ዮሐንስ ወንጌል 3
14-15 ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት
እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።
16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ
ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። 17 ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም
እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።
18 በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን
ተፈርዶበታል። 19 ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ
ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። 20 ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም
እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ 21 እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ
ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።
  • 2 Posts
  • 2 Photos
  • Accountant/Controller at Mesfin Industrial Enginering mekelle
  • Lives in Ethiopia Tigray Mekelle
  • From wag himra sekota
  • Studied Accountant and Finance at Admas Univesity
    Class of Degree
  • Male
  • 05/01/1989
  • Followed by 11 people
Search
Recent Updates
More Stories