• https://www.esetube.com/ethiopian-bank-insurance-job-vacancy/
    https://www.esetube.com/ethiopian-bank-insurance-job-vacancy/
    Ethiopian Bank Insurance Job Vacancy
    Like
    2
    0 Comments 2 Shares
  • ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫ ግንባታ እስካሁን ድረስ ግን ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት አልጀመረም።

    በአፍሪካ የመጀመሪያው ነው የተባለለት ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫ ግንባታው የተጀመረው ከአምስት ዓመት በፊት ነበር።

    የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ፥ ፕሮጀክቱ ሰኔ ወር 2009 ዓመተ ምህረት ነበር ግንባታው ተጠናቆ ስራ መጀመር የነበረበት ብለዋል።

    የፕሮጀክቱ መጓተት ምክንያቶችን አስመልክተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ምስክር ነጋሽ እንደሚሉት፥ ወደ ግንባታው በሚገባበት ጊዜ በወቅቱ የኮንትራት ድርድር የተራዘመበት ሁኔታ መኖሩ በአንደኛነት አንስተዋል።

    በሁለተኛ ደረጃም ከግንባታ ቦታ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ መስተዳድር ንብረቶች የሆኑ በወቅቱ ባለመነሳታቸው እነሱ እስኪነሱ ድረስ የወሰደው ጊዜ እንደነበር ተናግረዋል።

    እንዲሁም ለማመንጫ የሚያገለግሉ እቃዎች ከውጭ አገር ተገዝተው የመጡ ከመሆናቸው አንፃር ግንባታው ስፍራ እስኪደርሱ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት።

    እነዚህን እና ሌሎችንም መሰል ችግሮች አልፎ አሁን አፈጻጸሙ በመቶኛ ዘጠናዎቹ ውስጥ ገብቷል ከተባለ በኋላም ቢሆን በቅርቡ ይጠናቀቃል እየተባለ የ2010 ጥር ወር ላይ ደርሷል።

    ከዚህስ በኋላ መቼ ነው ይህ የሀይል ማመንጫ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው ለሚለው ጣቢያችን ላነሳው ጥያቄ፥ “በጋራ የተነጋገርነው ጊዜው ሲደርስ እናሳውቃለን የሚል ነው” ሲሉ አቶ ምስክር ነግረዉናል።

    ይህ ፕሮጀክት ግንባታው ከመጀመሩ በፊትም ቢሆን በጥናት ሶስት ዓመታትን አሳልፏል፤ በድምሩ ስምንት ዓመታት መሆኑ ነው።

    ኢንጂነር አዜብ አስናቀ፥ ስራው ከ95 በመቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም የተተከሉት ነገሮች በትክክል ይሰራሉ ወይስ አይሰሩም የሚለው ፍተሻ እና ሙከራ መደረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

    ይሁን እንጂ በኮሪደሩ ውስጥ ነዋሪዎች እያሉ ሙከራ ለማድረግ የሚያስችል ሃይል መልቀቅ አይቻልም ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፥ ምክንያቱም አደጋ ሊያጋጥም ይችላል ሲሉ አብራርተዋል።

    የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው እንደሚሉት፥ አሁን ባለው መረጃ በመስመሩ ሁለት የልማት ተነሺዎች ብቻ የቀሩ ሲሆን እነዚህ ለማንሳት በፍጥነት እንፈፅመዋለን ብለዋል።

    አቶ አባተ እንደሚናገሩት፥ የዚህ ፕሮጀክት መጠናቀቅ ምናልባትም ከሌሎቹም ባለድርሻ አካላት በላይ ከተማ አስተዳደሩ አጥብቆ ይፈልገዋል።

    ምክንያቱም ፕሮጀክቱ ለመዲናዋ ፅዳት እና ውበት ትልቅ ፋይዳ ስላለው እኛ ሃላፊነት ወስደን በአጭር ጊዜ የልማት ተነሺዎች ጉዳይን እናስተካክላለን ብለዋል።

    ፕሮጀክቱ እንደ ሃገር ከሚያመነጨው እና ወደ ብሄራዊ ቋት ከሚያስገባው ተጨማሪ የ50 ሜጋ ዋት ኃይል በላይ በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ለሚገኘው የከተማዋ ንፅህና የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ተብሏል።

