• Get ready everyone for yet another cultural journey brought to you by Afrikaweyan Radio Sheger FM!! This time we travel through the Sahara Desert and bring you live shows by ANEWAL: Tuareg Desert Blues music. ANEWAL is coming to Addis to celebrate our Second Annual African Freedom Day celebration!!!!
    Friday: Hiber Cultural Resturant @ 8:00
    NOT TO BE MISSED!!!
    entrance: only birr
    Get ready everyone for yet another cultural journey brought to you by Afrikaweyan Radio Sheger FM!! This time we travel through the Sahara Desert and bring you live shows by ANEWAL: Tuareg Desert Blues music. ANEWAL is coming to Addis to celebrate our Second Annual African Freedom Day celebration!!!! Friday: Hiber Cultural Resturant @ 8:00 NOT TO BE MISSED!!! entrance: only birr
    0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • ማንቼስተር ዩናይትድ የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ ሆነ
    አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩሮፓ ሊግ በእንግሊዙ ማንቼስተር ዩናይትድ አሸናፊነት ተጠናቋል።

    የላንክሻየሩ ክለብ ትናንት ምሽት በስዊድን ፍሬንድስ አሬና በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ፥ የሆላንዱን አያክስ አምስተርዳምን 2 ለ 0 አሸንፏል።

    ፖል ፖግባ ከዕረፍት በፊት ሄንሪክ ሚኪታሪያን ደግሞ ከእረፍት መልስ የድል ጎሎችን ለማንቼስተር ዩናይትድ አስቆጥረዋል።

    ድሉን ተከትሎም ማንቼስተር በትልቁ የአውሮፓ የክለቦች ውድድር በሆነው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ በቀጥታ መግባቱን አረጋግጧል።

    በምሽቱ ጨዋታ በወጣቶች የተሞላው አያክስ አምስተርዳም በኳስ ቁጥጥር ሙሉውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የተሻለ ነበር።

    የልምድ ማነስ እና የመሃል ሜዳውን የኳስ ቁጥጥር በሶስተኛው የሜዳ ክፍል መድገም አለመቻላቸው ግን የማንቼስተርን መረብ እንዳይደፍሩ አድርጓቸዋል።

    ልምዳቸውን የተጠቀሙት ማንቸስተሮችም ወደ ትልቁ የአውሮፓ የክለቦች ውድድር መድረክ ለመመለስ ያደረጉት ጥረት ተሳክቶላቸዋል።

    አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆም በአውሮፓ መድረክ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ያሳኩትን ድል አራት ማድረስ ችለዋል።

    ከፖርቶ ጋር የቀድሞውን የማህበረሰብ (አሁን ዩሮፓ ሊግ) እና የቻምፒየንስ ሊግ፣ ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ጋር ደግሞ ቻምፒየንስ ሊግን ሲያነሱ ትናንት ምሽት አራተኛውን ዋንጫ ከማንቼስተር ጋር በስቶኮልም አሳክተዋል።

    ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሁለት የቻምፒየንስ ሊግ እና ሁለት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን በማንሳትም ብቸኛው አሰልጣኝ ሆነዋል።

    ከጨዋታው በፊት በማንቼስተር ተዘጋጅቶ በነበረው የሙዚቃ ድግስ ላይ በደረሰው ጥቃት ለሞቱ ንጹሃን ዜጎች የህሊና ፀሎት ተደርጓል።

    ከዚህ ባለፈም ማንቼስተር ዩናይትድ በጨዋታው ጥቁር ጨርቅ የተጫዋቾች ክንድ ላይ በማሰር ገብቷል።

    በርካታ የክለቡ ደጋፊዎችም ተጫዋቾች ለከተማዋ መጽናኛ የሚሆነውን ድል ያስመዘግቡ ዘንድ የሚጠይቅ ባነር ይዘው ወደ ስታዲየም ገብተዋል።

    ከድሉ በኋላም የማንቼስተር ተጫዋቾች የማንቼስተርን አንድነት የሚገልጽ ባነር በመያዝ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

    ማንቼስተር ዩናይትድ በአውሮፓ የክለቦች ውድድር ሶስት ትልልቅ ዋንጫዎችን በማንሳት አምስተኛው ክለብ ሆኗል።

    የተሰረዘውን ካፕ ዊነርስ ካፕ፣ ቻምፒየንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግን በማሸነፍ፥ አያክስ፣ ባየር ሙኒክ፣ ቼልሲ እና ጁቬንቱስ ብቸኛዎቹ ክለቦች ነበሩ።

