-
-
-
-
-
Class of accounting and it
-
-
Recent Updates
-
8ኛው ሽ/የፍርድ ቀን ዘመቻ
ያጎረስክበት ሰሀን
ለሞትህ እጣ ከሆነ
የተኛህበት አልጋ
ለመገነዣህ ካደረ
ያቀፍካት ያች ወዳጅህ
ልብህን ሰብራ ከሄደች
እሷ ግን አንተን ጠርጥራ
ያኔ በቃል ካሰረች
ትናንት የወጣችውን እንጨት
የረገጠችውን ካላየች
አዲስ ጎጆ ፈልጋ
ጎጆህን ካፈረሰች
እሷም ደረቅ አይቀናት
እርጥቡን ከሰበረች
እባክሽ አትሂጅ ስትላት
በድለህኛል ካለች
የስጋህን ደም ረስታ
ሌላ ደም ከፈጠረች
ይቅርታህ ካልመለሳት
እንቢ አሻፈረኝ ካለች
አትድከም ውድ ወዳጄ
እሷ ካንተ እርቃለች
ወደቤት ግቢ ስትላት
አንተን ማመን ካቆመች
እመነኝ ውድ ወዳጄ
አቋም ተክላ ወጣለች
የአንተን ቤት አፍርሷ
በላብህ ቤት ሰርታለች
አልገባህ አለ እንጅ
አንተ የተተውከው
ቤትህ ሲፈርስ ሳይሆን
ቤትህ ሲታደስ ነው
የትናንቱን አስብ......
አዳም ከሞቀ ቤት
ከገነት የወጣው
በፍላጩ አጥንት
ከጉድጓድ የገባው
በሴት ልጅ ምላስ ነው
ያን ጸጋውን ያጣው.
እና ውድ ወንድሜ
ቆፍጠንጠን በልና
ልብህን አበርታ
በሴት ገላ ሳይሆን
ታቀፍ ባምላክ ኩታ
እስኪበቃው ስቆ
አልረካ እያለ
ለነገ ሳቅ ደግሞ
ተስፋውን የጣለ
ማነው ሳቁን ስቆ
በሳቁ የኖረ
ያን ጥርሱን ፈልቅቆ
በሀዘኑ ያረረ
የውስጥን ገመና
ሳቅ እየሸፈነ
ለነገውም ጉዱ
ውስጡን የከፈነ
ሳቅም ሳቅ ይመኛል
እየተጋነነ
መሳቅ ድሮ ቀረ
ዛሬን ከልቡ የሚስቅ የታለ
ውስጡ እያረረ
ሳቅን ሳኩ እያለ
ሳይስቅ ስቆ አዳሪ
አስመስሎ ኖሪ
ሃ ሃ ሃ ብሎ የሚስቅ እንጅ ማነው ተደስቶ አዳሪ
እያነባ የሚስቅ
ስቆ ግን የማያውቅ
ፈገግ ብሎ ሳቂ
ለሰው ይምሰል ብቻ
ጥርሱን አብረቅራቂ
ያሰበው ቢሳካ ባይሳካ
ምኞቱ ላያልቅ
በተደረገለት ልክ ረክቶ ላይረካ
ይሄ ቢሞላልኝ እደሰታለሁ ብለህ
ቃል ብትገባ ለራስህ
ሳቁን አትስቅም
ወሰን ከሌለው ምኞትህ
ልሳቅ ብትልስ
እንዴት ትስቃለህ
ገመናህን ሸፍነህ
ፈገግ ብቻ ትላለህ
ስቆ አዳሪ መስለህ
በውስጥህ ሃዘንህ ተሸክመህ
ደግሞ ራስህ ሳትስቅ
ሰውን ለማስደስት ብለህ
ደፋ ቀና ትላለህ
የሚስቅ ይኖራል ብለህ
አይ ሞኝነትህ
አንተ ሳትደሰት ሳቂታ
አለ ብለህ ማሰብህ
ሰውን ለማስደሰት
ሌት ተቀ ትጥራለህ
ግን ሰውን ማስደሰት አትችልም
ድካም ብቻ ታተርፋለህ
እስኪ ልጠይቅህ
ስቆ የበቃውስ የት ታገኛለህ
መሳቅ ጥሩ ነበር
ከልብ መደሰት
ሳቁ ካላይ ከላይ ሆነብን እንጅ
የሰው ሁሉ ማንነት
ሳቂ የለም እንጅ
ተደስቶ አዳሪ
ይበዛ ነበረ በሳቁ ስቆ ኖሪ
10q አትበለኝ
10q አትበለኝ
ተናግሬ ይውጣለኝ
እኔም ታማሚ ነኝ
ቁሜ መሄዴን አትየኝ
አታመስግነኝ
አልቅሼ ይውጣለኝ
የሆዴን ያንጀቴን ተናግሬ