    ፕሮጀክቱ እንደተወራለት ከሆነ እጅግ ዘመናዊ በመሆኑ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ቀድሞ የደረቅ ቆሻሻ መጣያ የነበረው ስፍራ ሙሉ ለሙሉ ስለሚዘጋ በአካባቢው ነዋሪ ላይ ሲፈጥር የነበረውን መጥፎ ጠረን ያለው ጢስ እና ሽታ ማስቀረት ያስችላል።

    አሁን ቆሻሻ የተከመረበት ቦታም ተስተካክሎ አፈር ከተሞላ በኋላ በአረንጓዴ ተክሎች ተሸፍኖ ወደ መናፈሻ ስፍራነት ይለወጣል።

    ይህ ብቻ አይደለም፤ ቆሻሻው የኤሌክትሪክ ኃይል ካመነጨ በኋላ ተጨምቆ የሚወጣው ውኃ አትክልቶችን ለማልማት፣ በተረፈ ምርትነት የሚወጣው አመድም ለብሎኬት ማምረቻነት ይውላል።

    አቶ አባተ እንደሚሉት እነዚህ እና መሰል ጥቅሞቹ ተደማምረው ነው ከተማ አስተዳደሩ የፕሮጀክቱን መጠናቀቅ ከሁሉም በላይ በጉጉት እንዲጠብቀው እና በባለቤትነት ስሜትም እንዲሰራ ያደረጉት።

    ይሁን እና ምክትል ከንቲባው ፕሮጀክቱ ሲጀመር አካባቢ የካሳ ክፍያው ተጓቶ ስለነበር የልማት ተነሺዎችን በፍጥነት ከቦታው ከማንሳት ጋር በተያያዘ ችግሮች ነበሩ።

    የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀም በበኩላቸው፥ የከተማ አስተዳደሩ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አንስተውልናል።