    ትናንት ምሽት ይህን ማሳካት የቻለው ማንቼስተርም የአራቱን ክለቦች ጎራ መቀላቀል ችሏል።
    ማንቼስተር ዩናይትድ የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ ሆነ አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩሮፓ ሊግ በእንግሊዙ ማንቼስተር ዩናይትድ አሸናፊነት ተጠናቋል። የላንክሻየሩ ክለብ ትናንት ምሽት በስዊድን ፍሬንድስ አሬና በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ፥ የሆላንዱን አያክስ አምስተርዳምን 2 ለ 0 አሸንፏል። ፖል ፖግባ ከዕረፍት በፊት ሄንሪክ ሚኪታሪያን ደግሞ ከእረፍት መልስ የድል ጎሎችን ለማንቼስተር ዩናይትድ አስቆጥረዋል። ድሉን ተከትሎም ማንቼስተር በትልቁ የአውሮፓ የክለቦች ውድድር በሆነው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ በቀጥታ መግባቱን አረጋግጧል። በምሽቱ ጨዋታ በወጣቶች የተሞላው አያክስ አምስተርዳም በኳስ ቁጥጥር ሙሉውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የተሻለ ነበር። የልምድ ማነስ እና የመሃል ሜዳውን የኳስ ቁጥጥር በሶስተኛው የሜዳ ክፍል መድገም አለመቻላቸው ግን የማንቼስተርን መረብ እንዳይደፍሩ አድርጓቸዋል። ልምዳቸውን የተጠቀሙት ማንቸስተሮችም ወደ ትልቁ የአውሮፓ የክለቦች ውድድር መድረክ ለመመለስ ያደረጉት ጥረት ተሳክቶላቸዋል። አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆም በአውሮፓ መድረክ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ያሳኩትን ድል አራት ማድረስ ችለዋል። ከፖርቶ ጋር የቀድሞውን የማህበረሰብ (አሁን ዩሮፓ ሊግ) እና የቻምፒየንስ ሊግ፣ ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ጋር ደግሞ ቻምፒየንስ ሊግን ሲያነሱ ትናንት ምሽት አራተኛውን ዋንጫ ከማንቼስተር ጋር በስቶኮልም አሳክተዋል። ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሁለት የቻምፒየንስ ሊግ እና ሁለት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን በማንሳትም ብቸኛው አሰልጣኝ ሆነዋል። ከጨዋታው በፊት በማንቼስተር ተዘጋጅቶ በነበረው የሙዚቃ ድግስ ላይ በደረሰው ጥቃት ለሞቱ ንጹሃን ዜጎች የህሊና ፀሎት ተደርጓል። ከዚህ ባለፈም ማንቼስተር ዩናይትድ በጨዋታው ጥቁር ጨርቅ የተጫዋቾች ክንድ ላይ በማሰር ገብቷል። በርካታ የክለቡ ደጋፊዎችም ተጫዋቾች ለከተማዋ መጽናኛ የሚሆነውን ድል ያስመዘግቡ ዘንድ የሚጠይቅ ባነር ይዘው ወደ ስታዲየም ገብተዋል። ከድሉ በኋላም የማንቼስተር ተጫዋቾች የማንቼስተርን አንድነት የሚገልጽ ባነር በመያዝ አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ማንቼስተር ዩናይትድ በአውሮፓ የክለቦች ውድድር ሶስት ትልልቅ ዋንጫዎችን በማንሳት አምስተኛው ክለብ ሆኗል። የተሰረዘውን ካፕ ዊነርስ ካፕ፣ ቻምፒየንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግን በማሸነፍ፥ አያክስ፣ ባየር ሙኒክ፣ ቼልሲ እና ጁቬንቱስ ብቸኛዎቹ ክለቦች ነበሩ። ትናንት ምሽት ይህን ማሳካት የቻለው ማንቼስተርም የአራቱን ክለቦች ጎራ መቀላቀል ችሏል።
    0 Comments 0 Shares
  • WWW.FANABC.COM
    FBC - ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲችን በድጋሚ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
    አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ሰርቢያዊው አሰልጣኝ ድራገን ፖፓዲችን በድጋሚ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ። ኢትዮጵያ ቡና በ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቡን የሚመሩትን አሰልጣኝ በት...
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጨዋታ ህጻናት በተፈጥሮ የሚከውኑት ተግባር ሲሆን፥ ወላጆችም ይህንን ተግባራቸውን ሊያበረታቱት እንደሚገባ ይነገራል።

