የፊታችን ሐሙስ በሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ላይ የሚገኙ ምዕመናንን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዲቪዥን ሃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፉ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በዓሉን ለማክበር ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር በርካታ ምዕመናን፣ ጎብኝዎችና የሀይማኖት አባቶች ወደ ስፍራው እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡
በመሆኑም በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ዘረፋና የተለያዩ ወንጀሎች የሚፈጽሙ ግለሰቦችን ለመቆጣጠር ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከሐረሪ ክልል፣ ከምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ፣ ከመከላከያና ሚሊሺያ ሃላፊዎች ጋር በመወያየት ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
ተጓዦችም ሕገ-ወጥ ድርጊት ሲያጋጥማቸው ለፖሊስ በመጠቆም እንዲተባበሩ አሳስበዋል፤ ምዕመናኑ በሚገኙበት ስፍራና በሌሎች አካባቢዎች የፖሊስ አባላት መመደባቸውን በመጥቀስ።
ምዕመናን የሞባይል አጠቃቀማቸውን፣ ውድ ጌጣጌጦችን እና ገንዘባቸውን በጥንቃቄ መያዝ እንደሚኖርባቸውም ጠቁመዋል።
በስፍራውም ጊዜያዊ የፖሊስ ጣቢያዎች፣ አቃቢ ህግና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት የተቋቋመ በመሆኑ፥ ተጠርጣሪዎች ሲያዙ የምርመራ መዝገባቸው ተጣርቶ አፋጣኝ የፍርድ ሂደትን መሰረት ያደረገ ውሳኔ ይሰጣልም ነው ያሉት።
ምዕመናኑ ማንኛውም ዓይነት ወንጀል ሲፈጸምና ሲያጋጥማቸውም ሆነ ንብረት ወድቆ ሲያገኙ ለጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ፥ በስልክ ቁጥር 025 339 0355 ደውለው እንዲጠቁሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ተሽከርካሪዎችን ለማስተናገድ ከመደበኛ ትራፊክ ፖሊስ በተጨማሪ የተማሪ ትራፊክ ፖሊስ መመደቡን ጠቁመው፥ አሽከርካሪዎችም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከጨለንቆ እስከ ቀርሳ ባለው መንገድ ላይ ተሽከርካሪ እንዳያቆሙ ጠይቀዋል።