    በአጠቃላይ ቦታው ከሰዎችና ከቤቶች ነጻ ከተደረገ በኋላም ቢሆን ምናልባትም ከከተማ አስተዳደሩ እውቅና ውጪ ብዙ አካባቢዎች ላይ እንደምናየው ዓይነት ቤቶችን ሰርተው በድጋሚ መኖር የጀመሩ ሰዎች ካሉ ከተማ አስተዳደሩ ማረጋገጥ እና አካባቢውን ነጻ ማድረግ ይጠበቅበታል።
    ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫ ግንባታ እስካሁን ድረስ ግን ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት አልጀመረም። በአፍሪካ የመጀመሪያው ነው የተባለለት ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫ ግንባታው የተጀመረው ከአምስት ዓመት በፊት ነበር። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ፥ ፕሮጀክቱ ሰኔ ወር 2009 ዓመተ ምህረት ነበር ግንባታው ተጠናቆ ስራ መጀመር የነበረበት ብለዋል። የፕሮጀክቱ መጓተት ምክንያቶችን አስመልክተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ምስክር ነጋሽ እንደሚሉት፥ ወደ ግንባታው በሚገባበት ጊዜ በወቅቱ የኮንትራት ድርድር የተራዘመበት ሁኔታ መኖሩ በአንደኛነት አንስተዋል። በሁለተኛ ደረጃም ከግንባታ ቦታ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ መስተዳድር ንብረቶች የሆኑ በወቅቱ ባለመነሳታቸው እነሱ እስኪነሱ ድረስ የወሰደው ጊዜ እንደነበር ተናግረዋል። እንዲሁም ለማመንጫ የሚያገለግሉ እቃዎች ከውጭ አገር ተገዝተው የመጡ ከመሆናቸው አንፃር ግንባታው ስፍራ እስኪደርሱ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት። እነዚህን እና ሌሎችንም መሰል ችግሮች አልፎ አሁን አፈጻጸሙ በመቶኛ ዘጠናዎቹ ውስጥ ገብቷል ከተባለ በኋላም ቢሆን በቅርቡ ይጠናቀቃል እየተባለ የ2010 ጥር ወር ላይ ደርሷል። ከዚህስ በኋላ መቼ ነው ይህ የሀይል ማመንጫ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው ለሚለው ጣቢያችን ላነሳው ጥያቄ፥ “በጋራ የተነጋገርነው ጊዜው ሲደርስ እናሳውቃለን የሚል ነው” ሲሉ አቶ ምስክር ነግረዉናል። ይህ ፕሮጀክት ግንባታው ከመጀመሩ በፊትም ቢሆን በጥናት ሶስት ዓመታትን አሳልፏል፤ በድምሩ ስምንት ዓመታት መሆኑ ነው። ኢንጂነር አዜብ አስናቀ፥ ስራው ከ95 በመቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም የተተከሉት ነገሮች በትክክል ይሰራሉ ወይስ አይሰሩም የሚለው ፍተሻ እና ሙከራ መደረግ ያስፈልጋል ብለዋል። ይሁን እንጂ በኮሪደሩ ውስጥ ነዋሪዎች እያሉ ሙከራ ለማድረግ የሚያስችል ሃይል መልቀቅ አይቻልም ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፥ ምክንያቱም አደጋ ሊያጋጥም ይችላል ሲሉ አብራርተዋል። የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው እንደሚሉት፥ አሁን ባለው መረጃ በመስመሩ ሁለት የልማት ተነሺዎች ብቻ የቀሩ ሲሆን እነዚህ ለማንሳት በፍጥነት እንፈፅመዋለን ብለዋል። አቶ አባተ እንደሚናገሩት፥ የዚህ ፕሮጀክት መጠናቀቅ ምናልባትም ከሌሎቹም ባለድርሻ አካላት በላይ ከተማ አስተዳደሩ አጥብቆ ይፈልገዋል። ምክንያቱም ፕሮጀክቱ ለመዲናዋ ፅዳት እና ውበት ትልቅ ፋይዳ ስላለው እኛ ሃላፊነት ወስደን በአጭር ጊዜ የልማት ተነሺዎች ጉዳይን እናስተካክላለን ብለዋል። ፕሮጀክቱ እንደ ሃገር ከሚያመነጨው እና ወደ ብሄራዊ ቋት ከሚያስገባው ተጨማሪ የ50 ሜጋ ዋት ኃይል በላይ በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ለሚገኘው የከተማዋ ንፅህና የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ተብሏል። ፕሮጀክቱ እንደተወራለት ከሆነ እጅግ ዘመናዊ በመሆኑ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ቀድሞ የደረቅ ቆሻሻ መጣያ የነበረው ስፍራ ሙሉ ለሙሉ ስለሚዘጋ በአካባቢው ነዋሪ ላይ ሲፈጥር የነበረውን መጥፎ ጠረን ያለው ጢስ እና ሽታ ማስቀረት ያስችላል። አሁን ቆሻሻ የተከመረበት ቦታም ተስተካክሎ አፈር ከተሞላ በኋላ በአረንጓዴ ተክሎች ተሸፍኖ ወደ መናፈሻ ስፍራነት ይለወጣል። ይህ ብቻ አይደለም፤ ቆሻሻው የኤሌክትሪክ ኃይል ካመነጨ በኋላ ተጨምቆ የሚወጣው ውኃ አትክልቶችን ለማልማት፣ በተረፈ ምርትነት የሚወጣው አመድም ለብሎኬት ማምረቻነት ይውላል። አቶ አባተ እንደሚሉት እነዚህ እና መሰል ጥቅሞቹ ተደማምረው ነው ከተማ አስተዳደሩ የፕሮጀክቱን መጠናቀቅ ከሁሉም በላይ በጉጉት እንዲጠብቀው እና በባለቤትነት ስሜትም እንዲሰራ ያደረጉት። ይሁን እና ምክትል ከንቲባው ፕሮጀክቱ ሲጀመር አካባቢ የካሳ ክፍያው ተጓቶ ስለነበር የልማት ተነሺዎችን በፍጥነት ከቦታው ከማንሳት ጋር በተያያዘ ችግሮች ነበሩ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀም በበኩላቸው፥ የከተማ አስተዳደሩ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አንስተውልናል። በአጠቃላይ ቦታው ከሰዎችና ከቤቶች ነጻ ከተደረገ በኋላም ቢሆን ምናልባትም ከከተማ አስተዳደሩ እውቅና ውጪ ብዙ አካባቢዎች ላይ እንደምናየው ዓይነት ቤቶችን ሰርተው በድጋሚ መኖር የጀመሩ ሰዎች ካሉ ከተማ አስተዳደሩ ማረጋገጥ እና አካባቢውን ነጻ ማድረግ ይጠበቅበታል።
    Like
    2
    0 Comments 1 Shares
  • በአማራ እና ትግራይ ክልሎች በተያዘው ዓመት በጥናት በተለዩ 45 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ የከርሰ ምድር ውሃ መገኛ አከባቢያዊ ካርታ ሊዘጋጅ መሆኑን የእርሻ እና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር አስታወቀ።