የፈላው ደሜ እንዲቀዘቅዝልኝ
አታመስግነኝ
ባለኝ ተደስቼ
የማልኖር ደካማ ነኝ
10q አትበለኝ
ብሶት እኔም አለብኝ
የከፋኝ ነኝ
ሳቅን እየሳኩ
ሳልስቅ የምኖር
ምስኪን ፍጡር ነኝ
ይቅርብኝ አታመስግነኝ
የውስጤን ብናገር
ማንም ሰለማይሰማኝ
ያዘነ ላያፅናናኝ
ዝም በለኝ
ሲከፋኝ ተናግሬ እንዲወጣልኝ
የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ.©
ጆሮሽ በደመና እንደተደፈነ
ልብሽ በሰም ቀፎ እንደተቀሰመ
እንደ ይሁዳ ልብ ......
ክህደትሽ ሳያንሰኝ
እንደ ጴጥሮስ ምላስ
እምነትሽ ሲገርፈኝ.
አንች የእግዜር ጠላት
ቂም ይዘሽ ይቅርታ
መቅደስ የምትገቢ
በጠዋት በማታ
ሁሉ አልበቃሽ ብሎ
የኔ በደል ሲቃ
ገመናየን ገፈሽ
ስጋየን አክስተሽ
እምነቴን አሳስተሽ
ከኔ ከወዳጅሽ
የካምፕ ወሬ ሰምተሽ
ቅርጥፍጥፍ አረግሽኝ
አፍሽ መሀል ከተሽ
የፈጠረሽንም ባላውቅ
የማንን ህግ ተግባሪ
በኔ አምላክ ልለምንሽ
በህዝበ አዳም ፈጣሪ
አታንሽኝ ተይኝ በቃ
የራስሽን ኑሮ ኑሪ።
ጆሮሽ እየሰማ፣መስማት ካልቻለ
ዓይንሽ እያየ ፣ማየት ከተከለከለ
አእምሮ እያለሽ፣ ማሰብን ካልቻለ
ልቦና እያለሽ ፣ካላስተዋለ
እንድ ላይ በፍቅር፣
ተሳስቦ መኖር ሳለ
የሚያፈቅር ልብ
ማፍቅር አትችልም ከተባለ
ክፋት የሌለበት ልብ
እንዳያዝን ለሰው ከተከለከለ
መልካም አንደበት
በጎ በጎውን እንዳይናገር ከተከለከለ
ክንቱ ድካም ብቻ ፣ይሄ ሁሉ ምግባር
ሁለት ልብ ውስጥ ከሌለ
መለያየት እንጅ
ሌላ ምን መላ አለ
አንዱ ከልቡ አፍቃሪ
ሌላኛው ሰው ደግሞ
የሰው ልብ ሰባሪ
አንዱ ፍቅርን ተርቦ
ሌትም ቀንም ሲያንባ
ሌላኛው ሰው ደግሞ
ሲመገብ ይኖራል በተነባው እንባ
እሷን ካልመሰላት
አንተ እሷን ማፍቀርህ
ምን ታደርግልሃለች
ካልሆነች የቅርብ ርዳትህ
ቸላ በላት ትቅርብህ
መሆን ካልቻለች ግራ ጎንህ
ስትታመም ካልሆነች ፈዋሽህ
ስታነባ ካልሆነች እንባ አባሽህ
ስትከፋ ካላስደስተችህ
ስትበሳጭ ካላረጋጋችህ
ስታዝን ካላስደሰተችህ
ሲደክምህ ካልረዳችህ
ስታፈቅራት ካላፈቀረችህ
ምን ልታደርግልህ
ኑራስ ምን ልትጠቅምህ
ተዋት ትሄድ
ወደ መሰላት
የምትወዳት ካልመሰላት
ይቆጫታል ያኔ ሲገባት
ደግሞም ከእሷ በላይ አለች
አምላክ ላንተ ያላት
አውቃለሁ ከባድ ነው
የምትወደውን ሰው አጥተህ መኖሩ
አይዞህ ቻል አድርገው
ቢከብድም ልብን ማለቱ እሹሩሹሩ
አንችም የሌላ ነሽ
እሱም የሌላ ሊሆን ነው
በሰላም ይኑርበት ህይወቱን አትበጥብጭው
በቃ ተይው
ስሙን እየጠራሽ እንዲህ ነው አትበይው
ክፉ ነው እያልሽ አትሚው
የሱ ጠላት ዓይኑ ነው
እሷን ባየበት ዓይን
ሌላ ሰው ቢያይ ምነው
በቃ ተይው ጊዜው
እየሮጠ ነው
የፀሃይ ድምቀት በጨለማ ሊተካ
