኃላ ጉዳት ያስተናገደ የሚመስለው አጥቂው እዮብ ወልደማርያም በ28ኛው ደቂቃ ላይ በቢኒያም አየለ ተቀይሮ ከሜዳ ለመውጣት ተገዷል፡፡ እዮብ ከወጣበት ደቂቃ አንስቶም ወልዋሎዎች ወደ ማጥቃት ሂደት ሲገቡ የነበራቸው አስፈሪነት ቀንሶ ተስተውሏል፡፡
    በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር አዲስአበባ ስታዲየም ላይ ወልዋሎ ዓ.ዩ እና ወልዲያ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ወልዋሎ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ጅማ አቅንቶ በጅማ አባጅፋር 3-0 ከተረታው የቡድን ስብስብ ውስጥ ተከላካዩ ሮቤል ግርማን በተከላካይ አማካዩ ብርሃኑ አሻሞ ፣ በጉዳት በዛሬው ጨዋታ ላይ ያልነበረው አጥቂውን ሙሉአለም ጥላሁንን በእዮብ ወልደማርያም እንዲሁም ግብጠባቂው በረከት አማረን በዘውዱ መስፍን በመተካት በተመሳሳይ የ4-3-3 ቅርጽ ጨዋታውን ጀምረዋል፡፡ በአንጻሩ ወልዲያ ባሳለፍነው ሳምንት በሜዳው አርባምንጭ ከተማን 2-0 ከረታው የቡድን ስብስብ ውስጥ በተመሳሳይ የ4-3-3 ቅርፅ የፊት አጥቂውን አንዱአለም ንጉሴን ብቻ በኤደሞ ኮድዞ በመተካት ጨዋታውን ጀምረዋል፡፡ በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ፍፁም የሆነ የኳስ ቁጥጥር እንዲሁም ከተጋጣሚያቸው በተሻለ የግብ ሙከራዎችን የማድረግ ብልጫ መውሰድ የቻሉት ወልዋሎዎች የመጀመሪያ አስደንጋጭ ሙከራቸውን ለማድረግ የፈጀባቸው 3 ደቂቃዎች ነበሩ። የመስመር አጥቂው ከድር ሳሊህ በፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ የተገኘችውን ኳስ 2 የወልዲያ ተከላካዮች ለ4 የወልዋሎ ተጫዋቾች ሆነው ያገኘውን አጋጣሚ በቀላሉ ለቤሌንጌ ያሳቀፈው ኳስ የመጀመሪያ ሙከራቸው ነበረች፡፡ የወልዋሎዎች ጠንካራ የማጥቃት አማራጭ በሆነውና የመስመር አጥቂው ፕሪንስ ሴቪሪንሆ ዋንኛ ተዋናይ በሆነበት የወልዋሎዎች የቀኝ መስመር በኩል ባጋደለ መልኩ ጥቃቶችን በተደጋጋሚ ሲሰነዝሩ የነበሩ ሲሆን በተለይም በ10ኛውና በ14ኛው ደቂቃ ፕሪንስ ከቀኝ መስመር አደገኛ ኳሶችን ወደ ሳጥን ውስጥ ቢጥልም እዮብ ወልደማርያም ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል፡፡ የወልዲያ ሁለቱ የመስመር አጥቂዎች እንዲሁም ከተከላካይ አማካዩ ዳንኤል ደምሴ ፊት የነበሩት ሁለቱ አማካዮች ቡድኑ ከማጥቃት ወደ መከላከል በሚያደርገው ሽግግር ላይ ያላቸው እጅግ ዘገምተኛ ሽግግር የወልዲያን የተከላካይ ክፍል በእጅጉ ተጋላጭ ሆኖ ተስተውሏል፡፡ በአንጻሩ በወልዋሎዎች በኩል እንደወትሮው ሁሉ ጠበብ ባለ የቦታ አያያዝ የሚጫወቱት ሶስቱ አማካዮች እንዲሁም ሁለቱ የመስመር አጥቂዎች በወልዲያ የተከላካይና