    ሚኒስቴሩ ዘንድሮ በጥናት በለያቸው በሁለቱ ክልሎች የመስኖ ከርሰ ምድር ውሃ፥ አርሶ አደሩን በመስኖ ልማት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ተብሏል።

    በሚኒስቴሩ አነስተኛ መስኖ ልማት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ አወል ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖርት እንደተናገሩት፥ ሚኒስቴሩ የከርሰ ምድር ውሃ መገኛ አካባቢያዊ ካርታ ያዘጋጃል።

    በ2010 ዓ.ም የተጠናቀቀው ይህ ጥናት፥ አቶ ኤልያስ በሁለቱ ክልሎች በ45 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ውስጥ የከርሰ ምድር ውሃ 85 በመቶ መኖሩን አረጋግጧል ብለዋል።

    በዚህ መልኩ የተለዩትን ቦታዎች ካርታ ከማዘጋጀት ጎን ለጎን በቁፋሮ ዘርፍ ስራ ፈላጊ ወጣቶችን በማሰማራት ከየካቲት ወር ጀምሮ የቁፋሮ ስራ ይጀመራል ነው የተባለው።

    ቁፋሮው ሲጠናቀቅ አርሶ አደሩ በሚወጣው የከርሰ ምድር ውሃ በመስኖ ልማቱ ተጠቃሚ እንደሚሆን ተገልጿል።
    በአማራ እና ትግራይ ክልሎች በተያዘው ዓመት በጥናት በተለዩ 45 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ የከርሰ ምድር ውሃ መገኛ አከባቢያዊ ካርታ ሊዘጋጅ መሆኑን የእርሻ እና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ዘንድሮ በጥናት በለያቸው በሁለቱ ክልሎች የመስኖ ከርሰ ምድር ውሃ፥ አርሶ አደሩን በመስኖ ልማት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ተብሏል። በሚኒስቴሩ አነስተኛ መስኖ ልማት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ አወል ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖርት እንደተናገሩት፥ ሚኒስቴሩ የከርሰ ምድር ውሃ መገኛ አካባቢያዊ ካርታ ያዘጋጃል። በ2010 ዓ.ም የተጠናቀቀው ይህ ጥናት፥ አቶ ኤልያስ በሁለቱ ክልሎች በ45 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ውስጥ የከርሰ ምድር ውሃ 85 በመቶ መኖሩን አረጋግጧል ብለዋል። በዚህ መልኩ የተለዩትን ቦታዎች ካርታ ከማዘጋጀት ጎን ለጎን በቁፋሮ ዘርፍ ስራ ፈላጊ ወጣቶችን በማሰማራት ከየካቲት ወር ጀምሮ የቁፋሮ ስራ ይጀመራል ነው የተባለው። ቁፋሮው ሲጠናቀቅ አርሶ አደሩ በሚወጣው የከርሰ ምድር ውሃ በመስኖ ልማቱ ተጠቃሚ እንደሚሆን ተገልጿል።
    Like
    2
    0 Comments 1 Shares
  • የሜርኩሪ ማእድን አለን በማለት ከ9 ሚልየን ብር በላይ አንድን ግለሰብ በማጭበርበር ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በተባሉ አራት ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ።

    ተከሳሾቹ ሬድዋን ሀሩን፣ እስክንድር ሰይድ፣ ሪዳ አሊ እና መሀመድ ቃይድ የሚባሉ ናቸው።

    1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ነዋሪነታቸው በድሬዳዋ ከተማ እና በአዲስ አበባ ሲሆን፥ 3ኛ ተከሳሽ ግን በዜግነት ጅቡቲያዊ ናቸው።

    የከሳሽ አቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር እንደሚያስረዳው፥ ግለሰቦቹ የማይገባቸውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ ቢላል የተባለን ግለሰብ የአቃቤ ህግ ሶስተኛ ምስክር የሆነ መስፍን የተባለ ግለሰብ እንዲያስተዋውቃቸው ያደርጉታል።

    ከዚያም “የሜርኩሪው ባለቤቶች ድሬዳዋ ናቸው፤ ነገር ግን ሜርኩሪውን ለአረቦች ሊሸጡት ስለሆነ አንተ የገንዘብ አቅም ስላለህ ገዝተህ ተጠቀም” በማለት የግል ተበዳይን ያሳምኑታል።

    በመሆኑም በአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ 1ኛ ተከሳሽ ሬድዋን ሀሩንና ሙክታር መሀመድ የተባለ ግለሰብ ከድሬዳዋ የመጡ ግለሰቦች መስለው የግል ተበዳይን ይተዋወቁታል።

