0 Comments
0 Shares
Directory
-
Please log in to like, share and comment!
-
AMHARIC.VOANEWS.COMእስራኤል በጥቅምቱ ጥቃት ከተሳተፉ የሐማስ ታጣቂዎች አንዱን መግደሏን አስታወቀችየእስራኤል የጦር ኃይል በጎርጎርሳዊያኑ ጥቅምት ሰባት ሓማስ ባደረሰው ጥቃት ላይ በቪዲዮ ምስል የሚታይ የቡድኑን ታጣቂ መግደሉን አስታወቀ፡፡ የጦር ኃይል የእስራኤል የጦር ኃይል ዛሬ ማክሰኞ እንዳስታወቀው የተገደለው የሐማስ ታጣቂ አባታቸው በቦንብ ጥቃት የተገደለባቸው ሁለት የቆሰሉ ህጻናት ፊት ለስላሳ መጠጥ ሲጠጣ በቪዲዮ ምስሉ በሰፊው የሚታየው ነው፡፡ የእስራኤል መከላከያ ኃይል ታጣቂው በጥቅምቱ ጥቃት ወቅት በአየር መብረሪያ ፓራግላይደር ወደ ኔቲቭ ኻሳራ መንደር...0 Comments 0 Shares -
AMHARIC.VOANEWS.COMየዩጋንዳ ተቃዋሚ መሪ ቦቢ ዋይን በጥይት መመታቱን ፓርቲው አስታወቀበዩጋንዳ ለበርካታ ዓመታት ስልጣን ላይ ያሉትን ፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒን በመቃወም፤ ቀዳሚ የሆነው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ቦቢ ዋይን ዛሬ ማክሰኞ ዋና ከተማዋ ካምፓላ ሰሜናዊ ዳርቻ በደህንነት አባላት በተተኮሰ ጥይት እግሩን መመታቱን ፓርቲው አስታውቋል። ከፖፕ ሙዚቃ ወደ ፖለቲካ ፊቱን ያዞረው እና በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን የተባለው ሮበርት ኪያጉላኒ በጎርጎርሳዊያኑ 2021 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዩጋንዳን ለአራት አስርት ዓመታት ያህል የመሩትን ሙሴቬኒን በመከተል...0 Comments 0 Shares -
AMHARIC.VOANEWS.COMበጎንደር ከተማ በአጋቾች የተወሰደችው የ2 ዓመት ህፃን ግድያ ቁጣ ቀሰቀሰበድጋሚ የታደሰ በጎንደር ከተማ ባለፈው አርብ ባልታወቁ ሰዎች ታግታ ከተወሰደች በኋላ ግማሽ ሚልየን ብር ተጠይቆባት የነበረችው የ2 አመት ህፃን በትላንትው እለት መገደሏ ከተሰማ ወዲህ በከተማው ነዋሪዎች ዘንድ ቁጣ ቀስቅሷል፡፡ አጋቾቹ ህፃኗን የገደሏት ወላጆቿ በድርድር እንዲከፍሉ የጠየቁትን 300 ሺ ብር ከተቀበሉ በኋላ ነው:: ዜናውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው ቁጣቸውን አሰምተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን...0 Comments 0 Shares -
AMHARIC.VOANEWS.COMባንክ ሂሳቡ እንዳይንቀሳቀስ መታገድ የአስመራ በረራውን ለማቋረጡ 'አንዱ ምክኒያት ነው' የኢትዮጵያ አየር መንገድየኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የባንክ ሒሳቡ እንዳያንቀሳቅስ በኤርትራ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን በመታገዱ የአስመራ በረራውን ማቋረጡን አስታወቀ፡፡ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሠው በሰጡት መግለጫ፣ የኤርትራ ሲቪል አቭዬሽን ባለሥልጣን ቀደም ብሎ ስላስተላለፈው የበረራ እገዳ ውሳኔም ሆነ ቀጥሎ በመጣው የባንክ ሒሳብ እግድ ጉዳይ ዙሪያ ለመወያየትም ሆነ ለማብራራት ፈቃደኛ አልሆነም ብለዋል፡፡ በዚህ የተነሳም አየር መንገዱ ‘ከዛሬ ጀምሮ የአስመራ...0 Comments 0 Shares -
AMHARIC.VOANEWS.COMበማረቆ ልዩ ወረዳ እና የመስቃን ቤተ ጉራጌ ግጭቶች ሳቢያ የሰላማዊ ሰዎች ግድያ መቀጠሉ ተገለጸበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ እና በማረቆ ልዩ ወረዳ መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያ ካለፈው አርብ እስከ ትላንት በስቲያ እሁድ በነበረው ጊዜ ውስጥ 12 ሰዎች መገደላቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ነዋሪዎች አስታወቁ:: የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እንዳሻው ጣሰው በአከባቢዎቹ ላለው የፀጥታ ችግሮችና ሰላማዊ ሰዎች ጥቃት የወረዳዎቹ አመራሮች እጅ እንዳለበት ጠቅሰው የተጠረጠሩም እየታሠሩ መኾናቸውን...0 Comments 0 Shares -
AMHARIC.VOANEWS.COMየምርጫ ተአማኒነትን በተመለከተ ያለው ጥርጣሬ፣ ውጥረት እንዳያባብስ አስግቷልበአሜሪካ የሚገኙ ሁለቱ ዋና ፓርቲዎች “የምርጫ ተአማኒነትን” በተመለከተ የሚያሳስቧቸው ጉዳዮች እንዳሉ በመግለጽ ላይ ናቸው። የምዝገባ፣ የድምጽ መስጠት፣ የድምጽ ቆጠራ፣ ቆጠራውን ማረጋጥ እንዲሁም ችግር ቢከሰት መፍትሄ መሻትን የመሰሉ ጉዳዮች በተገቢው መንገድ መካሄዳቸውን በተመለከተ የሚያሳስቧቸው ጉዳዮች አሉ።0 Comments 0 Shares -
AMHARIC.VOANEWS.COMበናይጄሪያ በሀገር ክህደት የተከሰሱ 10 የመንግሥት ተቃዋሚዎች ፍርድ ቤት ቀረቡበናይጄሪያ በተከሰተው የኑሮ ውድነት ምክንያት ባለፈው ወር ከተቀሰቀሰው ፀረ-መንግስት ተቃውሞ ጋር በተያያዘ 10 ሰዎች በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሰው ትላንት ሰኞ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ተከሳሾቹ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ የሞት ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወገዘውን ይህን የክስ ጉዳይ አስመልክቶ ቲሞቲ ኦቢዙ ከአቡጃ ተከታዩን ዘግቧል ደረጀ ደስታ ወደ አማርኛ መልሶታል፡፡0 Comments 0 Shares