ዳይ እየተሰዳደብን ...

0
0

«ዘውድአለም ታደሰ»

ሰው ሁሉ የፖለቲካ ተንታኝ ሆኖልኛል። ጭራሽ እየሩሳሌምን ለእስራኤል አሳልፈን አንሰጥም! አንሰጥም! አንሰጥም!
እንሰጣለን! እንሰጣለን! እንሰጣለን! ... የሚሉ መፈክሮችን የሚያሰሙ በሁለት ጎራ የተከፈሉ ግሩፖችን እያየሁ ነው!! ኡኡቴ አሉ እማማ ፈለቁ ባላቸው እሩብ ኪሎ ስጋ ይዞ የገቡ እለት :D

ማይ ብራዘር ...... የአለም የመጨረሻ ችጋራም ፣ ደሃ ፣ ብድራም፣ ዱቤያም፣ ረሃብተኛ፣ ኋላቀር፣ ጎስቋላ ሐገር ላይ ተቀምጦ በኢየሩሳሌም ጉዳይ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን መሞከር ቲኒሽ ኪላሽ አያረግም?
እስቲ ኢየሩሳሌምን ለፓለስታይን ከማስመለስህ በፊት ወደብህን አስመልስ፣ እስቲ ጅቡቲን አስመልስ፣ እስቲ ለሱዳን የተሰጠውን መሬት አስመልስ .... አረ ሼም ነው። ጆሯችንን አደማችሁትኮ። ሰው ይታዘባል አይባልም እንዴ?። ዘመዶችህ ሊቢያ ላይ እንደሸቀጥ አካላቸው እየተቸበቸበ ራስህን በፍልስጤም ነፃ አውጪ ግምባር ሂሳብ ታያለህ እንዴ? ታው ኢንጂ ናፍሴ :)

ደሞኮ ኢየሩሳሌም ማን ነች? ምንድን ነች? ቢባል አይኑን የሚየቁለጨልጨው ሁሉ እኮ ነው ሃይማኖታዊ ፅንፈኝነት አንቆ ይዞት የሚለፈልፈው!!

«እስራኤልና ኢትዮጵያ አንድ ናቸው» ይባልልኛላ! ወይ ጉድ .... እስራኤል ኢትዮጵያ ላይ ስንት ግፍና በደል እንደሰራች ፣ በግብፅ በኩል ስንት መስዋእትነት እንዳስከፈለችን ስንቱ ይሆን ሚያውቀው? አሁን እንኳ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ምን ይዛ በምን እንደተደራደረችን እናውቃለን እኮ! ስለዚህ እስራኤልን ከደገፍክ እንዲያው በአቦ ሰጡኝ ሳይሆን በምክኒያት አስረዳኝ! ሰዎቹንኮ ዩሃንስ ራሱ «የእፉኚት ልጆች» ብሏቸዋል ናፍሴ! ኢያነበብን እንጂ!

ደሞ በዚህ ፅንፍ ልክ እንደዛኛው ሃይማኖታዊ ወገንተኝነት ይዞት ይቀውጠዋል ... ኢ ፍትሃዊ ነው ፣ ግፍ ነው ፣ አሜሪካ ትውደም፣ ምናምን ይላል ... ስንቱ ይሆን ስለስድስቱ ቀን ጦርነት ያነበበው? አረብ በሙሉ ተሰብስቦ እስራኤልን ከምድረገፅ ሊያጠፋ ፣ ህፃን ሳይል አዋቂ ሊፈጅ ሲያሴር አይደል እንዴ ቀድማ ነቅታ በመስሪዋ ግብፅ በኩል አላማውን ያንኮታኮተችው?

አለም በፅድቅ ላይ የቆመች ይመስል ዝም ብለህ አታዝገኝ ባክህ! መንግስትህ በቡልዶዘር ቤትህን ደርምሶ ሲሄድ ጭጭ ብለህ ኢየሩሳሌም ላይ ኮንዶሚኒየም ሚሰራልህ ይመስል መቀወጥ ነውር አይደለም እንዴ? አይደለም ወይ?

(ዳይ እየተሰዳደብን ... :)

ፍለጋ
Categories
Read More
Uncategorized
‹‹ እፎፎፎፎይ አሉ እቴጌ ጣይቱ››
አሌክስ አብርሃም‹‹ እፎፎፎፎይ አሉ እቴጌ ጣይቱ››(ከድድ አድማስ ኋላ) እዚህ አራዳ ህንፃ የሚባለው አንደኛ...
By binid 2017-11-25 13:33:42 0 0
Uncategorized
ማበድ ደጉ!
«ዘውድአለም ታደሰ» ዳኒ የሰፈራችን ፅድት ያለ እብድ ነው። ቤተሰቦቹ ሃብታሞች ስለሆኑ ምንም ነገር አይቸግረውም። ልብሱም ንፁህ ነው።...
By Zewdalem 2017-12-14 19:33:57 0 0
Uncategorized
ወርቃማው ደብዳቤ !
(አሌክስ አብረሃም) እንዴት ናት ኢትዮጲያ እንዴት ነው አፈሩ ጤናቸው እንዴት ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ ?ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህናናቸው...
By binid 2017-11-24 20:16:44 0 0
Uncategorized
የዚምባብዌ ጦር ገዢው ፓርቲ ላይ በሚደረገው ጣልቃ ገብነት ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ
ብዙም ያልተለመደው የጣልቃ ገብነት ጉዳይ የተከሰተው ሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ምክትላቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋን ከስራ ካሰናበቱ በኋላ ነው። ከ90...
By Dawitda 2017-11-14 18:21:39 0 0
Uncategorized
የብርሃኑ ፍሬ
እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን...
By Seller 2017-11-24 08:29:50 0 0