የቀረ ትንሽ ደቂቃ ነው
ዥምበር ልትጠልቅ ነው
ብርሃንና ጨለማ ውጭ አልወጣም እየተባባሉ ነው
የፀሀይዋ ብርታት ተሽንፎ
ጨለማው ሊተካ ነው
የዛሬ የቀኑ ግማሽ
የጨለማ ድል ነው
የነገው ድል ደግሞ
የፀሀይ ነው
የነጋው
ለነገ ነው
ነገ አዲስ ቀን ነው፣ ነገ ሌላ ቀን ነው።
ህይወትም እንደዚያው ነው
ለአንዱ ሲነጋ ለሌላው
ምሽት ነው።
8ኛው ሽ/የፍርድ ቀን ዘመቻ ያጎረስክበት ሰሀን ለሞትህ እጣ ከሆነ የተኛህበት አልጋ ለመገነዣህ ካደረ ያቀፍካት ያች ወዳጅህ ልብህን ሰብራ ከሄደች እሷ ግን አንተን ጠርጥራ ያኔ በቃል ካሰረች ትናንት የወጣችውን እንጨት የረገጠችውን ካላየች አዲስ ጎጆ ፈልጋ ጎጆህን ካፈረሰች እሷም ደረቅ አይቀናት እርጥቡን ከሰበረች እባክሽ አትሂጅ ስትላት በድለህኛል ካለች የስጋህን ደም ረስታ ሌላ ደም ከፈጠረች ይቅርታህ ካልመለሳት እንቢ አሻፈረኝ ካለች አትድከም ውድ ወዳጄ እሷ ካንተ እርቃለች ወደቤት ግቢ ስትላት አንተን ማመን ካቆመች እመነኝ ውድ ወዳጄ አቋም ተክላ ወጣለች የአንተን ቤት አፍርሷ በላብህ ቤት ሰርታለች አልገባህ አለ እንጅ አንተ የተተውከው ቤትህ ሲፈርስ ሳይሆን ቤትህ ሲታደስ ነው የትናንቱን አስብ...... አዳም ከሞቀ ቤት ከገነት የወጣው በፍላጩ አጥንት ከጉድጓድ የገባው በሴት ልጅ ምላስ ነው ያን ጸጋውን ያጣው. እና ውድ ወንድሜ ቆፍጠንጠን በልና ልብህን አበርታ በሴት ገላ ሳይሆን ታቀፍ ባምላክ ኩታ እስኪበቃው ስቆ አልረካ እያለ ለነገ ሳቅ ደግሞ ተስፋውን የጣለ ማነው ሳቁን ስቆ በሳቁ የኖረ ያን ጥርሱን ፈልቅቆ በሀዘኑ ያረረ የውስጥን ገመና ሳቅ እየሸፈነ ለነገውም ጉዱ ውስጡን የከፈነ ሳቅም ሳቅ ይመኛል እየተጋነነ መሳቅ ድሮ ቀረ ዛሬን ከልቡ የሚስቅ የታለ ውስጡ እያረረ ሳቅን ሳኩ እያለ ሳይስቅ ስቆ አዳሪ አስመስሎ ኖሪ ሃ ሃ ሃ ብሎ የሚስቅ እንጅ ማነው ተደስቶ አዳሪ እያነባ የሚስቅ ስቆ ግን የማያውቅ ፈገግ ብሎ ሳቂ ለሰው ይምሰል ብቻ ጥርሱን አብረቅራቂ ያሰበው ቢሳካ ባይሳካ ምኞቱ ላያልቅ በተደረገለት ልክ ረክቶ ላይረካ ይሄ ቢሞላልኝ እደሰታለሁ ብለህ ቃል ብትገባ ለራስህ ሳቁን አትስቅም ወሰን ከሌለው ምኞትህ ልሳቅ ብትልስ እንዴት ትስቃለህ ገመናህን ሸፍነህ ፈገግ ብቻ ትላለህ ስቆ አዳሪ መስለህ በውስጥህ ሃዘንህ ተሸክመህ ደግሞ ራስህ ሳትስቅ ሰውን ለማስደስት ብለህ ደፋ ቀና ትላለህ የሚስቅ ይኖራል ብለህ አይ ሞኝነትህ አንተ ሳትደሰት ሳቂታ አለ ብለህ ማሰብህ ሰውን ለማስደሰት ሌት ተቀ ትጥራለህ ግን ሰውን ማስደሰት አትችልም ድካም ብቻ ታተርፋለህ እስኪ ልጠይቅህ ስቆ የበቃውስ የት ታገኛለህ መሳቅ ጥሩ ነበር ከልብ መደሰት ሳቁ ካላይ ከላይ ሆነብን እንጅ የሰው ሁሉ ማንነት ሳቂ የለም እንጅ ተደስቶ አዳሪ ይበዛ ነበረ በሳቁ ስቆ ኖሪ 10q አትበለኝ 10q አትበለኝ ተናግሬ ይውጣለኝ እኔም ታማሚ ነኝ ቁሜ መሄዴን አትየኝ አታመስግነኝ አልቅሼ ይውጣለኝ የሆዴን ያንጀቴን ተናግሬ የፈላው ደሜ እንዲቀዘቅዝልኝ አታመስግነኝ ባለኝ ተደስቼ የማልኖር ደካማ ነኝ 10q አትበለኝ ብሶት እኔም አለብኝ የከፋኝ ነኝ ሳቅን እየሳኩ ሳልስቅ የምኖር ምስኪን ፍጡር ነኝ ይቅርብኝ አታመስግነኝ የውስጤን ብናገር ማንም ሰለማይሰማኝ ያዘነ ላያፅናናኝ ዝም በለኝ ሲከፋኝ ተናግሬ እንዲወጣልኝ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ.© ጆሮሽ በደመና እንደተደፈነ ልብሽ በሰም ቀፎ እንደተቀሰመ እንደ ይሁዳ ልብ ...... ክህደትሽ ሳያንሰኝ እንደ ጴጥሮስ ምላስ እምነትሽ ሲገርፈኝ. አንች የእግዜር ጠላት ቂም ይዘሽ ይቅርታ መቅደስ የምትገቢ በጠዋት በማታ ሁሉ አልበቃሽ ብሎ የኔ በደል ሲቃ ገመናየን ገፈሽ ስጋየን አክስተሽ እምነቴን አሳስተሽ ከኔ ከወዳጅሽ የካምፕ ወሬ ሰምተሽ ቅርጥፍጥፍ አረግሽኝ አፍሽ መሀል ከተሽ የፈጠረሽንም ባላውቅ የማንን ህግ ተግባሪ በኔ አምላክ ልለምንሽ በህዝበ አዳም ፈጣሪ አታንሽኝ ተይኝ በቃ የራስሽን ኑሮ ኑሪ። ጆሮሽ እየሰማ፣መስማት ካልቻለ ዓይንሽ እያየ ፣ማየት ከተከለከለ አእምሮ እያለሽ፣ ማሰብን ካልቻለ ልቦና እያለሽ ፣ካላስተዋለ እንድ ላይ በፍቅር፣ ተሳስቦ መኖር ሳለ የሚያፈቅር ልብ ማፍቅር አትችልም ከተባለ ክፋት የሌለበት ልብ እንዳያዝን ለሰው ከተከለከለ መልካም አንደበት በጎ በጎውን እንዳይናገር ከተከለከለ ክንቱ ድካም ብቻ ፣ይሄ ሁሉ ምግባር ሁለት ልብ ውስጥ ከሌለ መለያየት እንጅ ሌላ ምን መላ አለ አንዱ ከልቡ አፍቃሪ ሌላኛው ሰው ደግሞ የሰው ልብ ሰባሪ አንዱ ፍቅርን ተርቦ ሌትም ቀንም ሲያንባ ሌላኛው ሰው ደግሞ ሲመገብ ይኖራል በተነባው እንባ እሷን ካልመሰላት አንተ እሷን ማፍቀርህ ምን ታደርግልሃለች ካልሆነች የቅርብ ርዳትህ ቸላ በላት ትቅርብህ መሆን ካልቻለች ግራ ጎንህ ስትታመም ካልሆነች ፈዋሽህ ስታነባ ካልሆነች እንባ አባሽህ ስትከፋ ካላስደስተችህ ስትበሳጭ ካላረጋጋችህ ስታዝን ካላስደሰተችህ ሲደክምህ ካልረዳችህ ስታፈቅራት ካላፈቀረችህ ምን ልታደርግልህ ኑራስ ምን ልትጠቅምህ ተዋት ትሄድ ወደ መሰላት የምትወዳት ካልመሰላት ይቆጫታል ያኔ ሲገባት ደግሞም ከእሷ በላይ አለች አምላክ ላንተ ያላት አውቃለሁ ከባድ ነው የምትወደውን ሰው አጥተህ መኖሩ አይዞህ ቻል አድርገው ቢከብድም ልብን ማለቱ እሹሩሹሩ አንችም የሌላ ነሽ እሱም የሌላ ሊሆን ነው በሰላም ይኑርበት