    ታህሳስ 21 ቀን 2008 ዓ.ም ከግል ተበዳይ መኖርያ ቤት በመሄድ ሜርኩሪውን እንፈትሸው በማለት ሙክታር መሀመድ የተባለው ግለሰብ ሜርኩሪ የተባለውን ቁስ ከጣቱ ቀለበት ጋር አንድ ላይ በመያዝ እና የተለያዩ ድምጾችን ጮክ ብሎ በማሰማት ሜርኩሪው ሰርቷል በማለት ጨብጠዋቸዋል ነው የተባለው።

    ሙክታር የተባለው ግለሰብ፥ ከዚህ በኋላ ስራውን ከአረቦቹ ጋር ጨርስ በማለት ከቤቱ የወጣ ሲሆን፥ የግል ተባዳይም ባዩት ነገር ተስማምተው 500 ሺህ ብር ከባንክ አውጥተው ለ1ኛ ተከሳሽ እና መሀመድ አብደላ ለተባለ ግለሰብ እንደሰጧቸውም በክሱ ተጠቅሷል።

    ግለሰቦቹ ገንዘቡን ከወሰዱ በኋላም በድጋሜ መጋቢት ወር 2008 ዓ.ም ሜርኩሪውን የሚገዛው አረብ ብሩን የሚልክልህ ባንተ ስም ስለሆነ ከሱ ላይ የሚቀነስ 4 ነጥብ 5 ሚልየን ብር ስጠን በማለት 1ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ገንዘቡን ከግል ተበዳዩ ግለሰብ ወስደዋል።

    በዚህ ያላበቁት ግለሰቦቹ ከወራቶች ቆይታ በኋላ የጠፋነው አረብ አገር ለስራ ሄደን ነበር በማለት 1ኛ ተከሳሽ ስሙን በመቀየር ዶክተር ሪያድ በማለይ ግለሰቡን ከተዋወቀው በኋላ በስራ ጉዳይ አውርተዋል።

    1ኛ ተከሳሽ ግለሰቡን ጅቡቲ ወደብ ላይ የውሃ መቆፈሪያ ማሽኖች አሉኝ በማለት ካሳመነው በኋላ፥ አንተ ሱሉልታ ለውሃ ምርት የሚሆን መሬት ፈልግ በማለት እንደተናገረው አቃቤ ህግ በክሱ አብራርቶታል።

    ማሽኖቹንም ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሚል የ700 ሺህ ብር ቼክ እና 1 ነጥብ 2 ሚልየን ብር በአጠቃላይ ከ9 ሚልየን ብር በላይ ከግለሰቡ በማታለል ወስደዋል ነው ያለው አቃቤ ህግ በክሱ።

    ከሳሽ አቃቤ ህግም ግለሰቦቹ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት የማታለል ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል።

    ተከሳሾቹም ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛው የወንጀል ችሎት የዋስትና ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፥ አቃቤ ህግም ከወንጀሉ ክብደት እና 3ኛ ተከሳሽ የውጭ ዜግነት ያላቸው በመሆኑ በዋስትና ቢለቀቁ ላይቀርቡ ይችላሉ በማለት ዋስትናውን ተቃውሟል።

    ፍርድ ቤቱም በዋስትናው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለከሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