የአማካይ መስመሮች መካከል የነበሩትን እጅግ ሰፋፊ ክፍተቶችን በጥቂት አጋጣሚዎች እዮብ ተጎድቶ እስኪወጣ ድረስ ካደረጋቸው የተወሰኑ ጥረቶች በስተቀር በአግባቡ መጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ፈጥን ባለ የማጥቃት እንቅስቃሴ ወደተጋጣሚያቸው የግብ ክልል መድረሳቸውን የቀጠሉት ወልዋሎዎች በደቂቃዎች ልዩነት አከታትለው አስደንጋጭ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል፡፡ በ24ኛው ደቂቃ መኩሪያ ደሱ ከሳጥን ውጪ አክርሮ ወደ ግብ የላካት በወልዲያው የመሀል ተከላካይ ስትመለስ በቅርብ ርቀት የነበረው አፍወርቅ ሀይሉ በድጋሚ ወደ ግብ የላካት ኳስ በሚያስገርም ሁኔታ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል። ከአንድ ደቂቃ በኃላ ደግሞ ወደ መሀል ሜዳ ተጠግተው ለመከላካል ሲሞክሩ የነበሩት የወልዲያ ተከላካዮች ባልተደራጁበት ሁኔታ በቀጥታ ከተከላካዮች የተላከውን ኳስ ተጠቅሞ እዮብ ወልደማርያም ከኤሚክሬል ቤሊንጌ ጋር 1ለ1 ተገናኝቶ በግብ ጠባቂው አናት በላይ ለማስቆጠር የሞከረውን ኳስ ቤሌንጌ ለጥቂት አድኖበታል፡፡ ከዚች ሙከራ በኃላ ጉዳት ያስተናገደ የሚመስለው አጥቂው እዮብ ወልደማርያም በ28ኛው ደቂቃ ላይ በቢኒያም አየለ ተቀይሮ ከሜዳ ለመውጣት ተገዷል፡፡ እዮብ ከወጣበት ደቂቃ አንስቶም ወልዋሎዎች ወደ ማጥቃት ሂደት ሲገቡ የነበራቸው አስፈሪነት ቀንሶ ተስተውሏል፡፡
    Like
    3
    0 Comments 0 Shares
  • ከኮሜዲያኖች ጋር የተደረገ አዝናኝ የገና በዓል ዝግጅት
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • እስላም እና ክርስቲያኑ በአንድነት የገናን በዓል ሲያከብሩ፤ ወሎ የፍቅር ሀገር
    Like
    2
    0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • Ethiopia: ልጅ ያሬድ ተመልካቹን በስድብ ያጥረገረገበት እጅግ አስገራሚ የበአል ዝግጅት
    Like
    3
    0 Comments 0 Shares
  • Ethiopia: የሟች ኢብራሒም ሻፊ ቤተሰቦች በለቅሶ ቤት ለፍቅር ቀጠሮ ብቻ የተናገሩት ልብ የሚነካ መልእክት
    Ethiopia: የሟች ኢብራሒም ሻፊ ቤተሰቦች በለቅሶ ቤት ለፍቅር ቀጠሮ ብቻ የተናገሩት ልብ የሚነካ መልእክት
    Like
    4
    0 Comments 1 Shares
  • Ethiopia: ለቴዲ አፍሮ ብቻ አይደለም ለኔም ሕይወቴ ነዉ! ጌታቸዉ ካሳ ከመዓዛ ብሩ ጋር በሸገር የጨዋታ እንግዳ
    Ethiopia: ለቴዲ አፍሮ ብቻ አይደለም ለኔም ሕይወቴ ነዉ! ጌታቸዉ ካሳ ከመዓዛ ብሩ ጋር በሸገር የጨዋታ እንግዳ
    Like
    4
    0 Comments 1 Shares