ህይወቱን አትበጥብጭው በቃ ተይው ስሙን እየጠራሽ እንዲህ ነው አትበይው ክፉ ነው እያልሽ አትሚው የሱ ጠላት ዓይኑ ነው እሷን ባየበት ዓይን ሌላ ሰው ቢያይ ምነው በቃ ተይው ጊዜው እየሮጠ ነው የፀሃይ ድምቀት በጨለማ ሊተካ የቀረ ትንሽ ደቂቃ ነው ዥምበር ልትጠልቅ ነው ብርሃንና ጨለማ ውጭ አልወጣም እየተባባሉ ነው የፀሀይዋ ብርታት ተሽንፎ ጨለማው ሊተካ ነው የዛሬ የቀኑ ግማሽ የጨለማ ድል ነው የነገው ድል ደግሞ የፀሀይ ነው የነጋው ለነገ ነው ነገ አዲስ ቀን ነው፣ ነገ ሌላ ቀን ነው። ህይወትም እንደዚያው ነው ለአንዱ ሲነጋ ለሌላው ምሽት ነው።0 Comments 0 SharesPlease log in to like, share and comment! -
የደም አይነትና አመጋገብ
Beki Beki
ለደም አይነትዎ የሚመከሩ የምግብ አይነቶች
ለደም አይነትዎ የሚመከሩ የምግብ አይነቶች
туристический онлайн-справочник
Лучшие Андроид планшеты
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዶክተር ፒተር ዲ
አዳሞ የተባሉ የስነ ምግብ ምሁር “ትክክለኛ ምግብ ለትክክለኛ
የደም አይነት” በሚለው መፅሀፋቸው የእያንዳንዱን የደም አይነት
ባህሪያትና ለደም አይነቶቹ ተስማሚ ያሉትን የምግብ አይነቶች
አስቀምጠዋል።
እያንዳንዱ ሰው የደም አይነቱን ቢያውቅና ተገቢውን የምግብ
አይነት ቢመገብ ረዥም እድሜ፣ ጤናማ ኑሮ እና የተስተካከለ
ተክለሰውነት ይኖረዋል ነው የሚለው መፅሃፉ።
የደም አይነት (Blood Type) ለጤናማ ኑሮ ያለውን ጠቀሜታ
የሚገልፁት ዶክተር ፒተር፥ አንዳንድ ምግቦች ከደም አይነታችን
ጋር ሳይጣጣሙ ሲቀሩ ለበሽታ እንደሚዳርጉና ለሌሎች የደም
አይነቶች በአንፃሩ ጠቃሚ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ።
አንዳንድ ባለሙያዎች በዶክተሩ ሃሳብ የማይሳማሙ ቢሆንም
መፅሃፉ 7 ሚሊየን ኮፒ መሸጡ አለማቀፍ ተቀባይነቱን ያሳያል።
እኛም ከመፅሃፉ የተገኙትን ምክሮች አቅርበናል።
አራቱ የደም አይነቶች
የደም አይነት “ኤ”
እንደ ዶክተር ፒተር ከሆነ ይህ የደም አይነት ከ20 ሺህ አመታት
በፊት ሰዎች ከአድኖ መብላት ወደ ግብርና ሲሸጋገሩ ነው
ጅማሬው። ስለሆነም ይህ የደም አይነት በአትክልትና ፍራፍሬ ላይ
የተመሰረተ ነው።
በዚህም “ኤ” የደም አይነት ያላቸው ሰዎች “ገበሬዎቹ” ተብለው
ይጠራሉ።
የደም አይነት “ኦ”
የረዥም እድሜ ባለቤት የሆነው “ኦ” ከ30 ሺህ አመት በላይ
እድሜ እንዳለው ይነገራል። የደም አይነቱ ከሌሎች የደም
