AMHARIC.VOANEWS.COM
የአማጺያን ጥቃት የደረሰባት ማሊ መዲናዋን መቆጣጠሯን አስታወቀች
ማሊ ዛሬ ንጋት ላይ አማጺያን በፖሊስ ማሰልጠኛና ሌሎችም ሥፍራዎች ላይ ያደረሱትን ጥቃትና የተኩስ እሩምታ ተከትሉ፣ መዲናዋን ባማኮ በቁጥጥር ስር ማድረጉን መንግስት አስታውቋል። “ንጋት ላይ የሽብር ቡድኖች ፋላዴ የፖሊስ ማሰልጠኛን ሊቆጣጠሩ ሞክረው ነበር” ያለው ሰራዊቱ፤ አያይዞም፣ “በአሁን ሰዓት የተቀሩትን የማጽዳት ስራ እየተካሄደ ነው” ሲል በመግለጫው አስታውቋል፡፡ ይፋዊ ተጨማሪ መግለጫ እስኪሰጥ ድረስም ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲርቁ ጥሪ ተደርጓል፡፡...
0 Comments 0 Shares