ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ በኩባ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ፕሬዚዳንቱ ለጉብኝት ወደ ኩባ ያቀኑት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ራውል ካስትሮ ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት ነው።
ፕሬዚዳንት ሙላቱ በተለይ ሁለቱ አገሮች በትምህርት፣ በጤናና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከኩባ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
በተያያዘ ዜና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዛሬ ገብተዋል።
በነገው ዕለትም ከአገሪቱ አቻቸው ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን እንዲሁም ከሰራተኛና የሰው ኃብት ሚኒስትር ጋር የሁለቱን አገሮች የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ በመግለጫው ተመልክቷል።