አይነቶች በተለየ በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ይፈልጋል።
የደም አይነት “ቢ”
ለዚህ የደም አይነት ወተትና ወተት ነክ ምግቦች ወሳኝ ናቸው።
ይህን ተከትሎም የ”ቢ” የደም አይነት ያላቸው ሰዎች “ከብት
አርቢዎቹ” ወይም “አዳኞቹ” ተብለው ይጠራሉ። ይህ አይነት የደም
አይነት ለመጀመሪያ ጊዜ የታወቀው ከ10 ሺህ አመት በፊት
እንደነበር ነው የሚነገረው።
የደም አይነት “ኤቢ”
“ኤቢ” በቅርብ ጊዜ የተፈጠረ የደም አይነት መሆኑን ተከትሎ፥ ይህ
የደም አይነት ያላቸው ሰዎች የሚጠቀሙት የምግብ አይነት ከ”ኤ”
እና “ቢ” የደም አይነት ካላቸው ሰዎች የተለየ ነው።
ለእያንዳንዱ የደም አይነቶች የሚመከሩ የምግብ አይነቶች
ለደም አይነት “ኤ”
የሚጠቀሙዋቸው፦
ሁሉንም አይነት ጥራጥሬዎች (ከፓስታና ዳቦ ውጭ)፣ አትክልቶች፣
አቮካዶ፣ ኮክ እና አፕል እንዲሁም ፕሮቲን የያዙ እንደ ኦቾሎኒ እና
አኩሪ አተር
የማይጠቀሙዋቸው፦
ማንኛውም አይነት ስጋ እና ወተት እንዲሁም የወተት ተዋፅኦዎች
ለደም አይነት “ኦ”
የሚጠቀማቸው፦
የባህር ላይ ምግቦች(አሳዎች)፣ ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ እና ሌሎች
ፕሮቲንን ልናገኝባቸው የምንችለው ምግቦች፣ ቆስጣ፣ የሀበሻ
ጎመን እና አበባ ጎመን ለዚህ የደም አይነት ተመራጮች ናቸው።
የማይጠቀማቸው፦
ጥራጥሬዎች (ምስር፣ ኦቾሎኒ፣ አተር)፣ የወተት እና እንቁላል
ውጤቶች እንዲሁም ከስንዴ እና ገብስ የሚዘጋጁ ምግቦች
ለደም አይነት “ቢ”
የሚጠቅማቸው፦
አረንጓዴ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች፣ ቀይ ስጋ፣ አሳ
የማይጠቀማቸው፦
ማንኛውም ጥራጥሬና የቅባት እህሎች (ተልባ፣ ምስር፣ አተር፣
በቆሎ ወዘተ)፣ ኦቾሎኒ፣ የዶሮ ስጋ
ለደም አይነት “ኤቢ”
የሚጠቀማቸው፦
የባህር ላይ ምግቦች (የተለያዩ የአሳ አይነቶች)፣ የወተት
ውጤቶች፣ አትክልቶች፣ የጥራጥሬ እህሎች(አተር፣ አደንጓሬ፣
ባቄላ፣ ሀባብ፣ አፕል እና ሙዝ
የማይጠቀማቸው፦
በቆሎ፣ ቀይ ስጋ፣ ከመጠን በላይ የአልኮል መጠጥና ቡና
ከማብዛትም መቆጠብ ይገባል።
ከላይ የጠቀስናቸው ነጥቦች የምግብ ምርጫዎቻችን ከደም
አይነታችን ጋር ይጣጣማል ወይም ይጋጫል የሚለውን ያሳያል
ብለን እናምናለን።
ማንኛውም ተፈጥሯዊ እድገቱን ተከትሎ ያደገ የምግብ ዓይነትን
መመገብ ለሁሉም የደም አይነቶች ሊመከር ቢችልም ሀኪሞን
ማማከር ግን ተገቢ ነው የሚሆነው።
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ማህበረሰባዊና ቤተሰባዊ ግንኙነቱ
በተጠናከረበት ሀገር የደም አይነትን ለይቶ ለዚያው