    “ህጻናት በተፈጥሮ የመጫወት ፍላጎት አላቸው፤ ይህም በስነ ህይወት የተዘጋጀላቸው መርሃ ግብር ነው” የሚሉት የእንግሊዝ ቻሪቲ ፕሌይ ሊቀመንብር ኒኮላ በትለር፥ “ጨዋታ

    ሰዎች እና ሌሎች አጥቢ እንስሳቶች አዳዲስ ነገሮችን የሚማሩበት መንገድ ነው” ብለዋል።

    እንደ ወላጅ፥ ሁላችንም ለልጆቻችን ሙሉ በሙሉ የመጫወት ነጻነት መስጠት አለብን፤ ምክንያቱ ደግሞ ህፃናት ስለ ራሳቸው እና አካባቢያቸው ስላለው ዓለም የሚማሩት በጫተዋ ስለሆነ ነው።

    በጫወታ ወቅት ህጻናት ነገሮችን የመረዳት አቅማቸው እና በራስ መተማመናቸው ቀጥለው በተዘረዘሩ አራት ነጥቦች ዙሪያ ይጨጠምራት ተብሏል።

    1 አካላዊ፦ ጥንካሬ፣ ሚዛን መጠበቅ እና ሌሎች መሰል አካላዊ ክህሎቶችን በጫወታ ወቅት ያዳብራሉ።

    2 ማህበራዊ እና ርህራሄ፦ ነገሮችን ማመዛዘን፣ ማዘዝ፣ ያላቸውን ከሰዎች ጋር መካፈል እና ተራ መጠበቅን ይማራሉ።

    3 የፈጠራ እና የአስተሳሰብ አቅም፦ ህጻናት በጨዋታ ወቅት የሚያደርጓቸው ነገሮች የአስተሳሰብ እና የፈጠራ እቀማቸውን ይጨምራል።

    4 ቋንቋ እና መግባባት፦ በጨዋታ ወቅት የህፃናት የመናገር፣ ትእዛዝ የመቀበል፣ ከሰዎች ጋር የመግባባት እና ሌሎች ክህሎቶች ይጨምራሉ።

    ህፃናት ሁሌም በሚጫወቱበት ወቅት እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን ክህሎቶች የማዳበር አቅማቸው ከእለት እለት እየጨመረ እንደሚሄድም ነው የሚነገረው።

    በህፃናት ጨዋታ ውስጥ የወላጆች ሚና ምን መሆን አለበት…?

    ከመመልከት ይልቅ አርቦ መጫወት

    ህፃናት በሚጫወቱበት ጊዜ ከመመልከት ይልቅ አብሮ መጫወት ህጻናት በወደፊት ህይወታቸው የራስ መተማመንን እንዲያጎለብቱ እንደሚረዳቸውም የስነ ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

    በጨዋታ ወቅት ህፃናት የመሪነቱን ሚና እንዲይዙ ማድረግ

    ህጻናት በሚጫወቱበት ጊዜ ቁጥጥራችንን ቀለል ማድረግ እና በጨዋታ ወቅት ህጻናት የሚወስኑትን ነገር ማክበር እንዲሁም ፍላጎታቸውን መጠበቅ ከወላጆች ይጠበቃልም ተብሏል።

    ይህም ህጻናት ነገሮችን ያለ ወላጆቻቸው ድጋፍ በራሳቸው እንዲያስተካክሉ አቅም ይፈጥርላቸዋል የተባለ ሲሆን፥ እንዲሁም በራስ የመተማመን አቅማቸውን ከፍ እንደሚያደርግም ተግልጿል።

    ህፃናት እንዲጫወቱ የመጫወጫ ጊዜ እና ቦታ መስጠት

    ህጻናት በሚጫወቱበት ጊዜ ማድረግ የፈለጉትን ነገሮች ሁሉ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸውን ቦታ እና ጊዜ መስጠት በጨዋታ ወቅት ከወላጆች የሚጠበቅ መሆኑም ተገልጿል።

    ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk
    አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጨዋታ ህጻናት በተፈጥሮ የሚከውኑት ተግባር ሲሆን፥ ወላጆችም ይህንን ተግባራቸውን ሊያበረታቱት እንደሚገባ ይነገራል። “ህጻናት በተፈጥሮ የመጫወት ፍላጎት አላቸው፤ ይህም በስነ ህይወት የተዘጋጀላቸው መርሃ ግብር ነው” የሚሉት የእንግሊዝ ቻሪቲ ፕሌይ ሊቀመንብር ኒኮላ በትለር፥ “ጨዋታ ሰዎች እና ሌሎች አጥቢ እንስሳቶች አዳዲስ ነገሮችን የሚማሩበት መንገድ ነው” ብለዋል። እንደ ወላጅ፥ ሁላችንም ለልጆቻችን ሙሉ በሙሉ የመጫወት ነጻነት መስጠት አለብን፤ ምክንያቱ ደግሞ ህፃናት ስለ ራሳቸው እና አካባቢያቸው ስላለው ዓለም የሚማሩት በጫተዋ ስለሆነ ነው። በጫወታ ወቅት ህጻናት ነገሮችን የመረዳት አቅማቸው እና በራስ መተማመናቸው ቀጥለው በተዘረዘሩ አራት ነጥቦች ዙሪያ ይጨጠምራት ተብሏል። 1 አካላዊ፦ ጥንካሬ፣ ሚዛን መጠበቅ እና ሌሎች መሰል አካላዊ ክህሎቶችን በጫወታ ወቅት ያዳብራሉ። 2 ማህበራዊ እና ርህራሄ፦ ነገሮችን ማመዛዘን፣ ማዘዝ፣ ያላቸውን ከሰዎች ጋር መካፈል እና ተራ መጠበቅን ይማራሉ። 3 የፈጠራ እና የአስተሳሰብ አቅም፦ ህጻናት በጨዋታ ወቅት የሚያደርጓቸው ነገሮች የአስተሳሰብ እና የፈጠራ እቀማቸውን ይጨምራል። 4 ቋንቋ እና መግባባት፦ በጨዋታ ወቅት የህፃናት የመናገር፣ ትእዛዝ የመቀበል፣ ከሰዎች ጋር የመግባባት እና ሌሎች ክህሎቶች ይጨምራሉ። ህፃናት ሁሌም በሚጫወቱበት ወቅት እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን ክህሎቶች የማዳበር አቅማቸው ከእለት እለት እየጨመረ እንደሚሄድም ነው የሚነገረው። በህፃናት ጨዋታ ውስጥ የወላጆች ሚና ምን መሆን አለበት…? ከመመልከት ይልቅ አርቦ መጫወት ህፃናት በሚጫወቱበት ጊዜ ከመመልከት ይልቅ አብሮ መጫወት ህጻናት በወደፊት ህይወታቸው የራስ መተማመንን እንዲያጎለብቱ እንደሚረዳቸውም የስነ ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በጨዋታ ወቅት ህፃናት የመሪነቱን ሚና እንዲይዙ ማድረግ ህጻናት በሚጫወቱበት ጊዜ ቁጥጥራችንን ቀለል ማድረግ እና በጨዋታ ወቅት ህጻናት የሚወስኑትን ነገር ማክበር እንዲሁም ፍላጎታቸውን መጠበቅ ከወላጆች ይጠበቃልም ተብሏል። ይህም ህጻናት ነገሮችን ያለ ወላጆቻቸው ድጋፍ በራሳቸው እንዲያስተካክሉ አቅም ይፈጥርላቸዋል የተባለ ሲሆን፥ እንዲሁም በራስ የመተማመን አቅማቸውን ከፍ እንደሚያደርግም ተግልጿል። ህፃናት እንዲጫወቱ የመጫወጫ ጊዜ እና ቦታ መስጠት ህጻናት በሚጫወቱበት ጊዜ ማድረግ የፈለጉትን ነገሮች ሁሉ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸውን ቦታ እና ጊዜ መስጠት በጨዋታ ወቅት ከወላጆች የሚጠበቅ መሆኑም ተገልጿል። ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk
    0 Comments 0 Shares
  • WWW.FANABC.COM
    FBC - ኢትዮጵያ ለኢንዱስትሪና ቢዝነስ ስራ የፈጠረችው ምቹ ሁኔታ በቀጣናው ቀዳሚ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ተቀባይ አድርጓታል - ተመድ
    አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ለኢንዱስትሪ እና ቢዝነስ ስራ የፈጠረችው ምቹ ሁኔታ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚዋ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ተቀባይ ሃገር እንዳደረጋት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት...
    0 Comments 0 Shares