    የሜርኩሪ ማእድን አለን በማለት ከ9 ሚልየን ብር በላይ አንድን ግለሰብ በማጭበርበር ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በተባሉ አራት ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ። ተከሳሾቹ ሬድዋን ሀሩን፣ እስክንድር ሰይድ፣ ሪዳ አሊ እና መሀመድ ቃይድ የሚባሉ ናቸው። 1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ነዋሪነታቸው በድሬዳዋ ከተማ እና በአዲስ አበባ ሲሆን፥ 3ኛ ተከሳሽ ግን በዜግነት ጅቡቲያዊ ናቸው። የከሳሽ አቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር እንደሚያስረዳው፥ ግለሰቦቹ የማይገባቸውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ ቢላል የተባለን ግለሰብ የአቃቤ ህግ ሶስተኛ ምስክር የሆነ መስፍን የተባለ ግለሰብ እንዲያስተዋውቃቸው ያደርጉታል። ከዚያም “የሜርኩሪው ባለቤቶች ድሬዳዋ ናቸው፤ ነገር ግን ሜርኩሪውን ለአረቦች ሊሸጡት ስለሆነ አንተ የገንዘብ አቅም ስላለህ ገዝተህ ተጠቀም” በማለት የግል ተበዳይን ያሳምኑታል። በመሆኑም በአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ 1ኛ ተከሳሽ ሬድዋን ሀሩንና ሙክታር መሀመድ የተባለ ግለሰብ ከድሬዳዋ የመጡ ግለሰቦች መስለው የግል ተበዳይን ይተዋወቁታል። ታህሳስ 21 ቀን 2008 ዓ.ም ከግል ተበዳይ መኖርያ ቤት በመሄድ ሜርኩሪውን እንፈትሸው በማለት ሙክታር መሀመድ የተባለው ግለሰብ ሜርኩሪ የተባለውን ቁስ ከጣቱ ቀለበት ጋር አንድ ላይ በመያዝ እና የተለያዩ ድምጾችን ጮክ ብሎ በማሰማት ሜርኩሪው ሰርቷል በማለት ጨብጠዋቸዋል ነው የተባለው። ሙክታር የተባለው ግለሰብ፥ ከዚህ በኋላ ስራውን ከአረቦቹ ጋር ጨርስ በማለት ከቤቱ የወጣ ሲሆን፥ የግል ተባዳይም ባዩት ነገር ተስማምተው 500 ሺህ ብር ከባንክ አውጥተው ለ1ኛ ተከሳሽ እና መሀመድ አብደላ ለተባለ ግለሰብ እንደሰጧቸውም በክሱ ተጠቅሷል። ግለሰቦቹ ገንዘቡን ከወሰዱ በኋላም በድጋሜ መጋቢት ወር 2008 ዓ.ም ሜርኩሪውን የሚገዛው አረብ ብሩን የሚልክልህ ባንተ ስም ስለሆነ ከሱ ላይ የሚቀነስ 4 ነጥብ 5 ሚልየን ብር ስጠን በማለት 1ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ገንዘቡን ከግል ተበዳዩ ግለሰብ ወስደዋል። በዚህ ያላበቁት ግለሰቦቹ ከወራቶች ቆይታ በኋላ የጠፋነው አረብ አገር ለስራ ሄደን ነበር በማለት 1ኛ ተከሳሽ ስሙን በመቀየር ዶክተር ሪያድ በማለይ ግለሰቡን ከተዋወቀው በኋላ በስራ ጉዳይ አውርተዋል። 1ኛ ተከሳሽ ግለሰቡን ጅቡቲ ወደብ ላይ የውሃ መቆፈሪያ ማሽኖች አሉኝ በማለት ካሳመነው በኋላ፥ አንተ ሱሉልታ ለውሃ ምርት የሚሆን መሬት ፈልግ በማለት እንደተናገረው አቃቤ ህግ በክሱ አብራርቶታል። ማሽኖቹንም ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሚል የ700 ሺህ ብር ቼክ እና 1 ነጥብ 2 ሚልየን ብር በአጠቃላይ ከ9 ሚልየን ብር በላይ ከግለሰቡ በማታለል ወስደዋል ነው ያለው አቃቤ ህግ በክሱ። ከሳሽ አቃቤ ህግም ግለሰቦቹ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት የማታለል ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል። ተከሳሾቹም ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛው የወንጀል ችሎት የዋስትና ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፥ አቃቤ ህግም ከወንጀሉ ክብደት እና 3ኛ ተከሳሽ የውጭ ዜግነት ያላቸው በመሆኑ በዋስትና ቢለቀቁ ላይቀርቡ ይችላሉ በማለት ዋስትናውን ተቃውሟል። ፍርድ ቤቱም በዋስትናው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለከሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
    Like
    2
    0 Comments 1 Shares
  • https://www.youtube.com/watch?v=aRkna00M_Lw
    https://www.youtube.com/watch?v=aRkna00M_Lw
    Like
    2
    0 Comments 1 Shares
  • https://www.youtube.com/watch?v=Hv8M2ay7BV0
    https://www.youtube.com/watch?v=Hv8M2ay7BV0
    Like
    2
    0 Comments 3 Shares
  • https://www.youtube.com/watch?v=d1Bo-AuiB3I&list=RDMMd1Bo-AuiB3I
    https://www.youtube.com/watch?v=d1Bo-AuiB3I&list=RDMMd1Bo-AuiB3I
    Like
    2
    0 Comments 1 Shares
  • 0 Comments 0 Shares