የሚስማማውን ለመመገብ አስቸጋሪ ቢመስልም፥ ዋናው ነገር
ጤና ነውና የጤና ባለሙያዎችን በማማከር የምግብ ምርጫችንን
ማስተካከል ተገቢ ነው።
እስካሁን የደም አይነታችን የማናውቅ ከሆነም በቀላሉ
በአቅራቢያችን ካሉ የጤና ማዕከላት ማወቅ ይቻላል።
ምንጭ፦
Healthy Food Team
healthyfoodteam.co
የደም አይነትና አመጋገብ Beki Beki ለደም አይነትዎ የሚመከሩ የምግብ አይነቶች ለደም አይነትዎ የሚመከሩ የምግብ አይነቶች туристический онлайн-справочник Лучшие Андроид планшеты አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዶክተር ፒተር ዲ አዳሞ የተባሉ የስነ ምግብ ምሁር “ትክክለኛ ምግብ ለትክክለኛ የደም አይነት” በሚለው መፅሀፋቸው የእያንዳንዱን የደም አይነት ባህሪያትና ለደም አይነቶቹ ተስማሚ ያሉትን የምግብ አይነቶች አስቀምጠዋል። እያንዳንዱ ሰው የደም አይነቱን ቢያውቅና ተገቢውን የምግብ አይነት ቢመገብ ረዥም እድሜ፣ ጤናማ ኑሮ እና የተስተካከለ ተክለሰውነት ይኖረዋል ነው የሚለው መፅሃፉ። የደም አይነት (Blood Type) ለጤናማ ኑሮ ያለውን ጠቀሜታ የሚገልፁት ዶክተር ፒተር፥ አንዳንድ ምግቦች ከደም አይነታችን ጋር ሳይጣጣሙ ሲቀሩ ለበሽታ እንደሚዳርጉና ለሌሎች የደም አይነቶች በአንፃሩ ጠቃሚ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ። አንዳንድ ባለሙያዎች በዶክተሩ ሃሳብ የማይሳማሙ ቢሆንም መፅሃፉ 7 ሚሊየን ኮፒ መሸጡ አለማቀፍ ተቀባይነቱን ያሳያል። እኛም ከመፅሃፉ የተገኙትን ምክሮች አቅርበናል። አራቱ የደም አይነቶች የደም አይነት “ኤ” እንደ ዶክተር ፒተር ከሆነ ይህ የደም አይነት ከ20 ሺህ አመታት በፊት ሰዎች ከአድኖ መብላት ወደ ግብርና ሲሸጋገሩ ነው ጅማሬው። ስለሆነም ይህ የደም አይነት በአትክልትና ፍራፍሬ ላይ የተመሰረተ ነው። በዚህም “ኤ” የደም አይነት ያላቸው ሰዎች “ገበሬዎቹ” ተብለው ይጠራሉ። የደም አይነት “ኦ” የረዥም እድሜ ባለቤት የሆነው “ኦ” ከ30 ሺህ አመት በላይ እድሜ እንዳለው ይነገራል። የደም አይነቱ ከሌሎች የደም አይነቶች በተለየ በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ይፈልጋል። የደም አይነት “ቢ” ለዚህ የደም አይነት ወተትና ወተት ነክ ምግቦች ወሳኝ ናቸው። ይህን ተከትሎም የ”ቢ” የደም አይነት ያላቸው ሰዎች “ከብት አርቢዎቹ” ወይም “አዳኞቹ” ተብለው ይጠራሉ። ይህ አይነት የደም አይነት ለመጀመሪያ ጊዜ የታወቀው ከ10 ሺህ አመት በፊት እንደነበር ነው የሚነገረው። የደም አይነት “ኤቢ” “ኤቢ” በቅርብ ጊዜ የተፈጠረ የደም አይነት መሆኑን ተከትሎ፥ ይህ የደም አይነት ያላቸው ሰዎች የሚጠቀሙት የምግብ አይነት ከ”ኤ” እና “ቢ” የደም አይነት ካላቸው ሰዎች የተለየ ነው። ለእያንዳንዱ የደም አይነቶች የሚመከሩ የምግብ አይነቶች ለደም አይነት “ኤ” የሚጠቀሙዋቸው፦ ሁሉንም አይነት ጥራጥሬዎች (ከፓስታና ዳቦ ውጭ)፣ አትክልቶች፣ አቮካዶ፣ ኮክ እና አፕል እንዲሁም ፕሮቲን የያዙ እንደ ኦቾሎኒ እና አኩሪ አተር የማይጠቀሙዋቸው፦ ማንኛውም አይነት ስጋ እና ወተት እንዲሁም የወተት ተዋፅኦዎች ለደም አይነት “ኦ” የሚጠቀማቸው፦ የባህር ላይ ምግቦች(አሳዎች)፣ ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ እና ሌሎች ፕሮቲንን ልናገኝባቸው የምንችለው ምግቦች፣ ቆስጣ፣ የሀበሻ ጎመን እና አበባ ጎመን ለዚህ የደም አይነት ተመራጮች ናቸው። የማይጠቀማቸው፦ ጥራጥሬዎች (ምስር፣ ኦቾሎኒ፣ አተር)፣ የወተት እና እንቁላል ውጤቶች እንዲሁም ከስንዴ እና ገብስ የሚዘጋጁ ምግቦች ለደም አይነት “ቢ” የሚጠቅማቸው፦ አረንጓዴ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች፣ ቀይ ስጋ፣ አሳ የማይጠቀማቸው፦ ማንኛውም ጥራጥሬና የቅባት እህሎች (ተልባ፣ ምስር፣ አተር፣ በቆሎ ወዘተ)፣ ኦቾሎኒ፣ የዶሮ ስጋ ለደም አይነት “ኤቢ” የሚጠቀማቸው፦ የባህር ላይ ምግቦች (የተለያዩ የአሳ አይነቶች)፣ የወተት ውጤቶች፣ አትክልቶች፣ የጥራጥሬ እህሎች(አተር፣ አደንጓሬ፣ ባቄላ፣ ሀባብ፣ አፕል እና ሙዝ የማይጠቀማቸው፦ በቆሎ፣ ቀይ ስጋ፣ ከመጠን በላይ የአልኮል መጠጥና ቡና ከማብዛትም መቆጠብ ይገባል። ከላይ የጠቀስናቸው ነጥቦች የምግብ ምርጫዎቻችን ከደም አይነታችን ጋር ይጣጣማል ወይም ይጋጫል የሚለውን ያሳያል ብለን እናምናለን። ማንኛውም ተፈጥሯዊ እድገቱን ተከትሎ ያደገ የምግብ ዓይነትን መመገብ ለሁሉም የደም አይነቶች ሊመከር ቢችልም ሀኪሞን ማማከር ግን ተገቢ ነው የሚሆነው። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ማህበረሰባዊና ቤተሰባዊ ግንኙነቱ በተጠናከረበት ሀገር የደም አይነትን ለይቶ ለዚያው የሚስማማውን ለመመገብ አስቸጋሪ ቢመስልም፥ ዋናው ነገር ጤና ነውና የጤና ባለሙያዎችን በማማከር የምግብ ምርጫችንን ማስተካከል ተገቢ ነው። እስካሁን የደም አይነታችን የማናውቅ ከሆነም በቀላሉ በአቅራቢያችን ካሉ የጤና ማዕከላት ማወቅ ይቻላል። ምንጭ፦ Healthy Food Team healthyfoodteam.co0 Comments 0 Shares
More Stories